Get Mystery Box with random crypto!

አድስ ዜና

የቴሌግራም ቻናል አርማ adszena — አድስ ዜና
የቴሌግራም ቻናል አርማ adszena — አድስ ዜና
የሰርጥ አድራሻ: @adszena
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.34K
የሰርጥ መግለጫ

ወቅታዊ፣ ጠቃሚ እና እንገብጋቢ መረጃወችን ከስር ከስር ለመከታተል የዚህ ቴሌግራም ቻናል ቤተሰብ ሆኑ!
ይጫኑ @adszena
Welcome to addis zena latest Ethiopian news channel you will get trust, usfull and latest news in and around the globe! STAY TUNED WITH ADDIS ZENA👍
@adszena

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-08-12 10:33:10 የአባይ ውሃ ለሦስተኛ ጊዜ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አናት ላይ መፍሰስ ጀምሯል፡፡

በግድቡ ግንባታ ላይ የተሳተፉ ባለሙያዎችም የደስታ ስሜታቸውን ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ፤ ከለውጡ በኋላ በፕሮጀክቱ ላይ በተወሰደው የማስተካከያ እርምጃ በግድቡ ውስጥ መተከል የነበረባቸው የውሃ ማስተላለፊያ የብረታ ብረት ስራዎች ተጠናቀው የግድቡን የመካከለኛው ክፍል ከፍታ ከባህር ጠለል በላይ ስድስት መቶ ሜትር እንዲሁም ግራና ቀኙን ስድስት መቶ አስራ አንድ ሜትር ማድረስ መቻሉም ገልጿል።

ከሶስት ዓመት በፊት ለዘመናት ከባህር ጠለል በላይ በአምስት መቶ ሜትር ከፍታ ላይ ይፈስ የነበረው የአባይ ወንዝ ዛሬ ለሦስተኛ ዙር በግድቡ አናት ላይ የፈሰሰው ከባህር ጠለል በላይ በስድስት መቶ ሜትር ከፍታ ላይ መሆኑን አሳውቋል።

በአሁኑ ወቅት የግድቡ ግራና ቀኝ ጠርዝ ከባህር ጠለል በላይ ስድስት መቶ አርባ አምስት ሜትር የደረሰ ሲሆን የግድቡ የሲቪል ሥራዎች ግንባታ 95 % ፣ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎች ፍብረካና ተከላ 61 % እንዲሁም የብረታ ብረት ሥራ 73 % ፣ አጠቃላይ አፈፃፀሙ ደግሞ 83 ነጥብ 3 % ደርሷል፡፡

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከፍታ ከመሬት 145 ሜትር ሲሆን ርዝመቱ ደግሞ 1 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር ይሆናል፡፡

የዋናው ግድብ ውፍረት የግድቡ ግርጌ ላይ 130 ሜትር፥ የግድቡ ጫፍ ወይም የላይኛው ክፍል ደግሞ 11 ሜትር ነው።

በበጀት ዓመቱ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በ2 ዩኒት ኃይል ማመንጨት እንዲጀምር ለማድረግ የያዘው እቅድ ተሳክቷል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
981 viewsMAK story, 07:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ