Get Mystery Box with random crypto!

Adoni Gospel channel

የቴሌግራም ቻናል አርማ adonigospel — Adoni Gospel channel A
የቴሌግራም ቻናል አርማ adonigospel — Adoni Gospel channel
የሰርጥ አድራሻ: @adonigospel
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 6.70K
የሰርጥ መግለጫ

የእግዚአብሄርን ፍቅር፣ ምህረትና ይቅርታ በተገለጠው የወንጌሉ ቃል መሰረት የምንማማርበት ቻናል ነው። ትምህርቶቹን በሚያመቻችሁ የሶሻል ሚድያ በኩል ለመጠቀም ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ።
Telegram ፦ @adonigospel
WhatsApp ፦ https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

3

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-27 10:47:10 “እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።” — ማቴዎስ 5፥44-45

አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ ጠላታችንን ቀርቶ የሚወዱንንም መውደድ አቅቶናልና የመውደድ ጸጋህን አብዛልን። የሚረግሙንን መመረቅ ቀርቶ ሰላም የሚሙሉንንም መመረቅ አቅቶናልና እባክህ የሚወዱንንም የሚጠሉንንም የምንወድበት አቅም ስጠን።

አቤቱ እግዚአብሔር እምነታችን ላልቷል የክርስትናችን ሕይወታችን ሰንፏን ለሚያሳድዱን መጸለይ አልቻልንም ለሚጹልዩልን እንኳ መንበርከክ አልቻልንም። ለሚጠሉን መልካም ማድረግ ቀርቶ ለምንወዳቸው እንኳ መልካም ለማድረግ ምክንያት የምናበዛ እጅና ፍቅር ያጠረብን ሆነናል። እባክህ ፍቅር አድለን።

አንተን መምሰል ይሁንልን ሃብታም ደሃ ሳትለይ ወንድ ሴት ሳትመርጥ የሚያምን የማያምን ሳትል ሁሉን በአንድ ልብ ወደኃልና እኛም ዘር ጎሳ ብሄር ሳንመርጥ ሰውን ሁሉ እንድንወድ ፍቅርህ ያግዘን። ሸካራው ልባችንን በፍቅርህ ዘይት አለስልስልን። አሜን!

አዶኒ

@adonigospel
@adonigospel
1.1K views@doni, 07:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 20:47:49 ምንም ስለሌለኝ......አመሰግንሃለሁ


ይቺን ምድር ከረገጥኩባት ነፍስ አውቄ ማገናዘብ ከጀመርኩባት ጊዜ ጀምሮ የብዙ ነገሮችን ጠባይ አስተውያለሁ። ሰውን ቢሆን ተፈጥሮን፤ ምኞትን ቢሆን ስሜትን ቃኝቻለሁ። ሁሉም ነገር ደምቀው የሚቆዩበት ጊዜ አላቸው ኋላም የሚደበዝዙበት ጊዜ አላቸው። ብርሃኑ ቢቆይ ለአስራ ሁለት ሰዓት ብቻ ነው ሳትጠግቡት ያልቃል። ያገኛችሁትም ሰው የመደበላችሁን ጊዜ ሲጨርስ ወደራሱ ህይወት ይጓዛል።

ታዲያ በዚህ ምድር ላይ የሚዘልቅ የሚከርም ነገር ምን ይሆን? ከዚህ ምድር የሆነ ዘላቂ ምንም የለም። ነገር ግን የተፈጥሮዋ ፀሐይ ስትጠልቅብኝ ከሰማይ የሆነው ቀኑን ሙሉ የሚያበራልኝ ፀሐይ ያገኘሁት ክርስቶስን ነው። አንድም ቀን ቢዚ ሆኖ ለኔ የነፈገኝ ጊዜ አልነበረም፤ ከስፍራው ያላጣሁት አምኜው ያልተንሸራተተብኝ፤ በሕይወቴ ላይ መጥፎ ትዝታ ያልፈጠረ ጥቁር አሻራ ያላሳረፈብኝ የቅርቤ ሰው ክርስቶስ ነው።

አዎ አልክድም ፦ እርሱ በምድረ በዳ የሕይወት ዘመኔ ሊያረካኝ የመጣ ጥም ቆራጬ ነው። ሐሩር ከሆነብኝ ብዙ ተግዳሮት ደመና ሆኖ የጋረደኝ እረፍቴ ነው። ጆሮዬ የሚሰማው ባጣበት ጊዜ እንኳን እውነተኛ ወዳጅ በፍቅር ሹክሹክታ ወደ ልቤ የዘለቀ ጓደኛዬ ነው። በኔ ሁኔታ ዝቅ ለማለት ያላፈረ ነው ከኔ ጋር አብሮ ለመታየት ያልተሸማቀቀብኝ እርሱ መድኃኔዓለም ነው። ማንም የማይችለውን ለሰው ቀርቶ ለአምላክ እንኳ አስቸጋሪ የሆነውን ጠባይ በሰፊው ትዕግስቱ ተሸክሞ ያኖረኝ፤ ብዙ ስህተቶቼ ያልሰለቹት ሁሌም በኔ ተስፋ የማይቆርጥ የእንደገና አምላክ ሆኖኝ ለዛሬ ያቆመኝ እርሱ ብቸኛዬ ነው።

ምኔ ነህ ልበለው? እንደ እናት አጉርሶኝ እንደ አባት አልብሶኝ፣ እንደ ወንድም መከታ ሆኖኝ፣ እንደ ጓደኛ አበርትቶኝ፣ እንደ ወዳጅ ተሳስሮኝ በዘለዓለም ፍቅር ከኔ ጋር የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ቃላቶች፣ ሆሄያት፣ አረፍተ ነገሮች የማይገልፁ ውዴ ነህ። አመሰግንሃለሁ። ይህንን ወዳጄን እናንተም በአንደበታችሁ ፍሬ አመስግኑልኝ።

አዶኒ

Join @adonigospel
@adonigospel
1.1K views@doni, edited  17:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 17:11:39
ብዙዎች ዛሬን ማየት ናፍቀው ሳይመለከቷት አሸልበዋል፤ አንዳንዶችም ራዕያቸውን ሳያሳኩ ወደዛኛው ዓለም ሔደዋል። እኛም ነገን ማየት እንናፍቃለን ነገ ላይ ከመድረሳችን በፊት ዛሬን በሚገባ ልንኖራት ይገባል። እኛ ዛሬ የሚጎበኘን ሰው አለ የሚጠይቃቸው ደጃቸው የሰው ኮቴ ከሰማ የሰንበቱ ምስኪኖች አሉ። በበዓል ቀን ሁሉም ሰው በቤቱ ከቤተሰቡ ጋር ሲሰባሰብ በብቸኝነትና በብዙ ናፍቆት ብቻቸውን የሚያሳልፉ አዛውንቶች አሉ። እነርሱን በማሰብ ካለን በመቁረስ አዲሱን አመት እንድንቀበል በፍቅር እጠይቃችኋለሁ።

በፍፁም ማንንም ሰው ለማሳቀቅ ታስቦ የተጠቀሰ የገንዘብ መጠን አይደለም። ይህንን ማድረግ የማይችል ሰው የአቅሙን ማድረግ ቢችል አጠራቅመን አስቤዛውን በመግዛት ለምስኪኖቹ ማድረስ እንችላለን። እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይባርካችሁ!

@adonigospel
1.5K views@doni, 14:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 14:56:49 ከአራት አመት በፊት ከፃፍኩት ማስታወሻ

             " እግዚአብሔር ትቶኛል "


       በዚህ ዓለም ላይ መከራ የማይደርስበት ቢኖር ራሱ መከራ ብቻ ነው። ስለዚህ ሁላችንም መከራ በተለያየ ጊዜ ይገጥመናል። በምንፈተንበት ጊዜ ደግሞ ከለመድነው እንጉርጉሮ መሃል እግዚአብሔር ትቶኛል፣ እግዚአብሔር ረስቶኛል፣ እግዚአብሔር አይሰማኝም የሚለው ተጠቃሽ ነው። ወዳጆቼ ፈተናው እጅግ ሲያስመርረን እግዚአብሔር እንዴት አይደርስልኝም? እንዴት ለብቻዬ ይተወኛል እንላለን። ህይወትን ሶስት መቶ ዲግሪ ማየት ስንጀምር የተደሰትነውን ያህል ማዘን እንጀምራለን፤ የሳቅነውን ያህል እናለቅሳለን፤ የጠገብነውን ያህል እንራባለን። ስለዚህ የገጠመህ መከራህ ህይወትን ሶስት መቶ ስልሳ ዲግሪ የማየትህ ማሳያ እንጂ እግዚአብሔር ትቶህ ወይም ረስቶህ አይደለም።

      ንጉስ ዳዊት በእግዚአብሔር እንደልቤ የተባለ ሰው ነው።(1ኛ ሳሙ 13፥14) ይህ ማለት ቅድስናው 99.9 % የደረሰ ሰው ነው ማለት ነው። እንደውም ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ቀጥሎ ለእግዚአብሄር የቅርብ ወዳጁ ዳዊት ሳይሆን አይቀርም። ለእግዚአብሄር እንዲህ የቀረበው ዳዊት ግን እግዚአብሄር እጎኑ ያልተገኘ በሚመስለው ጊዜ ሁሉ እንዲህ በማለት በተደጋጋሚ ቅሬታውን ገልፃል። "እግዚአብሄር ሆይ ለምን እንደዚህ ርቀር ቆምህ? በመከራ ጊዜስ ለምን ድምፅህን አጠፋህ? " (መዝ 10፥1) "
ለምን ተውከኝ? "( መዝ 43፥2)

    እግዚአብሔር ግን በዘመን ሁሉ ማንንም ትቶ አያውቅም ዳዊትንም አልተወውም። ታዲያ ከየት ባመጣው ባህሪው አንተና አንቺን ይተዋል? እንዲህ በማለት በተደጋጋሚ ተስፋ ተሰቶናል፦" አይለይህም ከቶም አይተውህም" (ዘዳ 31፥8)

      እግዚአብሔር አልተውህም አልለይህም አለ እንጂ ህልውናዬ ሁልጊዜ ይሰማሃል በማለት ቃል አልገባም። እንደውም አንዳንድ ጊዜ ፊቱን ከእኛ የሚሰውር መሆኑን ያምናል። “የእስራኤል አምላክ መድኃኒት ሆይ፥ በእውነት አንተ ራስህን የምትሰውር አምላክ ነህ።”— ኢሳ 45፥15
በሕይወትህ የሚያከናውነውን ስራ አቋርጦ በድንገት የሚጠፋ የሚመስልባቸው ጊዜዎች አሉ። ትፀልያለህ ምንም አይሆንም፤ መንፈሳዊ ስሜቶችህ ሁሉ ትተውህ እንደጠፉ ትረዳለህ፤ ዲያብሎስን ትገስፃለህ ድርጊትህ የሚያመጣው ለውጥ የለም፤ ሀጥያትህን ትናዘዛለህ አሁንም ምንም የሚሆን ነገር አይኖርም።

ይህ መንፈሳዊ ጭጋግ እስከመቼ ነው የሚቆየው? የሚለው ነገር ያሳስብሀል። ለቀናት ለሳምንት ለወራት .... እውነት ልንገርህ ይህ ሁሉ ሲሆን አንተ ያጠፋኸው ነገር ያለ ይመስልሀል ግን አንተ ምንም አላጠፋህም።  ከእግዚአብሄር ጋር ያለህን ወዳጅነት መፈተኛና ማሳደጊያ ሂደት ነው።

የእግዚአብሄር ህልውና በማይሰማህና በህይወትህ በመስራት ላይ ያለ የመሆኑ ግልጥ ማረገገጫ በማይኖርህ ጊዜ እግዚአብሄርን መውደድህን፣ማመንህን መታዘዝህን ማምለክህን ቀጥል። አዲስ ክርስቲያን በሆንክ ጊዜ እግዚአብሄር ብዙ የማረጋገጫ ስሜቶችን ይሰጥሀል በጣም ጨቅላና ግለ ተኮር ፀሎቶችህን ይመልሳል። ይህን የሚያደርገው ህያውነቱን ታውቅ ዘንድ ነው። በእምነት እያደክ ስትሄድ ግን እነዚህን ጥገኝነቶች ያቋርጣቸዋል።

መገኘቱ በማይሰማህ ጊዜ እንኳን እግዚአብሄር በቅርብህ አለ። መገኘቱ በስሜት መግለጥ የማይቻልና እጅግ ታላቅ ነው። መገኘቱ እንዲሰማህ ይፈልጋል ግን በስሜት ከምታውቀው ይልቅ በእርሱ ማመንህን ነው ይበልጥ የሚሻው። እግዚአብሄር የሚያስደስተው የስሜቶች ጉዳይ ሳይሆን እምነትህ ነው።

      አዶኒ

Join፦ @adonigospel
@adonigospel
1.1K views@doni, 11:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 09:58:54 ቀናችሁ ብሩክ ይሁን

@adonigospel
@adonigospel
1.1K views@doni, edited  06:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 09:42:55 እግዚአብሔር መባረክን ይባርካችሁ

ለወዳጅዎ ይባረኩበት ዘንድ በፍቅር ሼር ያድርጉላቸው

ወንድማችሁ አዶኒ

@adonigospel
1.2K views@doni, edited  06:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 19:16:24 ወዳጆቼ ሰው አለባበሳችሁን ተመልክቶ ተመችቷቸዋል ይላችኋል ማንም የማያይላችሁን የተሸከማችሁትን ሸክም ግን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያውቀዋል።

ገጻችሁን ተመልክተው ውበቱን ደፍቶባችኋል ይላችኋል። በጓዳ የምታፈሱትን እንባ ግን መድኃኔዓለም ያውቅላችኋል።

ማንም ደርሶ የማይነካላችሁን የችግራችሁን ስምጥ ሸለቆ ጠልቆ የሚነካላችሁ፤ ሸክማችሁን የሚያንከባልላችሁ፤ እንባችሁን የሚያብስላችሁ አማኑኤል አለ።

እርሱ የተሰበረ ልብን፣ የተሰበረ ህልምን፣ የተሰበረ ሕይወትን ይፈውሳል። እመኑት መቼም አይጥላችሁም። የሰላም ምሽት ይሁንላችሁ!

አዶኒ

ነሐሴ 18/2014 ዓ.ም

@adonigospel
@adonigospel
4.7K views@doni, 16:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 08:32:50
Join and share @adonigospel
1.3K views@doni, 05:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 15:03:36 እግዚአብሔር ሁሌም ይወደናል

“እኛም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር አውቀናል አምነንማል። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፥ በፍቅርም የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል።”  — 1ኛ ዮሐንስ 4፥16

    ስታዝኑ፣ ብቸኝነት ሲሰማችሁ፣ ከፍቅር የተራቆታችሁ ሲመስላችሁ፣ ተስፋ መቁረጥ ሲያጋጥማችሁ፣ ጭለማ ውስጥ የወደቃችኩ ሲመስላችሁ ሁሌም እንደ አላርም ቀስቅሶ የሚያነቃችሁን አንድ ነገር አስታውሱ፦ እርሱም
" እግዚአብሔር ወረት በሌለው ፍቅሩ ይወደኛል" ማለትን ነው።

    በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ብትሆኑ ካላችሁበት መጥፎ ስሜት ውስጥ መንቅሎ የሚያወጣችሁ፤ የሞት መንገድን ስትጀምሩ አጥር ሆኖ የሚመልሳችሁ የእግዚአብሔር ፍቅርን ማሰብ ነው።

    ሰው በማይወዳችሁ ዘመን የሚወዳችሁ እግዚአብሔር ነው፤ ሰው ወረተኛ ነውና ዛሬ ያላንተ መኖር አልችልም ቢላችሁ ውሎ አድሮ ያለ አንተ መኖር ተስማማኝ ይላችኋል። እግዚአብሔር ግን ወረት በሌለው ፍቅር ይወዳችኋል። ወዳጆቼ እግዚአብሔር ያላችሁበትን ሁነት ባለፈ፣ ያላችሁበትን ድክመት ባለፈ ፍቅር ይወዳችኋል። አመንዝራ ስለሆንሽ አይጠላሽም፤ ሌባ ስለሆንክ አይጠላህም በእግዚአብሔር ፍቅር ላይ ጥርጣሬ አይግባችሁ። እግዚአብሔር እንኳን ለኛ ለሰይጣንም ጥላቻ የለውም።

    የልባችሁ profile word እግዚአብሔር ለዘላለም ይወደኛል የሚል ይሁን። ተባረኩልኝ

አዶኒ

ነሐሴ 17/2014 ዓ.ም

ቻናላችንን በመቀላቀል በየቀኑ የሚለቀቁ ትምህርቶችን ዝማሬዎችን ያግኙ
@adonigospel
@adonigospel
1.6K views@doni, 12:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 10:29:15 ይህንንና ሌሎችንም የዲያቆን ሐዋዝ ተገኝ አዲስ ዝማሬ በyoutube ገብታችሁ በመስማት እንድትባረኩ እንድትፅናኑ እጋብዛችኋለሁ።

አገልግሎቱን ማገዝ ዘማሪውንም ከዚህ በላይ ጸጋውን እንዲያካፍል በገንዘብ ማገዝ እፈልጋለሁ ለምትሉ ወዳጆች ሁሉ ፦
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000402887037
ሐዋዝ ተገኝ


YouTube


1.2K views@doni, edited  07:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ