Get Mystery Box with random crypto!

AfandishaHarar 🇪🇷🇪🇹🇯🇴🇸🇩🇪🇭🇸🇴

የቴሌግራም ቻናል አርማ afandishaharar — AfandishaHarar 🇪🇷🇪🇹🇯🇴🇸🇩🇪🇭🇸🇴 A
የቴሌግራም ቻናል አርማ afandishaharar — AfandishaHarar 🇪🇷🇪🇹🇯🇴🇸🇩🇪🇭🇸🇴
የሰርጥ አድራሻ: @afandishaharar
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.31K
የሰርጥ መግለጫ

Spreading Ethnographic and Historical Truth.

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-07-15 05:21:14 ለኢትዮጵያ መንግሥት፣ ለአማራ ክልላዊ መንግሥት እና ለትግራይ ክልላዊ መንግሥት
------
አምና በዚህ ቀን የተጻፈ (July 15/2021)
------
ችግራችሁ የመሬት ውዝግብ እና የይገባኛል ጥያቄ ከሆነ ጦርነቱን አቁሙና ውዝግቡን በሰላማዊ መንገድ ፍቱ። ውጊያ ይቁም! ወንድማማቾች አይጨራረሱ! ንብረት አይውደም! መንገድና መሠረተ ልማት አይፍረስ! ህዝብ አይፈናቀል!
------
ህወሓት "ከትግራይ ህዝብ 80% የሚሆነው እየተራበ ነው" ሲል እንደነበረ እናስታውሳለን። የኢትዮጵያ መንግሥት ደግሞ "ከትግራይ የወጣሁት ለረሀብተኛው የነፍስ አድን እርዳታ እንዲደርስ እና ገበሬዎች እርሻቸውን እንዲያርሱ ነው" የሚል ምክንያት ሰጥቶ ነበር። ታዲያ ለምንድነው ጦርነት አቁማችሁ ህዝቡ በረሃብ እንዳይሞት ጥረት የማታደርጉት? ሌላ ዙር እልቂት ቢመጣ ተጠቃሚው ማን ነው?
------
ጦርነት፣ ረሀብ፣ እልቂት፣ ግጭት፣ ውድመት፣ ጥፋት፣ ሞት፣ ሞት!
893 views02:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 23:21:43
Magfira Harun (Magi Harun) in 1980s..
-------
This was one of the most iconic posters printed by the Ethiopian Tourism Commission to promote Tourism and art in Ethiopia.
1.1K views20:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 20:31:12 ፓውሎ ሮሲን በጨረፍታ
----
(አፈንዲ ሙተቂ)
----
በዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ በተናጥል ከሚሰጡት ሽልማቶች መካከል ከፍተኛ ክብር የሚሰጣቸው "የወርቅ ኳስ" እና "የወርቅ ጫማ" የሚባሉት ናቸው። እነዚህን ሽልማቶች በአንድ ላይ ለማሸነፍ የቻሉት አራት ተጫዋቾች ብቻ ናቸው። የመጀመሪያው የብራዚሉ ጋሪንቻ (1962) ነው። ሁለተኛው የአርጀንቲናው ማሪዮ ኬምፐስ (1978) ነው። ሶስተኛው ሰው ሳልቫቶሬ ሺላቺ ይባላል። ሺላቺ የ1990 ዓለም ዋንጫ ጀግና ነው። አራተኛው ደግሞ አምና ያረፈው አንድ ግሩም ተጫዋች ነው። ይህ ሰው በዓለም እግር ኳስ አፍቃሪዎች ዘንድ በጣም የታወቀው በ1982 በስፔን በተካሄደው የዓለም ዋንጫ ነው።

ያ የዓለም ዋንጫ እጅግ ውብ የሆኑ የእግር ኳስ ጥበበኞች የተካፈሉበት ነበር። የጣሊያኑ ዲኖ ዞፍ፣ የብራዚል ውድ ልጆች የነበሩት ዚኮ፣ ፋልካኦ፣ ሶቅራጥስና ኤደር፣ የፈረንሳዮቹ ሚሼል ፕላቲኒ እና ጃን ቲጋና፣ የአርጀንቲናው ማራዶና፣ የጀርመኑ ካርልሄንዝ ሩሚኒጌ እና ሌሎችም በውድድሩ ተካፍለው በጣም ያማረ football ለዓለም ህዝብ አሳይተዋል።

በዚያ የዓለም ዋንጫ ከፍተኛ ግምት የተሰጠው ኳስን እንደ ዳንስ ይራቀቅበት ለነበረው የዘመኑ የብራዚል ብሄራዊ ቡድን ነበር። እንደዚያ ዓይነት ጥበበኛ ቡድን በዓለም ዋንጫ ታሪክ እንዳልታየ የስፖርቱ ኤክስፐርቶች ይናገራሉ። ይሁንና ያ ብርቅዬ ቡድን ከሩብ ፍጻሜ ወዲያ ሊጓዝ አልቻለም። ጉዞአቸውን የገታው ደግሞ በፎቶው ላይ የምትመለከቱት የእግር ኳስ ጥበበኛ ለእናት ሀገሩ ያደረገው ተጋድሎ ነው (ሶቅጥራስ በዚያ ውድድር ብራዚል ዋንጫውን ባለማግኝቷ ስሜቱ ስለተነካ ከእግር ኳስ ተገልሎ ነበር)።
----
ይህ ባለ ከባድ ሚዛን የእግር ኳስ ሊቅ ፓውሎ ሮሲ ይባላል። ኢጣሊያ ካፈራቻቸው ምርጥ እግር ኳስ ተጫዋቾች መካከል የእርሱንና የሮቤርቶ ባጂዮን ያህል የገነነ የለም። ሮሲ በተለያዩ የኢጣሊያ ክለቦች ተጫውቶ ባለ ብዙ ሽልማት ለመሆን የቻለ ጀግና ነበር። የዓለም ህዝብም ሆነ የኢትዮጵያ እግር ኳስ አፍቃሪዎች እርሱን በደንብ የሚያስታውሱት ግን በስፔኑ የዓለም ዋንጫ ላይ ባሳየው ድንቅ ብቃቱ ነው።

ፓውሎ ሮሲ በዚያ የዓለም ዋንጫ ቡድኑን በመምራት ለድል አብቅቶታል። ለራሱ ደግሞ ኮከብ ተጫዋች እና ኮከብ ግብ አግቢ ሆኖ በተናጥል የሚሰጡትን ታላላቅ ሽልማቶች (የወርቅ ኳስ እና የወርቅ ጫማ) ወስዷል። ውዱ ተጫዋች ፓውሎ ሮሲ አምና ታሕሳስ 1/2013 በ64 ዓመቱ አርፏል።
--------
አፈንዲ ሙተቂ፣ ታሕሳስ 1/2013

Afendi Muteki, December 9/2020
------
የቴሌግራም ቻናሌ የሚከተለው ነው።

You may join my telegram channel here.

https://t.me/afandishaHarar
1.5K viewsedited  17:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 11:07:40
አባይ እና ጣና- በጀምስ ብሩስ ካርታ ላይ
-----
(አፈንዲ ሙተቂ)
-----
ጀምስ ብሩስ ይህንን ካርታ ያነሳው በ1770ዎቹ ነው፡፡ ፈረንጆች እርሱ የጻፈውን መጽሐፍ አንብበው “ጀምስ ብሩስ የጥቁር አባይን ምንጭ አገኘ” ይላሉ፡፡ ጳውሎስ ኞኞ በዚህ ዙሪያ ሲጽፍ “አረ ለመሆኑ ዕድሜ ልኩን ከአባይ ጋር ሲኖር የነበረው የጎንደርና የጎጃም ገበሬ የት ሄዶ ነው ፈረንጆች እንዲህ የሚሉት?” በማለት ሞግቶ ነበር፡፡

በርግጥም “ምንጩን ጀምስ ብሩስ አገኘው” ማለት ትልቅ ምጸት ነው፡፡ ባይሆን “ጀምስ ብሩስ የጥቁር አባይን መነሻ በዐይኑ አይቶ በእንግሊዝኛ ቋንቋ በመጻፍ የመጀመሪያው አውሮጳዊ ነው” ቢባል ይሻላል፡፡ እዚህ ላይ በእንግሊዝኛ ያልኩት ሊሰመበርት ይገባል፡፡ ከጀምስ ብሩስም ሆነ ከሌሎች የውጪ ተወላጆች በፊት ስለአባይ በግዕዝ ቋንቋ የጻፉት የኛው ሀገር ተወላጆች ናቸው፡፡ በማስከተልም በዐረብኛ ቋንቋ ስለአባይ መነሻ ተጽፏል፡፡

ከአውሮጳዊያን መካከል የአባይን መነሻ በዐይኑ አይቶ ትክክለኛ ዘገባ ያቀረቡት የመጀመሪያው ሰው ደግሞ ፖርቱጋላዊው ቄስ ጄሮኒሞ ሎቦ ናቸው፡፡ እኝህ ሰው በአጼ ሱስንዮስ ዘመን ወደ ኢትዮጵያ የመጡት “ኢየሱሳዊያን” (Jesuits) የሚባሉት ሚሲዮኖች አባል ነበሩ፡፡ ቄስ ሎቦ በኢትዮጵያ ለዘጠኝ ዓመታት ኖረዋል፡፡ “ኢየሱሳዊያን” ከኢትዮጵያ ከተባረሩ በኋላ ወደ ሀገራቸው በመሄድ በኢትዮጵያ ስላሳለፉት ኑሮ የሚተርክ Itinerário የሚል ርዕስ ያለው መጽሐፍ ጽፈዋል፡፡ በመጽሐፉ ከተጻፈው ነገር ከፊሉ ስህተት ቢሆንም ስለአባይ መነሻ የተጻፈው ግን መቶ በመቶ ትክክል እንደሆነ ተረጋግጧል፡፡
-----
አፈንዲ ሙተቂ
ሀምሌ 7/2009
አዳማ
1.7K views08:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 03:12:57 .አወይ ባቢሎን!
---
# የጥንቱ የአክሱም ነገስታት አስደናቂ ሃውልቶችን ሰሩ።

# የጥንቱ የኦሮሞ አባቶች ገዳን የመሰለ ውብ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ፈጠሩ።

# ቅዱስ ያሬድ በ6ኛው ክፍለ ዘመን አስደናቂ ዜማዎችን አፈለቀ።

# የጥንቱ የሀረላ ጎምቱዎች ከመሬት ውስጥ ተቆፍራ የተገኘችውን ከተማና መስጊዶቿን ሰሩ።

# የጥንቱ የዛግዌ ነገስታት ድንጋይ እየፈለፈሉ አስደናቂዎቹን አብያተ ክርስቲያን ሰሩ።

# የጥንቱ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ዛሬ ዓለም የሚደመምባቸውን የብራና መጻሕፍት ደረሱ።

# ዳዺ ጉዮ የሚባለው ጥንታዊ የቦረና ኦሮሞ ሊቅ አስደናቂ የሆነ የአስትሮኖሚ ጥበብ ፈጠረ።

# የጥንት የአፋር አዋቂዎች "ዳጉ" የሚባለውን ፈጣን የመረጃ መለዋወጫ ዘዴ ፈጠሩ።

# የጥንት የሶማሊ ወገኖቻችን በጣም አስደማሚ የማኅበራዊ መረዳጃ ዘዴ አስገኙ።

# የሀረሩ አሚር ኑር ሙጃሂድ በ16ኛው ክፍለ ዘመን የዓለም ቅርስ ለመሆን የበቃውን ጁገልን ገነባ።

# ዝነኛው አፄ ፋሲል ከአራት መቶ አመት በፊት ታዋቂውን የጎንደር ግንብ አሰራ።

# እነዚህ ህዝቦቻችን አንድ ሆነው አድዋ ላይ እጅግ ዘመናዊ መሳሪያ ታጥቆ የመጣውን ወራሪ ድል አድርገው መለሱ።
----
የዘመኑ ኢትዮጵያዊያን ግን እንኳንስ አዲስ ታሪክ ሊሰሩ፣ ምሳ በሳሕን ተዘጋጅቶ ሲቀርብላቸው "ኬኛ ነው"፣ "የኛ ነው" እየተባባሉ ይቧቀሳሉ።
አወይ ባቢሎን!!!
1.6K views00:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 23:25:27 (ከላይ ካለው ጽሑፍ የዘለቀ)

አቡ-ኒዳል በቀደመው ዘመኑ የሶሪያ መንግሥት ቀኝ እጅ ነበር። ከዚያ በኋላ የኢራቅ መንግሥት እንዳሻው የሚገለገልበት ተቀጣሪው ሆኗል። PLO የሚባለው ዋናው የፍልስጥኤማዊያን ድርጅት ለኢራቅ መንግሥት እንዳሻው አልታዘዝ በማለቱ ኢራቅ በእርሱ ምትክ አቡ-ኒዳልን ይዛዋለች። ኢራቅ በየዓመቱ ለፍልስጥኤም የምትመድበው ድጎማ፣ ለፍልስጥኤማዊያን ተማሪዎች የምትሰጠው ስኮላርሺፕ እና ፍልስጥኤማዊያን የሚገለገሉበት ራዲዮ ጣቢያ ለአቡ-ኒዳል ድርጅት ተሰጥተዋል። ሳያስበው በድንገት ከበርቴ የሆነው አቡ-ኒዳልም የኢራቅ መንግሥትን የሚተቹ የውጪ ዲፕሎማቶችን፣ ምሁራንን፣ ጋዜጠኞችንና የፍልስጥኤም ታጋዮችን ድራሻቸውን ያጠፋ ነበር። ከነዚህ ግድያዎች መካከል የያሲር አረፋት ምክትል እና የPLO ደህንነት ዘርፍ ሃላፊ በነበረው አቡ-ኢያድ (ሰላሕ ኸለፍ) የተፈጸመው ግድያ በዓለም ዙሪያ ከፍተኛ ውግዘትን አስከትሎበት ነበር።

አቡ-ኒዳል ለኢራቅ እየሰራ የሊቢያ መንግሥትንም አገልግሏል። በዚህም ብዙ ተከፍሎታል። በኋላ ላይ ግን በፍልስጥኤማዊያንና በሌሎች ዐረቦች ዘንድ ስሙን ያስጠቆሩ ፋይሎች ይወጡበት ጀመር። እነዚህ ፋይሎች አቡ-ኒዳል "ሞሳድ" ከሚባለው የእስራኤል የስለላ ተቋም ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንደነበረው የሚያጋልጡ ነበሩ። የዐረብ ፋይሎች እና የአሜሪካ ጋዜጦች በጉዳዩ ላይ በሰፊው ጽፈዋል።

ሞሳድ በቀረበበት ክስ ላይ አስተያየት ሰጥቶ አያውቅም (ተቋሙ በውጪ ስለሚፈጽማቸው ኦፕሬሽኖች አስተያየት አለመስጠቱ የሚታወቅበት ቋሚ አሰራር ነው)። አቡ-ኒዳል ግን በተጋለጡት ፋይሎች የተነሳ ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ነው የገባው። የትኛውም የዐረብና የምዕራብ ሀገር ሊያስጠጋው ባለመፍቀዱ የመጨረሻዎቹን አስር ዓመታት ራሱን በጣም ሸሸጎ ነው የኖረው። በስተመጨረሻም ባልታወቀ መንገድ ወደ ኢራቅ መግባቱ ስለተደረሰበት የኢራቅ የደህንነት ሚኒስትር አሳድዶ ያዘው። በአንድ ስውር ቤት ውስጥ በምርመራ ላይ እያለ ራሱን መግደሉም August 12/2002 ይፋ ሆኗል።
----
አፈንዲ ሙተቂ
ሀምሌ 6/2014
1.6K viewsedited  20:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 23:25:27 "አቡ ኒዳል": ዓለምን ያንቀጠቀጠው አሸባሪ
-------
ጸሐፊ: አፈንዲ ሙተቂ
-------
የዚህ ሰው ትክክለኛ ስም "ሰብሪ ኸሊል አል-በንና" ነው። ሆኖም ሰውዬው በደንብ የሚታወቀው "አቡ ኒዳል" በተሰኘ የትግል ስሙ ነው። በጽሑፍም ሆነ በሚዲያ በሚወሳው "አቡ ኒዳል" በሚለው ስም ነው።

"አቡ ኒዳል" በ1937 በጃፋ ከተማ የተወለደ ፍልስጥኤማዊ ነው። ይህ ሰው ትግል የጀመረው በያሲር አረፋት የሚመራውን የ"ፋታሕ" አንጃ በመቀላቀል ነው። በ1960ዎቹ መጨረሻ ላይ በሱዳን የፍልስጥኤም ነጻ አውጪ ድርጅት (PLO) ተወካይ ሆኖ ሰርቷል።

በ1970ዎቹ አጋማሽ ላይ ግን አቡ ኒዳል "የፋታሕ አመራር የትግል ወኔ የለውም" የሚል ንትርክ መፍጠር ጀመረ። የፋታሕ መሪዎች "ከትጥቅ ትግሉ ባሻገር የፍልስጥኤም ችግርን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚቻልበት አማራጭም መፈለግ ይገባል" የሚል አቋም ሲይዙ ደግሞ አቡ ኒዳል "ያሲር አረፋት እና ጓዶቹ የፍልስጥኤምን ትግል ክደዋል፣ ከእስራኤል ጋር ፈጽሞ መደራደር አይቻልም፣ የፍልስጥኤም ህዝብ እስራኤልን ከማጥፋት ውጪ ሌላ ግብ ሊኖረው አይገባም" በማለት ከፋታሕ መውጣቱን አስታወቀ። የፋታሕ መሪዎችንም ለማጥፋት ዛቻ አሰማ። "ፋታሕ" በሚለው ስም ላይ "አል-መጅሊስ አሥ-ሠውራ" (Revolutionary Council) የሚል ስም በመጨመር "Fatah- the Revolutionary Council" የተሰኘ አዲስ ድርጅት መመሥረቱንም አስታወቀ።

"አቡ ኒዳል" በ1975 ከፋታሕ እንደወጣ ከስሙ ጋር ተያይዞ የዘለቀውን አደገኛ የሽብር ድርጊት መፈጸም ጀመረ። ፍልስጥኤማዊም ሆነ እስራኤላዊ፣ ዐረብም ሆነ ፈረንጅ የሽብሩ ዒላማ ሆኑ። ኤምባሲዎችን በቦምብ ማጋየት፣ አውሮፕላን መጥለፍ፣ በምኩራብ በተሰበሰቡ የአይሁድ ጸሎተኞች ላይ ግድያ መፈጸም፣ በፋታሕ ካምፕ ላይ ድንገተኛ ወረራ ፈጽሞ ብዙዎችን መግደል ወዘተ በመሳሰሉት መንገዶች በድምሩ የአንድ ሺኅ ሰዎችን ሕይወት አጠፋ። በ1970ዎቹ እና በ1980ዎቹ በዓለማችን በጣም የሚፈሩት አሸባሪዎች ሁሉ ቁንጮ ሆኖ ተገኘ።

"አቡ ኒዳል" ዓለምን በሽብር ድርጊቶቹ ሲበጠብጥ የነበረው Fatah Revolutionary Council ብሎ በሰየመው ድርጅት ድርጅት ስር ባዋቀረው ኔትወርክ ነው። ይሁንና የእርሱ ድርጅት በስፋት የሚታወቀው "Abu Nidal Organization" (ANO) በተሰኘ ስም ነው። በዚህ ድርጅት ስር እጅግ ምርጥ የተባሉ እና ከ800 የማይበልጡ ገዳይ ኮማንዶዎች ብቻ ተሰባስበው ነበር። እነዚህ ኮማንዶዎች ወደ ድርጅቱ ከመግባት በስተቀር ከድርጅቱ መውጣት አይፈቀድላቸውም። በድርጅቱ ውስጥ ሳሉ የሚፈልጉት ሁሉ ይሟላላቸዋል። ከድርጅት ለመውጣት ካሰቡ ግን የሞት ቅጣት ይፈጸምባቸዋል። ከድርጅቱ ከድተው የወጡትን ሰዎች አቡ ኒዳል እያሳደደ አጥፍቶአቸዋል። ከጥቃቱ የተረፉት በጣት የሚቆጠሩት ብቻ ናቸው።

ANO ከአርባ በላይ በሚሆኑ ሀገሮች ውስጥ የራሱ ሴሎች ነበሩት። እነዚህ የአቡ ኒዳል ሴሎች በሃያ ሀገራት ውስጥ በድምሩ መቶ አርባ የሚሆኑ የሽብር ድርጊቶችን ፈጽመዋል። ይህ ድርጅት ከፈጸማቸው ጥቃቶች መካከል በቪየና እና በሮም አየር ማረፊያ የመንገደኞች ማስተናገጃ ላይ በተመሳሳይ ወቅት የተፈጸሙ ጥቃቶች፣ የፋታሕ ደጋፊዎች በሚኖሩበት ካምፕ ላይ የተፈጸመ የፍልስጥኤማዊያን ግድያ፣ በ1985 የግብጽ አየር መንገድ ንብረት በነበረ አውሮፕላን ላይ የተፈጸመ ጠለፋ (60 ሰው ተገድሎበታል)፣ በ1986 ከካራቺ ወደ ኒውዮርክ በሚበር የአሜሪካ አየር መንገድ አውሮፕላን ላይ የተፈጸመ ጠለፋ (ሃያ ሰው ሞቷል)፣ በተለያዩ የአፍሪቃ እና የአውሮጳ ሀገሮች በተመደቡ የፈረንሳይ፣ የሳዑዲ፣ የዮርዳኖስ፣ የእስራኤል እና የፍልስጥኤም ዲፕሎማቶች ላይ የተፈጸሙ ግድያዎች ይጠቀሳሉ።
-----
"አቡ ኒዳል" እስከ ዛሬ ድረስ "አሸባሪ" ተብለው ከተፈረጁ ግለሰቦች በብዙ መልኩ ይለያል። አንደኛ፣ ሰውዬው ጭካኔ እንጂ ርሕራሔ የሚባል ነገር አያውቅም። "እገድለዋለሁ" ያለውን ሰው መግደል እንጂ ምንም አይታየውም ነበር። ከተለያዩ ስፍራዎች አፍኖ የሚወስዳቸውን ሰዎች ሕይወት ከማጥፋት በቀር በድርድር ሲለቃቸው አልታየም። ሁለተኛ ሰውዬው ግልጽ የሆነ ርእዮተ ዓለም አልነበረውም። የኮሚኒዝም ሆነ የሶሻሊዝም ተከታይ አይደለም። የተለየ ሃይማኖታዊ አስተርዮ አማኝም አልነበረም። ሶስተኛ አቡ ኒዳል "የፍልስጥኤም ነፃነት ተፋላሚ ነኝ" ቢልም የሚታገልለት ዓላማ በግልጽ የሚታወቅ አልነበረም። ድርጊቶቹ በሙሉ ለፍስጥኤም ነፃነት እንታገላለን ከሚሉት ድርጅቶች ተቃራኒ ነበሩ (ለምሳሌ በዘመኑ ብዙ ፍልስጥኤማዊ ድርጅቶች ነበሩ። እነዚያ ድርጅቶች በዓላማ እና በስልት የተለያዩ ነበሩ። ሆኖም አንድ ፍልስጥኤማዊ ድርጅት ሌላውን ድርጅት በመሳሪያ ሃይል አያጠቃም። "ፍልስጥኤማዊ ድርጅት ነኝ" እያለ ሌሎች ድርጅቶችን በመሳሪያ መፋለምን ያመጣው የአቡ ኒዳል ድርጅት ነው)።

ከላይ ከተጠቀሱት ነጥቦች በበለጠ ሁኔታ አቡ-ኒዳልን ልዩ የሚያደርገው ሌላ ጉዳይ አለ። ይህም እርሱን ከሚያስተናግዱት ከሶስት ያልበለጡ ሀገራት ውጪ ሌሎች የዓለም ሀገራት በሙሉ ሰውዬውን "አሸባሪ" ብለው የፈረጁት መሆኑ ነው።

ይህ ፍረጃ በሀገራት ብቻ ሳይወሰን በዘመኑ "አሸባሪ" ተብለው የተፈረጁ ድርጅቶችንና ግለሰቦችን ጭምር የሚያካትት መሆኑ ያስደንቃል። ለምሳሌ በዚያ ዘመን "Shining Path" የሚባል እና በፔሩ ጫካዎች ውስጥ የሚታገል ድርጅት ነበር። ያ ድርጅት በአሜሪካ እና በብዙ ሀገራት "አሸባሪ" ተብሎ የተፈረጀ ነው። ታዲያ ይኸው ድርጅት አቡ ኒዳልን "አሸባሪ" ይለው ነበር።

እዚህ ላይ ሌላ የማመዛዘኛ ምሳሌ ልጨምርበት። በዚያ ዘመን "ካርሎስ ቀበሮው" የሚባል ሌላ ሰው አለምን ሲያናውጣት እንደነበረ ይታወቃል። ይሁንና ካርሎስን በግልጽ "አሸባሪ" ብለው የፈረጁት ምዕራባዊያን ሀገራት፣ እስራኤል እና ወዳጆቻቸው ብቻ ነበሩ። የኮሚኒስቱ ዓለም ካርሎስን "የፍልስጥኤም ነፃነት ታጋይ" ነበር የሚለው (አንዳንዶቹ እንዲህ ማለት ቢከብዳቸውም ሰውዬውን "አሸባሪ" ብሎ ከማውገዝ ይቆጠቡ ነበር)። "አቡ ኒዳል"ን የወሰዳችሁት እንደሆነ ግን የትኛውም ወገን "አሸባሪ" ነበር የሚለው።

ታዲታ ከሁሉም በላይ አቡ ኒዳልን ይጠሉ የነበሩት ማን መሰሏችሁ? ፍልስጥኤማዊያንና የፍልስጥኤም ድርጅቶች ናቸው። የትኛውም ፍልስጥኤማዊ ለአቡ ኒዳል ፍቅርና አክብሮት አልነበረውም። የለውምም። በአቡ ኒዳል ትእዛዝ ህይወታቸው ከጠፋው ሰዎች መካከል ግማሽ ያህሉ ፍልስጥኤማውያን ነበሩ። አቡ ኒዳልን የሚወዱትና የሚያደንቁት አንድ ሺህ የማይሞሉት ተከታዮቹ ብቻ ነበሩ።
----
ፓትሪክ ሲል የሚባለው የኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጠኛ በ1989 የአቡ ኒዳልን ህይወት እና ድርጊት የሚያትት "Abu Nidal: a Gun for Hire" የተሰኘ መጽሐፍ ጽፎ ነበር። ፓትሪክ ለመጽሐፉ የሰጠው ንዑስ ርእስ በደንብ የታሰበበት መሆኑ ያስታውቃል። ርእሱ የአቡ ኒዳልን ማንነት በትክክል የሚገልጽ ነውና።

"Gun for Hire" በማለት "ለኪራይ የቀረበ ጠመንጃ" ወይንም "የሚከራይ ጠመንጃ" ማለት ነው። እውነቱ ያለው እዚህ ውስጥ ነው። እዚህ ውስጥ ትልቅ ሚስጢር አለ።
1.5K views20:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 07:19:50 ከሼኽ ሑሴን ጂብሪል ግጥሞች
--

ሸዋ መርዙን ገዛ መሪውን ሳይተካ
ወያኔ አስፈራርቶት ንጉሥ እንዳይተካ
መዝረፍ እንዲመቸው ቦታና ፈረንካ
እንዴት ሰው በአገሩ ደም ለውሶ ያቡካ?
ጥይት እህል ሆኖ ሐበሻ ላይ ቦካ::
--
ቦታና መሬቱን ከተወሰደበት
ወዲያው መዓት ይወርዳል ታላቅ ጦርነት
በአማራ በእስላም ይገባል ድህነት
በተለይ አሥመራ ትሆናለች ዱቄት
ሸዋ ጠላት ገዛ ጥይት እረከሰበት::
--
መሳፍንት ከሞተ በሸዋ መዲና
ችግር ይፈጠራል አገርም አይቀና
ሐበሻ የዚያን ቀን አያገኝም ጤና
መለፍለፍ ነው እንጅ አዋጁም አይጠና
በለው ቶሎ አይበርድም ደም ተቃብቷልና::
--
ተዳፍና ስትኖር የአሥመራ እሳት
ማንም እንዳጭራት በውሃ ሲያጠፋት
በግድ አነደዱት የሸዋን ቅርጫት
ኋላ ግን ያራሉ እንደ እሳት እራት
ሸዋ ጦሩን ሰዶ አጣበት ብልሃት::
--
ሐበሻ ላም ሆና ታስራ ከታለበች
ጡቷን መዥገር ወሮት ጥጃዋን ገደለች
ላምዋም ትሞታለች እየመነመነች
ወተት ቢሉ አይገኝ አንደዜ ሙታለች
ይዘገያል እንጅ ኋላ ትድናለች::
--
አላህ ዝም ብሎ መንግሥት ሊያሳስት
ሰው እንደፍሪዳ ሲታረድበት
ምን ይችል ሐበሻ ጉድ አጃኢበት
በጦሩ ጨፍጭፎ ላይረጋ መሬት
እንኳንም አልደረስን ስትነድ መሬት::
--
የአሥመራ ወያኔ ከያዘ ጠመንጃ
ደንግጦ ይሞታል የአሥመራ ስልቻ፣
የኋላ የኋላ ከቲማውን እንጃ
ምን አስለፈለፈኝ ላይገኝ ፈረጃ
ነስሩም አይታወቅ ዘላለም ጦር ብቻ::
--
ምን ኑሮ ይገኛል መንግሥት ከከፋ
ሰውን ለመግደል ጦሩን ከአስፋፋ
ውሸት እንዳይመስልህ ይሆናል በይፋ
ጠብቀው ዘመኑን እንዳታንቀላፋ
ወቅታቸው እስኪቀርብ እስኪዘልቅ በይፋ::
--
ይኸ ቻይና እሚሉት ዘራቸው ካልጠፋ
ችግር ይፈጠራል ይሆናል የከፋ
ማጥፋት ይሻል ነበር በአገር ሳይስፋፋ
ወልደን ሳንጥለው ልጃችን ሳይጠፋ
ጠብቀው ዘመኑን እስኪታይ በይፋ::
--
ሐበሻ በሞላ በጦር ከተመራ
ወቅቃቸው ያበቃል ፉቀራና ደብተራ
ለአገር ባይመቹ የሚሠሩት ሥራ
ምድር እያሳዩ ሲያስጥስ ደንቃራ
ጉዳቸው አያልቅም ቢወራ ቢወራ::
(አቶ ቦጋለ ተፈሪ በዙ ካሳተሙት መጽሐፍ የተገኙ ናቸው)
2.0K views04:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 07:05:56
አሳዛኙ የአንድሬስ ኤስኮባር አሟሟት
----
በ1994 በአሜሪካ በተካሄደው የዓለም ዋንጫ ተሳታፊ በነበረው የኮሎምቢያ ብሄራዊ ቡድን ውስጥ በተከላካይነት ከተሰለፉት ተጫዋቾች መካከል አንዱ “አንድሬስ ኤስኮባር” የሚባል የሃያ ሰባት ዓመት ወጣት ነበር፡፡ ኤስኮባር የኮሎምቢያ ቡድን ከአሜሪካ ብሄራዊ ቡድን ጋር ባደረገው ሁለተኛ ጨዋታው ሳያስበው የመጀመሪያውን ግብ በራሱ ቡድን ላይ አስቆጠረ፡፡ ቀደም ሲል ከሮማኒያ ጋር ተጫውታ 3 ለ 0 የተሸነፈችው ኮሎምቢያ ከስዊትዘርላንድ ጋር ባደረገችው የመጨረሻ ጨዋታ 2 ለ 0 ተሸንፋለች። አጠቃላይ ነጥቧ ከሌሎች ቡድኖች በታች በመሆኑ በጊዜ ከውድድሩ ከተሸኙት አንዷ ሆነች፡፡

ታዲያ ከውድድሩ በጊዜ የተሸኘው የኮሎምቢያ ብሄራዊ ቡድን ወደ ሀገሩ ሲመለስ ያልተጠበቀ አስደንጋጭ አደጋ ተፈጠረ፡፡ አንድሬስ ኤስኮባር በራሱ ግብ ላይ በስሕተት ባስቆጠራት መዘዘኛ ግብ የተቆጡ የማዴሊን ከተማ ወሮበሎች በስድስት ጥይት ደብድበው ገደሉት፡፡ ገዳዩ እያንዳንዱን ጥይት ሲተኩስ “Goal” እያለ ይጮኽ እንደነበረ በቦታው የነበሩ ምስክሮች መናገራቸው ደግሞ ብዙዎችን ስሜታዊ አደረገ፡፡ የዓለም የስፖርት ቤተሰቦችና መላው የእግር ኳስ አፍቃሪዎች በዚህ አሳዛኝ ድርጊት ልባቸው ተሰበረ፡፡
-----
ኤስኮባር ለምን ተገደለ? በኦፊሴል የተነገረው ምክንያት ከላይ የተገለጸው ነው፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን ግን “ገዳዩ ቁማር አስይዞ ከፍተኛ ገንዘብ ስለተበላ ነው ኤስኮባርን የገደለው” የሚል ወሬ በሰፊው ተወርቶ ነበር፡፡

ያ አስደንጋጭ ክስተት ሲፈጠር ያልነበራችሁ ሰዎች የሚከተለውን ሊንክ ከፍታችሁ የአንድሬስ ኤስኮባርን የእግር ኳስ ውሎ በአጭሩ የሚያሳየውንና በFIFA የተዘጋጀውን አጭር ቪዲዮ እንድትመለከቱት ተጋብዛችኋል፡፡



1.7K views04:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 00:19:18
Luucco Konootii (ሉጮ ይኸውላችሁ)
-----
Afandii: Luucco (አንተ ሉጮ)
Luucco: Yeey (አቤት)
Afandii: Meeshaa xiqqaa tokko naaf ba'atuu nidandeessaa? (የሆነ ትንሽዬ እቃ ልትሸከምልኝ ትችላለህ?)
Luucco: Yaaboo ati wayyaa qabda (አንተ ደልቶሃል እባክህ!)
Afandii: Akkamitti! Maal jechuu keeti? (እንዴት? ምን ማለትህ ነው?)
Luucco: Ani nafsee tiyyaahu ba'achuu dadhabeetiin jira (እኔ ለራሴ ነፍሲያዬን እንኳ መሸከም አቅቶኛል)
----
Kkkkkkkkkkkkkkkkk
Koflaaniin gaggabe!
2.0K views21:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ