Get Mystery Box with random crypto!

AGARO DISH📡AND TECH.INFO/አጋሮ ዲሽና ቴክ መረጃ

የቴሌግራም ቻናል አርማ agarodishinfo — AGARO DISH📡AND TECH.INFO/አጋሮ ዲሽና ቴክ መረጃ A
የቴሌግራም ቻናል አርማ agarodishinfo — AGARO DISH📡AND TECH.INFO/አጋሮ ዲሽና ቴክ መረጃ
የሰርጥ አድራሻ: @agarodishinfo
ምድቦች: ቪዲዮዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 6.06K
የሰርጥ መግለጫ

♥ቻናላችንን Join ስላደረጉ እናመሰግናለን፡፡😉
ይህንን ቻናል ስትቀላቀሉ
✔የተለያዩ የዲሽ መረጃዎች
✔ አዳዲስ Software 🔥
🌠በአጠቃላይ የፈለጉትን የዲሽ መረጃ ያገኙበታል 👍
Telegram👉 @agarodishinfo
Fb👉 fb.me/agarodishinfo
Tell.📲 251910057393

For any Question 👉 @John_Dish

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2022-08-29 21:51:36 ውድ የ @agarodishinfo ተከታይዎች ሰላም ለእናንተ ይሁን

እንዴት አድርገን በቀላሉ ተወዳጁን TV VARZISH ያለበትን YAHSAT 52.5°E እንደምንሰራ በሰፊው እናያለን እስከ መጨረሻው ተከታተሉን!

Yahsatን ቶሎ  ለመጨረስ በ በትናንሾቹ eurostaሮች qualityው 4/5 በሚለው  ብንሰራው ይበልጥ   ስራችንን ያቀልልናል
ከሁሉም በፊት ግን የ ምድርን WEST, EAST, SOUTH AND NORTH directions መለየት ግዴታ ነው፡፡
በ eastም ሆነ በ west ሚገኙ satelliቶች ሁሉም ዲግሪያቸው ሚጀምረው ከ west ነው፡፡

ይህ ማለት 0° east እና 0° west መነሻቸው አንድ ነው ማለት ነው፡፡

ልዩነታቸው east ወደ ግራ ዲሻችንን ስናዞረው ዲግሪው ይጨምራል፡፡
west ደግሞ  በተቃራኒው ነው፡፡

ለምሳሌ፡ EUTELSAT 7°E ሲሰራ ከ nilesat 7°west ትንሽ ብቻ ነው ወደ ግራ ምናዞረው፡፡
ከዛ Nilesatን መቀጠል እንችላለን ማለት ነው፡፡
ይህ ሚያሳየን የ eastም የ westም መነሻ አንድ መሆኑን ነው።

ወደ ዋና pointaችን እንመለስ

  YAHSAT በ east በኩል 52.5° ላይ ሚገኝ satellite ነው፡፡
ይህን satellite  ለመስራት መጀመሪያ የ ፀሀይን መውጫና መግቢያ መለየት አስፈላጊ ነው፡፡
በ west ተጠልቃለች በ east ትወጣለች፡፡

ዲሻችንን በ ፀሀይ  መውጫ በኩል እናደርጋለን (በ nilesat ተቃራኒ  ማለት 105° አካባቢ ነን ማለት ነው፡፡

በመቀጠል ዲሹን  ወደ በመጠኑ(52.°) ወደ ቀኝ እናዞራለን::
ያ ማለት ከ 105° ወደ 52° አካባቢ ተጠጋን ማለት ነው፡፡
ከዛ receiveራችንን ወይንምfinder ተተቅመን exact(ትክክለኛ) አቅጣጫውን ማግኘት እንችላለን፡፡

  ለመስራት ምን ምን ያስፈልጋል?
HD receiver
ከ 90cm ጀምሮ dish
ከ <=0.5 db LNB
የ dISH ገመድ፡፡
በአብዛኛው ክፍለሀገር በ90cm ዲሽ አይገባም

                       WARNING
በ180 cm dish የምንሰራ ከሆነ dish ምንም አይነት መላላት ወይንም እንቅስቃሰ  ልኖረው አይገባም

ይበጥ አርፍ quality እንድመጣልን በዝናብ ሰዓት እንዳያስቸግረን STRONG LNB ብንጠቀም ይበልጥ አርፍ ነው

   ከዲሹ ፊትለፊት ህንፃ ወይም ዛፍም ሆነ satelliቱን ልጋርደው የምችል ነገር መኖር የለበትም


እነዚህን ካሟላን ቧላ  በreceiver/finder analog ከሆነ በቀላሉ የምናስገባበትን TP አብዛኛዎቹ በእራሱ በvarziah TP  ስለምሞክር/ስለምሰራ ቶሎ quality አይገባም ምርጥ yahsat ማምጫ TP 11938 V 27500 እንሞላለን፡፡

በeurostar ከ70 በላይ ከመጣል ቧላ ወደ HD receiver ቀይረን  varzish TP 11785 H 27500  ስንሞላ አርፍ quality  ይመጣልናል
የሚሰራው በ biss key ነው

TV Varzish & Football-HD

Yahsat 52.5°E
11785 H 27500(TV Varzish & Football-HD)

Biss Key
2020 ABEB CD01 03D1 - TV Varzish
1234 0046 ABCD 0078 - Football-HD

VARZISH biss key ስትሞሉ FOOTBALL HD Eማይሰራላችሁ
FOOT BALL HD biss key ስትሞሉ VARZISH Eማይሰራላችሁ

11785 በተለያየ satellite ሙሉና ለየ አንዳንዳቸው የየራሳቸውን biss key ስትሞሉ ሁለቱን ይሰራሉ

ከዚህ ቀደም post ባደረኩት መሰረት በ finder የምትሰሩ finder  ካገናኘን በኋላ BIG ATTENTION:የ LNB skew እናስተካክላለን፡፡
ምንድነው LNB SKEW

LNB SKEW ማለት የ LNBው  rotational( ዙረት ወይም መሽከርከር) position of LNB ማለት ነው፡፡
LNB ምናዟዙረው የ horizotal እና የ vetical polarized transpondeራችን  ስህተቶችን ወይም ግጭቶችን ለማስቀረት ነው፡፡

የገመድ ማስገቢያው በዚህ መልኩ መሆን አለበት፡፡
ከዛ ዲሹን እስከ 55° ከፍ እናደርጋለን፡፡
zigzag በሆነ way መፈለግ ነው ወዲያው ከች ይላል፡፡
662 views18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 21:50:23 የArabsat/Badr 26°E አሰራር
ውድ ተከታታይዎቻችን ሰላም ለናንተ ይሁን!
እስቲ ስለ Arabsat26°E/Bein Sport ያለበትን/ ሳተላይት እንዴት መስራት እንዳለብን ትንሽ ልበላችሁ።
ይህ ሳተላይት የBein Sport እንጂ ሌሎች ብዙም ለኛ የሚያስፈልጉን ቻናሎች አለበት ብዬ አላስብም።
ለማንኛውም ወደ አሰራሩ ስንገባ
ከዚህ በፊት እንዳልነው የትኛውንም ሳተላይት ስንሰራ ማወቅ ያለብን ነገር ቢኖር ሳተላይቱ የለበትን ዲግሪ(°) መሆኑን አትዘንጉ።
ለምሳሌ ናይልሳት በ7°ምዕራብ/West ላይ ነው የሚገኘው። የየትኛውም ሳተላይት መነሻ ደግሞ ምዕራብ/West ነው። ለምሳሌ Eutelsat 7°E ስንሰራ ሰሀናችንን ከናይልሳት ትንሽ ብቻ ነው ወደግራ አርገን ከፍ የምናረገው።
ይህ የሚያሳየን  የምንሰራው ሳተላይት በEast Direction ከሆነ ዲግሪው ሲጨምር ሰሀናችንን ወደግራ እያረግን ከፍ እንደምናደርገው ነው።
ወደ ርዕሳችን ስንመጣ፦
Arabsatን ለመስራት የሚያስፈልጉንን ማቴሪያሎች እናዘጋጃለን፤ ማለትም አንድ ሰሀን(ከናይልሳት ሌላ)፣ አንድ ተጨማሪ LNB እና አንድ HD ዲኮደር(ረሲቨር) ናቸው።
በመጀመሪያ ስራችንን ለማቃለል ናይልሳት እንሰራለን(11512V27500) በመቀጠል የናይልሳትን Q. ካገኘን በኋላ እዛው ሰሀኑን በማሰር ረሲቨራችን/ፋይንደራችን ላይ 11919H27500 እንሞላና ከሰሀኑ ኋላ በመሆን ሰሀናችንን 15°ዲግሪ አካባቢ ወደ ግራ እናረጋለን ከዛ ትንሽ ከፍ ማድረግ ነው Quality ወዲያውኑ ከች ይላል።
@agarodishinfo
587 viewsedited  18:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 21:49:44 የethiosat/NSS12 57°E አሰራር።
አምብበው ስጨርሱ #Forward  ማድረግዎን አይርሱ!!
በመጀመሪያ ethiosatን ከመስራታችን በፊት የሚያስፈልጉንን ማቴሪያሎች አንድ በአንድ እናያለን።

1. አንድ ሪሲቨር  HD/SD HD ቢሆን ግን ይመረጣል ምክንያቱም አብዛኛዎቹ ቻናሎች ኤች ዲ ናቸው።
2. አንድ 60cm እና ከዛ በላይ ሰሀን (የTV Varzish channel ተጠቃሚ ከሆኑ መጨመር የሚጠበቅባችሁ 1 LNB ብቻ ነው)።

3. አንድ LNB( ናይልሳት ላይ የነበረውን ሰሀን የምታዞሩ ከሆነ ተጨማሪ አያስልግም!)
4.አንድ DisQueC (ሁለት LNB እና ከዛ በላይ የምትጠቀሙ ከሆነ ብቻ)
 
  አሰራር 
ከዚህ በፊት እንዳልነው የትኛውንም ሳተላይት ስንሰራ ማወቅ ያለብን ነገር ቢኖር ሳተላይቱ የለበትን ዲግሪ(°) መሆኑን አትዘንጉ።
ለምሳሌ ናይልሳት በ7°ምዕራብ/West ላይ ነው የሚገኘው። ethiosat ደግሞ በ57ዲግሪ በስተምስራቅ/East አቅጣጫ ነው።  የየትኛውም ሳተላይት መነሻ ደግሞ ምዕራብ/West ነው። ለምሳሌ Eutelsat 7°E ስንሰራ ሰሀናችንን ከናይልሳት ትንሽ ብቻ ነው ወደግራ አርገን ከፍ የምናረገው።
ይህ የሚያሳየን  የምንሰራው ሳተላይት በEast Direction ከሆነ ዲግሪው ሲጨምር ሰሀናችንን ወደግራ እያረግን ከፍ እንደምናደርገው ነው።

ሌላው  የሰሀናችንን Azimuth's እና እና Elevation ማስተካከል ነው። 
Azimuth ማለት ሰሀናችንን ወደ ግራና ወደ ቀኝ በማሽከርከር የምናገኘው ውጤት ነው። 
@agarodishinfo
Elevation ደግሞ ሰሀናችንን ከፍና ዝቅ እያረግን Quality የምንፈልግበት አካሄድ ነው።
@agarodishinfo
የናይልሳት ተጠቃሚ ከሆንን ሰሀናችንን  ከነበረበት Nilesat ፍጹም ተቃራኒ እናደርገዋለን።
ይህ ማለት የሰሀናችን Azimuth's ትክክለኛውን አቅጣጫ አገኘ ማለት አይደለም!!
20°አካባቢ ወደ ቀኝ እንመልሰዋለን
(አንዳንድ ዲጂታል Finderዎች የራሳቸው Compass አላቸው)
ቀጥሎ ዲሻችንን ወደ ሰማይ በመጠኑ ከፍ ማድረግ
በመቀጠል ይህንን ቴክኒካዊ መረጃ   Finderአችን/Recieverአችን ላይ 11105 H 45000 /11545 Hor 30000 ሞልተን  በያዝነው መፍቻ ላላ አርገን በትንሹ ወደ ቀኝ ወደ ግራ እና ወደላይ ወደታች እያረግን QUALITY እስኪመጣልን ዞር ዞር  ማድረግ። Quality በትንሹም ቢሆን ካገኘን በኋላ LNBያችንን ግን ማዟዟር አንርሳ!
የethiosat LNB ገመድ ማስገቢያ   ወደ ጎንም ሙሉ በሙሉ አይደለም ወደ ታችም ሙሉ በሙሉ አያዘቀዝቅም።  
ይህንን ሳተላይት ስትሰሩ በአዲሱ ፍሪኩዊንሲ ማለትም በ 11545 Hor 30000 ብትሰሩ
ይቀላችዋል Quality ከመጣላችሁ በኋላ ሌሎቹን Freq. ቼክ ማድረግ።
@agarodishinfo
ከtv varzish ጋር ለምትሰሩ ሰዎች መጀመሪያ tv varzish ስሩ ከዛ በኋላ  የኢትዮሳትን አንድ LNB በቀኝ በኩል ደርቡበት።
አሁን ባለው መረጃ ኪትዮሳትን በ4 ፍሪኩዌንሲዎች እናገኘዋለን
11545 Hor 30000 ይህ የ SD ቻናሎች የሚገቡበት ፍሪኩዌንሲ ነው።

NSS12 57°E/ethiosat
11105 Hor 45000
11165 Hor 45000
10985 Hor 45000
11545 Hor 30000

ሌሎች የቻናላችን  መረጃዎች እንዲደርስዎ JOIN ያድርጉልን! JOIN ማድረግዎ የምንለቃቸው መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርስዎ ይረዳል።

ለሌሎች እንዲደርስ #ሼር ያድርጉ

FOLLOW US ON
   Facebook
         
fb.me/agarodishinfo

FOLLOW US ON
   Telegram
          
https://t.me/joinchat/AAAAAFec0jSOBhLmkaph1Q
582 viewsedited  18:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 21:48:05 Amos 4°Wን  እንዴት መስራት እንችላለን እና  ምን ምን  ያስፈልጋል ላላችሁኝ
ቻናሎቹን ለመስራት የሚያስፈልጉ ነገሮች:-
---------------------------------------------
የረሲቨር Wifi Antena 250-350 ብር
ሰርቨር የሚቀበል HD ረሲቨር (850 -1600 ብር)-ከሌላችሁ ብቻ!
1 ተጨማሪ LNB (Nile sat ላይ የሚደረብ)
የአሰራር ቅደም ተከተል:-
     -----------------------------
1. NAHOO,KANA ያለበትን የ Nilesat ዲሽ በግምት ከ 3-4 cm ትንሽ ወደ ላይ (የዲሹ አቅጣጫ ሳይቀየር) ከፍ ማድረግ እና ማሰር!
2. ተጨማሪውን LNB ድሮ ከነበረው እላዩ ላይ ትይዩ 1 cm ወደ ኋላ ሳብ በማድረግ ደርቦ በደንብ ማሰር!!
3. ድሮ  Nilesat የነበረውን LNB ኬብል በማውጣት የተደረበው LNB ላይ ማሰር!
የ ላይኛው LNB Nilesat 7°W ይሆናል!!
የታችኛው LNB Amos 4°W ይሆናል!!
4. ከሁለቱ LNB የወጣውን ገመድ ወደ Switch ገቢ ማስገባት ከዚያ የ ስዊቹን ወጭ ወደ ቤት ወስዶ ሬሲቨሩ ላይ ማሰር!!
5. የ ሬሲቨሩ "Menu" በመግባት Switch ገቢ የታሰረበትን disc port  ማስተካከል።
6. ከዚያም 11031 V 27500 ትራንስፖንደር በመጠቀም ቻናሎቹን ማስገባት!!
7. በመጨረሻም Menu ከዛም ኔትወርክ ሴቲንግ ውስጥ በመግባት ፥ መጀመሪያ ከስልካችሁ wifi hotspot በመክፈት ሬሲቨሩ በተገጠመው Wifi አንቴና አማካኝነት ማገናኘት። ከዚያም Server setting (እንደየ ሬሲቨሩ አይነት ይለያያል) ውስጥ በመግባት የ Gshare አካውንት መሙላት!!
8. ሰርቨሩን ሞልተው ok ብለው ሲጨርሱ ትንሽ ከ 5  -30sec. መጠበቅ!
9. ከዚያም የ ሚገራርሙ
Sport Channes
MTV MUSIC
MTV DANCE
VH1 MUSIC
Film Channels
Best kids Channels
Science & Family Channels
etc. ያለገደብ ሁሌ ያያሉ !!
ማሳሰቢያ:አነዚህን ቻናሎች ለመክፈት ተመራጩና ርካሹ ቨርቨር Gshare Plus ነው!!
ይህ ሰርቨር ለአብዛኛዎቹ አሁን ገበያ ላይ ላሉት ሬሲቨሮች መሆን ይችላል
ከሬሲቨሮቹ መካከል:-
LEG H14
LEG H14pro
LEG M18
LEG N24
LEG N24plus+
LEG N24pro&
LEG N24pro Iron
LIFESTAR 9200,9300HD,gold
LIFESTAR 9200,9300HD Smart
LIFESTAR 9200,9300,1000,2000,3000,4000HD(ባለ
አንድ ፍላሽ)
Lifestar 1000++HD
LIfestar 1000++Platinium
Lifestar 9090HD
Vanstar V8, V8pro, V8 Plus እና የመሳሰሉት ናቸው

#ማወቅ_ያለብን_ነገር(Expectations)

ማንኛውም Card Sharing Service የሚጠቀም ሰው ማወቅ ያለበት ነገር፥  ሁሌም  Gshare Plus ወይም ማንኛውንም ሰርቨር  ስንጠቀም ኢንተርኔት ሊኖር ይገባል። ይሄ ኢንተርኔት የሚያስፈልገው። የሞላነው የ ካርድ ቁጥር በ online server እየተነበበ በ encryption የተቆለፉ ቻናሎችን መክፈት ስላለበት ነው። ስለዚህ ቢያንስ ጥሩ የ 2G ኢንተርኔት ሊኖረን ይገባል።
ጭራሽ ምንም ኢንተርኔት የሌለበት አካባቢ ይህንን አገልግሎት እየተቆራረጠ ስለሚያስቸግራችሁ ባትጠቀሙ ይመረጣል። ነገር ግን ከ ባዶ ይሻላል ካላችሁ አገልግሎቱ እና አሰራሩ ብዙ ወጭ ስለማይጠይቅ፥መጠቀም ትችላላችሁ። ኢንተርኔት ያለበት በተለይ ከተማ አካባቢ ያላችሁ ግን ይህንን ምርጥ ቴክኖሎጂ መጠቀም ግድ ይላችኋል።
የ ኢንተርኔት ፍጆታው በጣም ዝቅተኛ ነው ። ለምሳሌ የ 3 ብር ፓኬጅ ብትገዙ ለ 24 ሰአት ያለ እረፍት ይሰራል!! ነገር ግን ስልካችሁን ዳታ ሪስትሪክት ማድረጋችሁን አትርሱ፤ ዳታ ስትከፍቱ ስልኩ ላይ ያሉት Applicationዎች Background በራሳቸው ስለሚበሉ ለአሞስ ብቻ ሳይሆን ኢንተርኔትም ስትጠቀሙ ማጥፋት አለባችሁ።
አሞስ ለመጠቀም ብር ይበላብኛል ብላችሁ የምትፈሩት መጀመሪያ ስልካችሁን ቼክ አርጉ
ዳታ ክፍት መሆኑን እንጂ የተለየ የሚወስደው MBየለም

DSTV ቤቶች ለምን ኳስ ለማሳየት አልተጠቀሙበትምን??
መልስ: አሞስ በኮኔክሽን ስለሚሰራ እንደማንኛውም የክፍያ ቻናሎች(Bein Sports,DSTV) እናሳይ ብንል ያው ለአንድ ሰከንድም ቢሆን ቀጥ ቀጥ ማለቱ አይቀርም፤ ደምበኞች ደግሞ እዲቀየሙን አንፈልግም!!

አሞስ ስታሰገጥሙ የምታገኙዋቸው የታላላቅ ሊጎች የእግርኳስ ወድድሮች
እንግሊዝ ፕሪሜር ሊግ
ስፔን ላሊጋ
ጣሊያን ሴሪአ
የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ
ጀርመን ቡንደስሊጋ
በፈረንሳይ ሊግ 1

በቅናሹና በተወዳጁ 𝗚𝘀𝗵𝗮𝗿𝗲_𝗣𝗹𝘂𝘀 ፈታ በሉበት
𝗚𝗦𝗵𝗮𝗿𝗲 -𝗣𝗹𝘂𝘀 ኮዱን ከፈልጋችሁ  ከኛ ማግኘት ትችላላችሁ
@Ju_admin
@John_dish
ላይ ይጠይቁን
ወይም
0938095915

@agarodishinfo
@agarodishinfobot
584 viewsedited  18:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 21:46:21 ጣበት ወቅት ከፍተኛ ጥንቃቄዎችን ማድረግ
ይገባናል፡፡
-ምንም እንኳን የተቻለንን ጥንቃቄ ብናደርግም በተለያየ የስራ
አጋጣሚ ሊደርሱብን የሚችሉ ቀለል ያሉ ጉዳቶች ሊኖሩ
ይችላሉ፡፡ በመሆኑም አንድ አነስ ያለች የመጀመሪያ ህክምና
እርዳታ መስጫ መሳሪያዎችን የያዘች ሳጥን ቢኖረን እጅግ
በጣም ጥሩ ነው፡፡ በውስጧም በርከት ያሉ የቁስል ፕላስተሮች፣
ንፁህ ጥጥ፣ ፋሻ፣ የተጠቀለለ ነጭ የቁስል
ፕላስተር፣በፕላስቲክ ጠርሙስ የታሸገ አልኮል (በተለምዶ ጂቢ
የምንለው) እና ሌሌችንም የያዘች ብትሆን እጅግ በጣም
ተመራጭ ነው፡፡ ያስታውሱ ምንጊዜም ቢሆን ለጥንቃቄ ቅድሚያ
መስጠት ይኖርብናል፡፡ ድንገት እንኳን በዛገ ቆርቆሮ ወይም
ሚስማር የመቆረጥ ወይም የመወጋት አደጋ ቢገጥመን
የመንጋጋ ቆልፍ በሽታ ተጠቂ እንዳንሆን በፍጥነት በአልኮል
በተነከረ ንፁህ ጥጥ የተቆረጠውን የሰውነታችን ክፍል በማከም
በቁስል ፕላስተር አሽገን በአቅራቢያችን ወደሚገኝ የህክምና
ተቋም መሄድ ይኖርብናል፡፡
-በክረምት ወራት በዝናብ ምክኒያት በሚኖር ርጥበት
መሰላሎችና ጣራ ላይ አዳልጦን የመውደቅ አደጋ
እንዳይደርስብን ርጥበቱ ሙሉ በሙሉ ተወግዶ እንኪደርቅ ድረስ
መጠበቅ ይኖርብናል፡፡ በበጋና እጅግ ፀሀያማ በሆነ ወቅት
በፀሀይ ብርሃን ምክኒያት የቆርቆሮ ጣራዎች በተለይም ከ ረፋዱ
5፡30 ሰአት ጀምሮ እስከ ቀትሩ 9፡30 እጅግ ከፍተኛ ሙቀትና
ግለት ስለሚፈጥሩ ስራችንን በአግባቡና በተዝናኖት
እንዳናከናውን ከፍተኛ የሆነ መሰናከል ሊሆኑብን እንደሚችል
ግልፅ ነው በመሆኑም በተቻለ መጠን ከተጠቀሱት ሰአታት
ውጭ ባሉት ጊዜያት ስራችንን በአግባቡና በተረጋጋ መንፈስ
ማድረግ ይሮርብናል፡፡ በከፍተኛ ሙቀት ላይ ጣራ ላይ ወጥቶ
ለረጅም ጊዜ መቆየት የአይን ብዥታን፣ያልታሰበ በአፍንጫ
ውስጥ ደም መውረድ (ነስር) ፣ ራስ ማዞርና የእይታ በከፊል
መጋረድ፣ ከባድ ራስ ምታትና ማናጃይትስ ወይም ማጅራት ገትር
እንደሚያስከትል ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ ወደ አለባበሳችን ደግሞ
ስንመጣ እግራችንን እንደፈለግን የሚያንቀሳቅሱንን ሱሪዎችንና
(እንደ ቱታ ያሉ) በቀለማቸው ሙቀትን የማይስቡ (ከጥቁር
ከነጭ ውጭ የሆኑ) ነፀብራቅን የማይፈጥሩ መሆን
ይኖርባቸዋል፡፡ ጫማዎቻችን የታችኛው ሶላቸው በደንብ መሬት
መቆንጠጥ የሚችልና ሙቀት አዝልቀው የማያስገቡ መሆን
ይኖርባቸዋል፡፡ ኮፍያዎችን የፀሀይ ሙቀት ሃያል በሚሆኑባቸው
ጊዜያቶች ማድረግ ጥቅሙ የጎላ ሲሆን ነገር ግን ኮፍያዎችን
ለረጅም ጊዜ ማድረግ ራሰ በራነትን ሊያስከትል ስለሚችል
አደራረጋችን ላይ ገደብ ልናበጅለት ይገባል፡፡
ማንኛውም የዲሽ ባለሞያ ሊኖረው የሚገቡ ስነ-ምግባራት:-
-ሁሉንም የህብረሰብ ክፍል ፍፁም ትህትና በተሞላበትና በቀና
መንገድና በእኩል አይነት መንገድ ማስተናገድ
-በስልክም ሆነ በአካል ከማንኛውም የህብረሰብ ክፍል
የሚመጡ ቅሬታዎችን በቅን አእምሮ ተቀብሎ በአግባቡ ትህትና
በተሞላበት መልኩ ማስተናገድ
-ለሰራበት ስራ ተገቢውን የሆነ ክፍያ መጠየቅና በተቻለ መጠን
በኢኮኖሚያቸው ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የማህበረሰብ
ክፍሎች አስተያየት በማድረግ መጠነኛ ክፍያ ማስከፈል
-አገልግሎት በሚሰጥበት ሰዓት የመጨረሻ አቅሙን ተጠቅሞ
ጥራት ያለው የማያዳግም ስራ በመስራት ደንበኞቹን ለማርካት
የላሰለሰ ጥረት ማድረግ፡፡ -ከአቅም በላይ ለሚሆኑ ችግሮች
ቀደም ያለ ጥልቅ እውቀትና ግንዛቤ ላላቸው የስራ አጋሮች
ግልፅ የሆነ ጥያቄ ማድረግ፡፡
-አገልግሎት እንዲሰጥ ጥሪ በሚደረግለት ሰዓት ቦታው
ለመድረስ የሚወስድበትን ጊዜ ገምቶ ማሳወቅና በሰዓቱ
መገኘት፡፡ በስራ መደራረብ ወይም በተለያያ ግላዊ ምክኒያቶች
ደንበኞችን ማስተናገድ የማይችልበት ሁኔታ ሲከሰት ለሌሎች
በቅርብ ለሚገኙ የስራ አጋሮቹ ማስተላለፍ ወይም
እንደማይመቸው መግለፅ፡፡
-በገበያው ላይ የሚገኙትን ትክክለኛ የዲሽ እቃ ዋጋዎች
ለህብረተሰቡ ግልፅ በማድረግ ግልፀኝነትን ማስፈን
-በራስ ላይ አደጋ ሊጥሉ የሚችሉ ወይም ተመሳሳይ ይዘት
ያለቸውን ስራዎችን ለራስ ክብርና ለሀገሪቱ ህልውና ሲባል
ባለመስራት የዜግነት ግዴታን መወጣት
-ባለው እውቀት ያለመመካትና ከሌሎች ዲሽ ቴክኒሻኖች ጋር
ያለ ምንም ክፍያ የሚያውቁትን በግልፅ ማካፈልና በተለያዩ
የመወያያ መድረኮች የሚገበዩትን እውቀት ለአጋር ባለሞያዎች
በስፋት ማዳረስ፡፡
እና ሌሌች መልካም ስነምግባርን የሚያመላክቱ ስራዎችንና
ባህሪያትን ማዳበር
ውድ አንባቢያን ከፅሁፉ መጠነኛ ትምህርት እንዳገኛችሁበትና
እንደወደዳችሁት ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ በቀጣይ ከዚህ ፅሁፍ ጋር
በተያያዘ ተከታታይ ፅሁፎችን በጥሩ ትንታኔ አጅበን ይዘን
እንድንመጣ ያግዘን ዘንድ የፌስቡክ ገፃችንን ላይክ በማድረግ
ኮሜንት በመፃፍና ኮፒ ፔስት ከማድረግ ታቅበው ይህንን ፅሁፍ
ሼር በማድረግ ጥቂት አእምሮአዊ እርካታ እንድናገኝ እንዲረዱን
በትህትና እንጠይቃለን፡፡ በቀጣይ አስተማሪ ፅሁፋችን
እንስክንገናኝ ድረስ ሰላሙን ሁሉ ያብዛላችሁ እላላሁ፡፡
@agarodishinfo
615 viewsedited  18:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 21:45:18 ከቦታ ቦታ ወድቀውም
ሆነ በአስቸጋሪ ሁኔታ ተገኝተው በመነሳት አሁን በገበያ ላይ
ከሚገኙ የተንቀሳቃሽ ስማርት ስልኮች የላቀ አቅም እንዳለቸው
ያስመሰከሩ ተንቀሳቃሽ ስልኮችን መያዝ፡፡ የስማርት ስልከ መያዝ
ወቅቱ ያፈራቸውን መረጃዎች በአቅራቢያችን እንዲኖሩንና
ሌሎች ተጨማሪ ነገሮችን ያለ ብዙ ድካም ለማግኘት
ስለሚረዱን በጥንቃቄ ከተያዙ የማይከፉ ቢሆንም ከላይ
በተጠቀሱት ምክኒያቶች አብዝቶ መጠቀሙ ጉዳቱ የሚያመዝን
መስሎ ስለሚታየን በተገልጋዮች ዘንድ የሚገኘውን የሲምካርድ
ቁጥር በኖርማል ሀንድሴትዎ፣ ለግላዊ ጉዳይ የሚጠቀሙበትን
ሲም ካርድዎ ደግሞ በስማርት ስልክዎ በማድረግ የተለመደ
ህይወትዎን ከቢዝነስ ህይወትዎ በተለያዩ ሁለት ሲም ካርዶች
አማካኝነት እንዲመሩ እንመክራለን፡፡
-አንድ ባለ አንድ አውትፑት (ገመድ ተቀባይ) LNB እና አንድ
ባለ ሁለት አወትፑት LNB ዎች ብንይዝ ለስራ በምንጓጓዝበት
ወቅት የተቃጠሉ፣ ጉዳት የደረሰባቸውን፣ የደከመ የምስል ጥራት
የሚያወጡ LNB ዎችን ለመለየትና በምትኩ በመግጠም
ከአላስፈላጊ ድካምና ወጪ ራሳችንን ማዳን እንችላለን፡፡
ያስታውሱ ሁሌም የተቃጠለ፣የተጎዳ ወይም የደከመ የምስል
ጥራት የሚያወጣ LNB በአዲስ በምንተካበት ወቅት ወዲያውኑ
በምትኩ ለራሳችን መግዛት እንዳለብን በፍፁም መዘንጋት
የለብንም፡፡
-በቤት ኪራይ ምክኒያት ሰዎች ከቦታ ቦታ ሲንቀሳቀሱ ከዚህ
ቀደም የነበረው የዲሽ ገመድ ሳህኑን ከምንተክልበት አዲስ ቦታ
ራቅ ያለ ሊሆን ስለሚችልና በተለያየ አጋጣሚ ገመዶች
የመተጣጠፍና የመቀጥቀጥ አደጋዎች ስለሚደርስባቸው
ለመቀጠያና ለመተኪያ የሚሆን ከ20 ሜትር ያላነሰ የዲሽ
ገመድ ለአያያዝ አመቺ በሆነ መልኩ መያዝ፡፡ ከገመዱ
የሚጠቀሙትን በሜትር አስልተው ከሙያ ዋጋ ክፍያዎ ጋር
ማስከፈልዎንና በምትኩም አዲስ ገመድ መግዛትን አይርሱ፡፡
-ነፃ የኳስ ቻናሎችን ወይም ሁለት LNB የሚጠይቁ ስራዎችን
በምንሰራበት ወቅት ለተጨማሪው LNB ትክክለኛ መቀመጫ
ቦታ ይሆን ዘንድ በጋራጅ ቤቶች ለዚሁ አገልግሎት የተሰራ ዘንግ
(የገበያ ስሙም ዘንግ ነው) መግዛትና መያዝ፡፡
በተለያዩ ቦታዎች ለማጠናከሪያነት ሊጠቅሙን የሚችሉ የተለያዩ
አይነት ሚስማሮችን መያዝ፡፡
-ገመዶች እንዳይጠላለፉና ውበታቸውን ጠብቀው
በግድግዳዎች ላይ እንዲሄዱ የሚያስችሉንን ትክክለኛ መጠን
ያለቸውን የገመድ ክሊፖች መያዝ፡፡
የገመዶችን ርዝመት ለመለካትና ከዚያም በላይ ለተጨማሪ
የሚለኩ ነገሮች የሚያገለግል ሜትር፡፡
- የሳህኑን አናትና እግር ካሰርንና እንዳይነቃነቅ ካጠባበቅን
በኋላ በትንሽ መነካካት ኳሊቲያቸው ሊወርዱና ሊወጡ የሚችሉ
ሳህኖች በንፋስ ሀይል በቅርቡ ሙሉ በሙሉ ኳሊቲያቸው
ሊወርድ ስለሚችል ይህንን እንዲቋቋምልን የሚያስችለንን ሽቦ
ከተመታው የቆርቆሮ ሚስማር ጋር መወጠር፡፡ እንደዚህ አይነት
አጋጣሚዎች ሊበዙ ስለሚችሉ የተጠቀለለ ሽቦ መያዝ፡፡
-ከላይ የተጠቀሱትን መሳሪያዎችና አንዳንድ ከቦታ ቦታ
ስንንቀሳቀስ የሚያስፈልጉንን የግል ንብረቶቻችን መያዣ የሚሆን
የጀርባ ሻንጣ ሊኖረን ይገባል፡፡ ከዚህ የጀርባ ሻንጣ አንድ
በአንድ የምናወጣቸውን የተለያዩ መሳሪያዎች ስራችንን
ከጨረስን በኋላ መልሰን ማስገባታችንን ሁሌም ቢሆን
ማረጋገጥ ይኖርብናል፡፡
-ለማስተካከል ወይም አዲስ ለመትከል እየተዘጋጀንለት ያለናቸው
ሪሲቨሮች አጠቃቀማቸውን በራሳችን ፍለጋ ማግኘት ወይም
አሰራሩ የተዋሀደው የዲሽ አሰሪ አካል ትብብር መጠየቅ (ብዙ
ጊዜ እጅግ ያረጁና አጠቃቀማቸው ግራ የሚያጋባ ሪሲቨሮች
ይገጥሙናል በዚህ ጊዜ ማድረግ የሚገባን አንድ ነገር ቢኖር
መጀመሪያ ራሳችንን ማረጋጋት ሲሆን ሲቀጥል እንደየ
እድሜያቸውና እንደኛ አቅም፣እና እንደየ ፋብሪካ ስሪታቸው
የሪሲቨሮቹን አሰራር መረዳት ሲሆን ብዙዎቹ ቆየት ያሉ ሪሲቨሮች
በመጠኑ አዳጋችና ለመረዳት ሰፋ ያለ ጊዜን የሚወስድ
ሶፍትዌር የተጫነባቸው ናቸው ይሁንና ያለንን መጠነኛ
የእንግሊዝኛ አቅም በመጠቀም እኚህን ሶፍትዌሮች በቀላሉ ከ
5 ደቂቃ ባለነሰ መልኩ ከራሳችን ጋር ማዋሀድ እንችላለን፡፡)
ይህንንም ድርጊት ማከናወን የአሰራር ፍጥነታችንን እጅግ
የሚያዳብረው ይሆናል፡፡
-በተለያዩ ምክኒያት የሚፈጠሩ የምስል ጥራት መጓደል፣ የኳሊቲ
ማነስና ሎሎች ተዛማች ችግሮችን በፍጥነት ለመለየት
የሚያስችል ከተለያዩ ምንጮች የተገኘ እውቀትና ራስን ሙሉ
በሙሉ ከዘመኑ ጋር እኩል ለማድረግ የሚያስችል ተጨባጭ
ክህሎት ለማዳበር ራስን በተለያየ መልኩ ማብቃት፡፡
-የዲሽ ስራ በባህሪው ከቦታ ቦታ መዘዋወርን የሚጠይቅ ስለሆነ
ሁሉም ቦታዎች ላይ ደግሞ በሚኒባስ፣ በባጃጅ ወይም በጋሪ
መድረስ ስለማይቻል የራሳችን የሆነ ከቦታ ቦታ ለመንቀሳቀሻነት
የምንጠቀምበት ሞተር ሳይክል ቢኖረን ጥሩ ነው፡፡ አቅማችን
ሞተር ለመግዛት የማይፈቅድ ከሆነ ደግሞ በኤሌክትሪክ
የሚሰራ ቻርጅ ከተደረገ በኋላ ብዙ ኪሎሜትሮችን መጓዝ
የሚችል ካቴና በተመታ ቁጥር ተጨማሪ ሀይል የሚሰጥ
(Scooter) በመባል የሚታወቅ መንቀሳቀሻ በመግዛት መኪናና
ባጃጆች ሊገቡባቸው የማይችሉ ጉራንጉሮች ውስጥ ሁሉ
ሳይቀር የተቀላጠፈ ስራ መስራት ይቻላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም
ያሉበት ከተማ ዳገት የመይበዛበት ከሆነ ብስክሌት በመግዛት
የፈለጉበት ቦታ ድረስ በመሄድ ስራዎን ማከናወን ይችላሉ፡፡
ማንኛውም የዲሽ ባለሞያ ለስራ በሚንቀሳቀስባቸው ጊዜያት
ሊወስዳቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎችና የስነምግባር መመሪያዎች
-ከምንም ከማንም በላይ ለራሳችን ህይወት ከፍተኛ የሆነ
ጥንቃቄ ማድረግ፡፡ በመሰላል በምንወጣጣበት ወቅት ከሁሉም
አስቀድመን የመሰላሉ ማንኛውም አካል ለአደጋ የሚያጋልጥ
አለመሆኑን በተደጋጋሚ ማረጋገጥ፡፡ መሰላሉ የሚቆምበት ቦታ
የተደላደለ መሆኑን ማረጋገጥ፡፡ በምንወጣበትና በምንወርድበት
ጊዜ መሰላሉ ወደ ጎንና ወደ ኋላ እንዳይንሸራተት በሰው
ማስያዝ፡፡ የተበላሹ የሚነቃነቁ፣ በርጥበት የተጎዱና በምስጥ
የተበሉ መሰላሎች በሚኖሩበት ወቅት ከጎረቤት የተሻለና
አስተማማኝ መሰላል እንዲመጣልን የዲሽ አሰሪዎችን መልካም
ትብብር መጠየቅ፡፡ አስተማማኝ መሰላሎች በማይገኝበት ወቅት
እራስን አደጋ ውስጥ ከማስገባት በፊት ተለዋጭ ቀጠሮ
በመስጠት አስተማማኝ መሰላል ሲገኝ ስልክ እንዲደወልልን
ማድረግ፡፡ ብዙ የሆነ መውጣትና መውረድ ለአደጋ
እንዳያጋልጠን ነገሮችን አስቀድመን መሬት ላይ መጨረስ
ለምሳሌ የዲሹን እግር ከጣውላዎች ጋር መምታትና
የመሳሰሉት፡፡
-እንደሚታወቀው የአብዛኞቻችን የሀገራችን ቤቶች የተሰሩት
ከእንጨትና ከቆርቆሮ በመሆኑና የሚተከሉት የዲሽ ሳህኖችም
ምርጥ ኳሊቲ እንዲገባልን ሲባል ጣራ ላይ በመሆናቸው ጣራ
ላይ ከወጣን በኋላ አግዳሚ ማገር ላይ የተመቱትን የቆርቆሮ
ሚስማሮች እንደ አመላካች በመጠቀም በጥንቃቄ መራመድ
ይኖርብናል፡፡ ለሳህኑ እግር መቀመጫ ቦታ ስንመርጥም ሳህኑ
እንዳይንቀሳቀስ ለማጠናከር የምንጠቀምበትን ድንጋይ ወይም
ብሎኬት ጫና መቋቋም እንዲችል አግዳሚ ማገሩ ላይ መሆን
ይኖርበታል፡፡ ሌላው መውሰድ ያለብን ጥንቃቄ የቆርቆሮ
ጠርዞችን የተመለከተ ሲሆን በምንም አይነት መልኩ
እንዲቆርጡን መፍቀድ የለብንም፡፡ ቆየት ብለው የተሰሩና ያረጁ
ጣራዎች በብዛት በዝገት ስለሚጠቁ የእኛን ክብደት የመቋቋም
አቅማቸው እጅግ የተዳከመ ሊሆን ስለሚችል አስፈላጊውን
ጥንቃቄ መውሰድ ይገባናል፡፡ በስህተት ማገር ላይ ያልተመታ
ቆርቆሮ ላይ በምንረግጥበት ጊዜ የመሰርጎድና ከበድ ያለ
የሚንቋቋ ድምፅ ስለሚሰጠን ፈጠን ብለን እግራችንን ማገር
ላይ ወደ ተመታው ቆርቆሮ መመለስ ይኖርብናል፡፡ እንደ
ድንጋይ፣ብሎኬትና የመሳሰሉትን ከበድ ያሉ ነገሮችን ወደ ጣራ
ይዘን በምንወ
743 views18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 21:44:25 ዲሽ አተካከል ለፍፁም ጀማሪዎችና ለተካኑ የዲሽ ቴክኒሺያኖች
ሰላም ጤና ይስጥልኝ የፔጃችን ተከታዮች እንደምን አላችሁ
ኑሮ እንዴት ይዞአችኋል:: ሁሉ ሰላም ነው? ጥቂት ብንጠፋፋም
ግን የመጣነው መጥፋታችንን በፍፁም ሙሉ በሙሉ የሚክስ
አዲስና እርስዎን እጅግ በጣም የሚጠቅም ስለ ሳተላይት ዲሽ
አተካከልና መወሰድ ያለባቸው ጥንቃቄዎች ዙሪያ ዘርዘር ያለ
መረጃ ይዘን ነው፡፡ ይህ ዛሬ ይዘን የመጣነው መረጃ በተለይ
ለፍፁም ጀማሪዎች ከራሳቸውና ከዲሽ ሰሪ አጋሮቻቸው ከተለያዩ
የመረጃ ምንጮች ከሚወስዷቸው ትምህርት ተጨማሪ የተወሰነ
ግን መሠረታዊ የሆነ ጠቀም ያለ መረጃ ነው ፡፡ ብዙ ሰላምታና
ማብራሪያ ሳነበዛ ወደሚያጓጓው ትምህርታዊ ፅሁፋችን
እናምራ፡፡
ዲሽ ለመጀመሪያ ጊዜ ለመትከልና ለመግጠም የተሰማሩ የዲሽ
ባለቤት ግለሰቦች ፡ ጀማሪ ወይም ልምድ ያላቸው ቴክኒሺያኖች
መያዝ የሚገባቸው የሳተላይት ዲሽ መግጠሚያ መሳሪያዎችና
አጠቃቀማቸው፡-
- ማንኛውም የሳተላይት ዲሽ ቴክኒሺያን በቅድሚያ
የሚገጥመውን የሳተላይት ዲሽ አይነትና አቅጣጫ በአትኩሮትና
በበቂ ሁኔታ ከምንም በላይ መገንዘብ ይኖርበታል፡፡
- በአብዛኛው በሃገራችን የሚገጠሙና ስርጭታቸው በሰፊ
ከሚገኙ የሳተላይት ዲሽ ቻናሎች ለመጥቀስ ያህል በየቤታችን
የሚገኘውና እጅግ ብዙ ተጠቃሚዎች ያሉት የናይልሳትና ከ 5
እና 6 አመታት በፊት ሁሉም የሀገራችን ብሎም ተወዳጅ የውጭ
ቻናሎች ይገኙበት የነበረው አሁን በአረቡ አለም ዘንድ ብቻ
በስፋት በጥቅም ላይ የሚውለው የአረብሳት ቻናል እና ነፃ የኳስ
ቻናሎች ማለትም ቨርዛሽ ቲቪ፣ ቶሎዶ ቲቪ እና ሌሎችን
የእንግሊዝና ስፔን ላሊጋ ብሎም፣ የቻምፒዮንስ ሊግ
ጨዋታዎችን የሚያስተላልፉ ቻናሎች የሚገኙባቸው የያህሳት
ቻናል ዲኤስቲቪ እና የ ፓወር ቪዩ ቻናሎች የሚገኙ ሲኖን እንደ
አንድ የሳተላይት ዲሽ ጀማሪም ሆነ የተካነ ቴክኒሺያን ማወቅ
ከሚገቡን ነገሮች መካከል የእያንዳንዱን ቻናል አቅጣጫና
አቀማመጥ ነው፡፡ እነዚህን ቻናሎች በአግባቡ ለመትከል
እንዲረዳን የአቅጣጫ ጠቋሚ ማለትም ኮምፓስ መጠቀም
በብዛት የሳተላይት ዲሾችን ለመግጠም ጥቅሙ እጅግ ከፍ ባለ
ደረጃ የሚረዳን ሲሆን አጠቃቀሙን በቀጣይ ፅሁፋችን ከፍተኛ
አትኩሮት ወደምንሰጥበት መሰረታዊ ፅንሠ ሃሳቦች ጋር ይዘን
በሰፊው እንመለስባቸዋለን፡፡
- ማንኛውም የሳተላይት ዲሽ ለመትከል የተዘጋጀ ጀማሪም ሆና
የተካነ ባለሙያ መያዝ ያለባቸው እጅግ መሰረታዊና የምንጊዜም
አጋዠ መሳሪያዎች መካከል የሚከተሉትን መዘርዘር ይቻላል፡፡
በተለምዶ አስር ቁጥር ብለን የመንጠራው የብሎን መፍቻ ለባለ
60 ሴንቲሜትር ሳህንና (ለ 90 ሲንቲሜትርና ከዛ ክፍ ለሚሉ
የዲሽ ሳህኖች፣ 10 ቁጥርን ጨምሮ እንደአስፈላጊነቱ
10፣11፣12፣ እና ከዚያ በላይ ያሉት መፍቻዎች በተናጠል
ወይም (በህብረት) ማለትም በአንድ የብረት ዘንግ ሶስቱንም
በስሩ የያዘ መፍቻ ወይም ከአነስተኝ እስከ ከፍተኛ የብሎን አናት
ቁጥሮችን በማጥበቅና በማላላት የምንጠቀምበት በተለምዶ
ካበ እንግሊዝ (Wrench) ብለን የምንጠራውን ባለ አንድ ወጥ
በጣት በማሽከርከር እንደ ብሎኑ አናት መጠን የሚጠብና
የሚሰፋ መፍቻ በቅርብ ከሚገኝ የህንጻ መሳሪያ መደብር
መግዛትና ሁሌም ዲሽ ለመትከልም ሆነ ለማስተካለል
በምንቀሳቀስበት ጊዜና ቦታ መያዝ፡፡
የሚቻልና አቅማችን ከፈቀደ (በተለይ ዲሽ መትከልን እንደ ዘላቂ
ሙያ ለያዡ) ሙሉ በሙሉ ዲጂታል የሆነ የሳተላይት ማሰሻ
ወይም Finder በመግዛት ለአስፈላጊው ስራ መዘጋጀት፡፡ አቅም
የማይፈቅድ ከሆነም ቆየት ያለውን ነገር ግን ላዩ ላይ ዲጅታል
ፋይንደር የሚል ፅሁፍ ያለውንና ከ 0 እስከ 10.5 ዲ.ቢ
የሚለካውን ባለ ሜትሩን የሳተላይት ዲሽ ማሰሻ ከ 400 ብር
ባልበለጠ ገንዘብ በአካባቢያችን በሚገኙ የኤሌክትሮኒክስ
እቃዎች መሸጫ መደብሮች መግዛትና መያዝ፡፡ ለስራችን
ቅልጥፍና የሚረዳን የመጀመሪያው አይነት ዲጅታል ፋይንደር
ሲሆን የራሱ የሆነ የባትሪ ሀይል ስላለው መብራት እንኳን
ቢጠፋ ጣራ ላይ ባለንበት ስራችንን ለመጨረስ ያስችለናል
በተጨማሪም የፋይንደሩ ሰሌዳ ላይ ልክ ሪሲቨሩ ላይ
እንደምናየው ሲግናልና ኳሊቲ ማንበቢያ ስላለውና
የምንፈልጋቸውን የቻናል ፍሪኩዌንሲዎች ሞልቶ ስለሚይዝልን
ስራችንን እጅግ ፈጣን ያደርግልናል፡፡ እጅግ በጣም
የሚያስፈልገን ከሆነ ደግሞ በአንገት የሚንጠለጠል
የምናስሰውን ቻናል በፋይንደሩ ሰሌዳ ላይ ልክ እንደ ቴሌቪዥን
ምስሉን በጥራት የሚያሳይ ድምፁንም በጥራት የሚያሰማ
ሲግናልና ኳሊቲ ማንበቢያ ያለው እጅግ ዘመናዊ የሆነ ፋይንደር
ገዝተን ስራችንን በጣም በዘመናዊ መልኩ ማካሄድ እንችላለን፡፡
-ከ ፋደራችን አይነትና አቅም ጋር የሚሄድ ተወርዋሪ ገመድ
ከዲሹ ጋር ከሚመጣው RG-6 Coaxial Cable (የዲሽ
ገመድ) ወይም ከቴሌቪዥን የውጭ አንቴና ጋር ከሚመጡ
በውስጣቸው ቀጭን የኮፐር ወይም መዳብ ዘንግ ከያዙ
ገመዶች ቆርጦ ርዝመቱ ከ 60 ሳንቲሜትር ያላነሰ ተወርዋሪ
ገመድ (Jump Caple) በሁለቱም በኩል የሴቴ ወይም
(Female Connector) የያዘ ገመድ ማዘጋጀት፡፡ የገመዱ
ጫፍ አንደኛው ወደ የዲሹ ጭንቅላት (LNB) ላይ የሚታሰር
ሲሆን ሌሌኛው ጫፍ ፋይንደሩ ላይ (To LNB) በሚለው
አቅጣጫ የሚታሰር ይሆናል፡፡ የፋይንደርን አጠቃቀም ወደ ፊት
ሰፋ ያለ ትንታኔ የምንሰጥበት ስለሆነ ለዛሬው እዚህ ላይ
እንግታው፡፡
-ተወርዋሪ ገመድ ወይም ከዲሹ ጋር አብሮ የሚመጣውን
ገመድ ጫፎች ለመላጥ፣ Female Connector ችን
ለማያያዝ፣ ገመዶችን ለማሳጠር ወይም ለመቀጠልና
ለማስረዘም እንዲረዳን አንድ ጥሩ የሆነ ፒንሳ ያስፈልገናል፡፡
በአቅራቢያችን ማግኘት የምንችል ከሆነ ደግሞ ኬብል ስትሪፐር
ወይም ኬብል ከተር መግዛት ስራችንን ቀልጣፋ ያደርግልናል፡፡
-የዲሹን LNB ማቀፊያ ለማጥበቅና ለማላላት ብሎም LNB
ለመቀየርና አዳፕተሮችን ለመፈታታትና ለማጥበቅ ሊረዳን
የሚችል በሁለቱም በኩል ሲቀያያር ጠፍጣፋና ባለ መስቀል
አናት የሚሰጥ ካቻቢቴ መያዝ ይጠበቅብናል፡፡
-የዲሹን ሳህን እግር በሁለት አቅጣጫ ረዘም ካሉ ጣውላዎች
ጋር መምቻና የዲሹን ገመዶች በየግድግዳው በኬብል ክሊፕ
ለማያያዝና ሌሎች ጠንከር ያለ ሀይል የሚጠይቁ ስራዎችን
ለማከናወን የሚጠቅመንን አጠርያለ የፕላስቲክ እጀታ ያለው
መዶሻ ያስፈልገናል፡፡
ከላይ የጠቀስናቸው መሳሪያዎች እጅግ መሰረታዊና አስፈላጊ
ሲሆኑ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ደግሞ አስፈላጊነታቸው በጣም
ብዙም ባይሆን እንኳን መያዛችን ግን ጥቅሙ እጅግ ያመዘነ
ይሆናል፡፡
-በማንኛውም ሁኔታ ቢሆን ሊጠቅሙን ስለሚችሉ በርከት ያሉ የ
Female connector, Audio Video Splittor Conector
ንና ከሁለት ያላነሱ Disqe Switch መያዝ፡፡
-እንደየ ፍላጎታችን የምንሞላውን ሳተላይት መሠረት ያደረጉ
የተለያዩ ፊሪክዌንሲዎችና፣ ፖላራይዜሽሮች ዝርዝር በጥንቃቄ
ለማወቅ ይረዳን ዘንድ እና አዳዲስ መረጃዎችን በማይረሱ
መልኩ ለመፃፍና በአስፈላጊ ጊዜ ዋቢ ለማድረግ ለመፃፊያነት
የሚረዱን መጠናቸው እንደየ ግል ፍላጎታችን በሚወሰኑ
ማስታወሻ ደብተሮች ላይ ማስፈር፡፡ ለዚህም ይረዳን ዘንድ
ለአያያዝ አመቺ የሆኑ ማስታወሻ ደብተሮችን በአቅራቢያችን
ከሚገኙ የፅህፈት መሳሪያ መደብሮች ገዝቶ መያዝ፡፡
-የስራው ባህሪ ሆኖ ብዙዎች ተገልጋዮችን የምናገኛቸው
በተንቀሳቃሽ ሞባይል ስልኮች ከመሆኑ የተነሳ የኔትወርክ
ግኑኝነት በማይኖረበት ቦታ የኔትወርክ ግኑኝነትን አስሰውና
ፈልገው የሚያመጡልንን ዘመኑ ኖርማል ሀንድሴት ብሎ
የሚጠራቸውን ግን በባትሪ ቆይታቸውና
1.1K views18:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 21:39:56 ይህ የ #AGARO_DISH_AND_TECH_INFO የቴሌግራም ቻናል ነው።
ይህ ቻናል ስለ ዲሽ መረጃ፣ ስለ ሳተላይት ዲሽ አሰራር መረጃ፣ ወቅታዊ ሳተላይት ዲሽ ነክ ዜናዎች፣ በተለያዩ ሳተላይቶች የሚገኙ ቻናሎች ዝርዝር፣ የሪሲቨሮች ሶፍትዌርና ሌሎች ቴክኖሎጂ ነክ ወቅታዊ መረጃዎች የሚገኝበት ቻናል ነው።
1.2K viewsedited  18:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 10:59:05 ቅዳሜ 11:00 ሰዓት ላይ Chelsea ከ Leicester የሚረጉት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ከታች በተጠቀሱት ነፃ ቻነሎች ይተላለፋሉ።

Chelsea Leicester
              11:00 ቅን

ZBC TV HD
Eutelsat 7°E | 11356H35000


YTV BOTSWANA
Intelsat 68.5°E | 12543V1600

CRTV SPORTS HD
Eutelsat 8°W | 3832H7579


SPORT 1
Amos 4°W | 11475V27500

@agarodishinfo
307 views07:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 10:28:11 Gshare plus,Super Ghare Plus, Funcam መግዛት ለምትፈልጉ
Gshare የ 6 ወር>> 300 birr
Super Bolt Iks የ6 ወር>> 300birr
Gshare የ1ዓመት 600Birr
Super Bolt Iks የ1 ዓመት 600Birr
Funcam & Apollo 1 አመት> 650birr
Funcam ብቻ የ1 ዓመት>>> 600birr

ንግድ ባንክ
User Name:JUNEDIN MOHAMMEDNUR
Acc. No. 1000372973599
ባሉበት ቦታ ሆነዎ በባንክ ብር በማስገባት ደረሰኙን ፎቶ በማንሳት/Screenshot/ በማድረግ
በ @Ju_admin
ወይም @John_dish ይላኩልን
ወዲያውኑ የአሞስ መክፈቻ ኮድ እንልክልዎታለን

SERVER ከእኔ ገዝታችሁ ሬሲቨሩ ቢበላሽ ወይም Restore ቢደረግ የገዛችሁትን ኮድ ድጋሚ ከእኔ ማግኘት ትችላላችሁ!!

አምናችሁ ስለምትልኩልን እናመሰግናለን
ማንኛውንም ጥያቄ መጠየቅ ስትፈልጉ
ከታች ያለውን ሊንክ መጠቀም ትችላላችሁ።
@John_dish ያናግሩን
+251938095912
306 viewsedited  07:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ