Get Mystery Box with random crypto!

AfandishaHarar 🇪🇷🇪🇹🇯🇴🇸🇩🇪🇭🇸🇴

የቴሌግራም ቻናል አርማ afandishaharar — AfandishaHarar 🇪🇷🇪🇹🇯🇴🇸🇩🇪🇭🇸🇴 A
የቴሌግራም ቻናል አርማ afandishaharar — AfandishaHarar 🇪🇷🇪🇹🇯🇴🇸🇩🇪🇭🇸🇴
የሰርጥ አድራሻ: @afandishaharar
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.31K
የሰርጥ መግለጫ

Spreading Ethnographic and Historical Truth.

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-07-12 03:15:37 I am watching "The Italian Job" (2003)
----
Old is gold. This is one of the best heist action movies ever produced in Hollywood.

Mat Demon
Jason Statham
Carliez Theron
Edward Norton
And others..
2.3K views00:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 19:32:28 Dh. D. U. O
----
OPDOn gaafa dura Galamso qabatte san akkana jettee sirbitee turte.

Dh.D.U. O. abbaa haqaa abbaa seenaa Oromoo (2)
Bilisummaa siin argannee kan gammanne ammoo (2)
-----
Nuti joolleen magaalaa guyyaa itti aanu walitti qabamnee walaloo san akkana jennee jalaa jijjiirre.

Dh.D.U.O. abbaa harree, abbaa gangeef saree (2)
Bilisummaa at baantu takkaa hin agarre (2)
2.4K views16:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 07:04:49
Hilary Clinton in Asmara
March 1997
------
Photo credit Mare Erythraeum
2.6K views04:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 22:55:24 የተረሱ የኦሮሞ ጀግኖች
-----
OMN በአንድ ሰሞን ምንነታቸው በማይታወቅ ጊዜ አመጣሽ አክቲቪስት ተብዬዎች ተጨናንቆ ነበር። ገረሱ ቱፋ፣ ብርሀኑ ሌንጂሶ፣ አየለ ደጋጋ፣ ነጌሳ ኦዶ ዱቤ፣ አሕመድ ጊሼ፣ ሳሊሃ ሳሚ፣ ጂንኒ ጀቡቲ፣..
እነዚህ ያልበሰሉ ጥሬዎች አሁን በገንዘብ ሰክረው ሌላ ካምፕ ውስጥ ነው ያሉት።
-----
ሚዲያው ለእነዚህ ቆሎ-ጆሌ ነጋዴዎች መድረክ ሰጥቶ እንዲበጠብጡን ከሚያደርግ በኦሮሞ ታሪክ ወደር የሌለው አኩሪ ስራ የሰሩትን ገዲም ጀግኖች ለወጣቱ ትውልድ ቢያስተዋውቅልንና የህይወት ተሞክሮአቸውን እንዲያጋሩልን ቢጋብዛቸው በጣም አሪፍ ነበር። ለምሳሌ ወልደ-ስላሴ ወልዲያ፣ ዶክተር ሞጋ ፍሪሳ፣ በቀለ ነዲ፣ ጀይሉ አቡበከር፣ አብዱልፈታህ ሙሳ (ቡልቱም ቢዮ)፣ ዘገዬ አስፋው፣ አብዩ ገለታ፣ መኮንን ገላን፣ ዱጎምሳ ዱጋሳ፣ አደም ከቢራ ወዘተ.. .

በውጪ ያሉትን ውጪ አነጋግሯቸው። ሀገር ቤት ያሉትን ደግሞ መላ ፈጥራችሁ ብታነጋግሯቸው መልካም ነው።
2.6K views19:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 22:25:44 የየመኒዎች ጨዋታ
----
አፈንዲ ሙተቂ
----
በዚህ ወቅት የቅርብ ጓደኛዬ የመኒው ሜጀር ጄኔራል ሙሐመድ አል ሐይደሪ ነው። በየቀኑ እንገናኛለን። በተለይም ከሰዓት አብረን ስንጫወት ነው የምናሳልፈው። በርካታ ቁም ነገሮችንም ከእርሱ እየተማርኩ ነው።
----
ጦርነትን ሸሽቶ ከሀገሩ የወጣው ሙሐመድ አል ሐይደሪ ወደዚህች ከተማ የመጣው ባለቤቱ የገለምሶ ተወላጅ ስለሆነች ነው። የእርሷ አባት በልጅነታችን ቢስኪሌት እንከራየው የነበረው ጋሽ ፉአድ ናስር ነው።

እንደሚታወቀው በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ የመኒዎች በሀገራችን ይኖሩ ነበር። ታዲያ እነዚያ የመኒዎች በንግድ ከባድ የመሆናቸውን ያህል በጨዋታ አደገኛ ናቸው። እስቲ አንዳንድ ታዋቂ ጨዋታዎቻቸውን እናስታውሳችሁ።
----
በ1967 በተካሄደው የዐረብ እስራኤል ጦርነት ወቅት ዐረቦች በደረሰባቸው ሽንፈት ተከፍተዋል። በኢትዮጵያ የሚኖሩ የመኒዎችም በጣም ተበሳጭተው ነበር። እናም የተለያዩ የሀገራችን ዜጎች ወደ የመኒዎች መደብር እየሄዱ ይለክፏቸዋል።

ኢትዮጵያዊው: "አንተ ባለ ሱቅ፣ የእስራኤል ሸሚዝ አለ?"

የመኒው: "አባትና እናትህን ረግጦ የገዛው ጣሊያን ሸሚዝ አለ"

(ጣሊያን ኢትዮጵያን አልገዛችም። የመኒው ለለከፋው መልስ ለመስጠት ሲል ነው "ረግጦ የገዛው" የሚል የንዴት መልስ የሰጠው)።
-----
የመኒው ተከሰሰ። ፍርድ ቤት ቀረበ። ዳኛው ክሱን አነበቡለት።

ዳኛ: "መደብርህ ፅዳት የለውም፣ ሸረሪት ተገኝቶበታል"

የመኒው: "ያ ዳኛ! ይሄ ዓይነት ሸረሪት ነው ወይስ ሌላ ዓይነት ሸረሪት?
(በፍርድ ቤቱ ግድግዳ ላይም ሸረሪት ነበረበት! ሃሃሃሃሃ)።
----
ረፋድ ላይ ነው። ወቅተል ሐራራ ነበር። የመኒው ኢጀበና ስላላደረገ መናገር አስጠልቶታል። አንድ እቃ ገዥ ወደ መደብሩ ገባ።

"የፋኖስ ብርጭቆ ፈልጌ ነበር"
"የለኝም"
"ይሄው አለ እኮ"
"የለኝም አልኩህ"
"ኧረ እያየሁት? ለምን አትሸጥልኝም?"

የመኒው ተናደደ። እናም የፋኖሱን ብርጭቆ ካለበት አንስቶት ባፍጢሙ መሬት ላይ ወርወረውና ሰባበረው። ከዚያም ገዥውን እንዲህ ብሎት ጠየቀው።
"አሁንስ ብርጭቆው አለ?"

(ይህኛው በጣም ነበር የሚያስቀኝ። ክርስቲያኗ ፍቅረኛዬ ለምላት ልጅ በነገርኩበት እለት ሳቋን ማቆም አቅቷት ነበር)።
-----
በሀገራችን ነጋዴዎችና ከተሜዎች ዘንድ ተዘውታሪ የሆኑ የየመን አባባሎችን ልጨምርላችሁ!!

ሹፍ ኡመሃ ወዘዊጅ ቢንተሃ (እናቷን አይተህ ልጅቷን አግባ)
የውም ዐሰል፣ የውም በሰል (አንድ ቀን ማር፣ አንድ ቀን ሽንኩርት)
ኢዛ ከሠረ ጠባኽ ፈሰደል መረኽ (አብሳይ ሲበዛ ወጥ ይበላሻል)
ከማ ተዲኑ ቱዳን (አትፍረድ ይፈረድብሃል)
ሓሪብ ሚነል መውት ደኸለ ሐድረመውት (ሞትን ሽሽት ወደ ሞት ማዕከል ገባ)
ኢተቂ መረን ሚን ዐደዊከ፣ ወ አልፍ መራ ሚን ሰዲቂከ (ከጠላትህ አንድ ጊዜ ተጠንቀቅ፣ ከወዳጅህ ግን ሺህ ጊዜ ተጠንቀቅ)
አል ወቅት ሰይፉን፣ ኢንለም ቱቅጠዕ ቢህ የቅጠዐክ (ጊዜ ሰይፍ ነው፣ ካልቆረጥክበት ይቆርጥሃል)።
-----
ተማም
አፈንዲ ሙተቂ
ገለምሶ-ምዕራብ ሀረርጌ
June 11/2019
2.4K views19:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 23:57:52 በድጋሚ የወጣ ማስታወሻ
-----
ዒድ ሙባረክ! በኪት ዒድ ዐረፋ!

ያ የምታውቁት የፌስቡክ ፔጄ "hack ተደርጓል። ለዚህ ነው የተለያዩ ምስሎች የሚወጡበት። መፍትሔው ያንን ፔጅ ብሎክ ማድረግ እና አዲሱን ፔጄን follow ማድረግ ነው። አዲሱን ፔጄን በዚህ ሊንክ ያግኙት።

https://www.facebook.com/AfendiEthno2018

Peejiin Feesbookii kiyya kan duraanii hack tahee jira. Kanaaf jecha peejii san irratti waan fokkotaa maxxansaa jiran. Amma Peeji haarawa baneetin jira. Linkii asii olitti tuqame bantaanii peejii kiyya haarawa "follow" gochuu nidandeessan.
-----
Here is my new Facebook page. You may open the link and follow me there.

https://www.facebook.com/AfendiEthno2018
----
2.6K viewsedited  20:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 22:28:16 ለጃል መሮ (ኩምሳ ድሪባ)
-----
ርዕዮት ሚዲያ ከሩዋንዳው "ራዲዮ ሚሊ ፎሊ" ተለይቶ የማይታይ፣ በኦሮሞ ህዝብ ጥላቻ የሰከረ፣ የገዳ ስርዓትን "የዘር ፍጅት ማስፈጸሚያ አደረጃጀት" ብሎ የሚጠራ፣ የኦሮሞ ታጋዮች ዘመናት ያደረጉትንና ከፍተኛ መስዋእትነት የከፈሉበትን የመብት ትግል ኢትዮጵያን ለመበተን የተደረገ የስቅየት ጉዞ አስመስሎ፣ የሚተርክ እጅግ አስቀያሚና ወራዳ የሰፈር መሸተኞች አንደበት ነው። የWBO (OLA) ዋና አዛዥ የሚል ስልጣን ይዘህ በዚያ ተራ እና መደዴ ሚዲያ ላይ መቅረብህ ለኦሮሞ ህዝብ ትልቅ ስድብ ነው።

ከዚህ በፊት ወያኔ (TPLF) የሚባለው የቀድሞው ገዥ ቡድን የለየለት ማጅራት መቺ፣ ገዳይ፣ ዘራፊና ጨፍጫፊ መሆኑ እየታወቀ ከዚህ ቡድን ጋር "የትግል አንድነት ፈጥረናል" ብላችሁ ህዝቡን አሳዝናችሁት ነበር። አሁን ደግሞ ሌላ ጥፋት ደገማችሁ።

እኛ የምናውቀው WBO እንደዚህ አልነበረም። WBO ለኦሮሞ ህዝብ ክብር ከሌለው እና የኦሮሞዎችን ትግል ለማሰናከል ሲጥር ከነበረ ማንኛውም አካል ጋር ትብብር አይመሰረትም። ኦሮሞን ለሚሰድብ ሚዲያም sympathy አያሳይም።
------
ርዕዮት ሚዲያ "አብይ ጠላቴ ነው" ከሚል ፍረጃ ተነስቶ ነው የኦሮሞ ህዝብን ሲዘልፍና ሲሰድብ የሚውለው። እናንተም የአብይን መንግሥት በጠላትነት ነው የምታዩት። በመሆኑም "የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው" በሚለው አነጋገር ተመርታችሁ በዚያ በሚዲያ ድምጻችሁን ያሰማችሁ ይመስለኛል። ታዲያ ይህ አባባል በስርዓቱ ካልተያዘ የሚያደርሰው ኪሳራ ብዙ ነው። የኦሮሞ ህዝብን በጅምላ እንደ ጨፍጫፊ፣ ገዳይ እና አረመኔ የሚፈርጅ ሚዲያ ለጥፋቱ በይፋ ይቅርታ ጠይቆ ራሱን እስካላስተካከለ ድረስ "የአብይን መንግሥት ይጠላል" ተብሎ እንደ ታክቲካል ወዳጅ መታየት የለበትም።

ይህ ሚዲያ እና ቴዎድሮስ ጸጋዬ የሚባለው "አጤረርቱ" ጋዜጠኛ ድራሻቸው ይጥፋ አቦ!!
2.7K views19:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 08:18:23 አዝናለሁ።
----
ዝናቡ ሌሊቱን አደረበት። አሁንም ድረስ እየዘነበ ነው። ደግሞም ከበድ ያለ ዝናብ ነው። የዒድ አደባባያችን ቀይ መረሬ አፈር በመሆኑ ለመስገድ ያስቸግራል።

እርሱስ ይሁን። አላህ ዝናቡን በቁድራው ያስቁመው እንጂ አስፋልቱ ላይ መስገድ እንችላለን። ወይንም ወደ መስጂዶች እንሄዳለን።
-----
ዒድ ሙባረክ።
2.8K views05:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 03:22:49 كل عام و حياتكم مملوءة بالسعادة اهنئكم بحلول عيد الاضحى أعاده الله علينا و عليكم بالخير والبركات
2.7K views00:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ