Get Mystery Box with random crypto!

አዲሰ ነገር አለም አቀፍ ዜና 🌎🌏🌍

የቴሌግራም ቻናል አርማ adisnews — አዲሰ ነገር አለም አቀፍ ዜና 🌎🌏🌍
የቴሌግራም ቻናል አርማ adisnews — አዲሰ ነገር አለም አቀፍ ዜና 🌎🌏🌍
የሰርጥ አድራሻ: @adisnews
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.65K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የዉጭ እና የሀገር ዉሰጥ አዳዲሰ
ዜናዎች የምናቀርበት ቻናል ነዉ።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
አለምአቀፋዊ 🌎🌏🌍
ወቅታዊ 🔊🔊🔊🔊
መረጃ የሚደርስበት ቻናል ነዉ
@Adisnews
@Adisnews
@Adisnews
እዉነተኛ የመረጃ ምንጭ

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2021-07-28 12:39:59 ሰላም አዲሰ ነገር አለም አቀፍ ዜና ቤተሰቦች እኛ የተለያዩ ዜናዎች እንድናደርስ የእናንተ እገዛ ያሰፈልገናል
እና እናንተ የተለያዩ ዜና አዳማጭ ቤተሰብ 'ጓደኛ ;ዘመድ ሼር በማድረግ እነሱም የተለያዩ ዜናዎች እንዲሰሙ አድርጉ በተጨማሪ ደግሞ ቻናል ያላችሁ ቻናል ላይ ግሩፕ ያላችሁ ግሩፕ ላይ ሼር በማድረግ ይተባበሩን የእናንተ ሼር ማድረግ ለእኛም
በርታት ይሆነናል እናመሰግናለን።

አዲሰ ነገር አለም አቀፍ ዜና
@Adisnews
@Adisnews
@Adisnews
2.9K views09:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-26 21:24:07 በትግራይ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች የነበሩ ተማሪዎች ወደ ሰመራ መግባት ጀመሩ

በትግራይ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ሲማሩ የነበሩ ተማሪዎች ወደ አፍር ክልል፤ ሰመራ ከተማ መግባት መጀመራቸው አል ዐይን አማርኛ ያነጋገራቸው የሰመራ የከተማዋ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡የተማሪዎች ወላጆች ከሰሞኑ ልጆቻቸው ትግራይ ክልል ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመለሱ ጥያቄ ሲያቀርቡ ቆይተዋል፡፡

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከትግራይ ክልል መውጣት ከጀመረ እና የተናጠል ተኩስ አቁም ከታወጀ በኋላ ትግራይ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች ልጆች ያሏቸውን ወላጆች ሲያሳስብ ቆይቷል፡፡
አሁን ላይ በትግራይ ክልል ከሚማሩ ተማሪዎች መካከል 325 የሚሆኑት በሰመራ ዩኒቨርሲቲ አቀባበል እንደተደረገላቸው ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የሰመራ ከተማ የሥራ ኃላፊ ለአል ዐይን አማርኛ ተናግረዋል፡፡

ዛሬ ሰመራ የገቡት ተማሪዎች ወደ የቤተሰቦቻቸው እየተሸኙ መሆኑ የስራ ኃለፊው ተናግረዋል፡፡

በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ልጆች ያሏቸው ወላጆች፤ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ኢሲኤ) ልጆቻቸው የሚመለሱበትን መንገድ እንዲያመቻችላቸው ከሰሞኑ በሰልፍ ጠይቀው ነበር፡፡

ትግራይ ክልል ባለው ግጭት ሳቢያ ስጋት ያደረባቸው ወላጆች ከተመድ በተጨማሪ፤ መንግስት በትግራይ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ባሉ በተማሪዎቹ ዙሪያ እልባት እንዲሰጣቸው በተደጋጋሚ ሲጠይቁ ነበር፡፡

የሳይንስና ከፍተኛ ት/ምሚኒስቴር በወቅቱ “ከየዩኒቨርስቲዎቹ አመራሮች እና ከዓለም አቀፍ ተራድኦ ተቋማት ጋር በመሆን ጉዳዩን እየሰራበት ይገኛል፡፡ በተደረገው ጥረትም የዩኒቨርቲዎችን አመራር ለማግኘት የተቻለ ሲሆን ተማሪዎች በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኙና የሁለተኛ መንፈቅ ዓመት ፈተና ለመውሰድ በዝግጅት ላይ ያሉም እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል” ሲል ለወላጆች ጥያቄ መልስ መስጠቱ ይታወሳል፡፡

@Adisnwes
2.8K views18:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-23 12:04:46
ከ30 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላር ይዞ በሕገ-ወጥ መንገድ ሲያዘዋውር የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

ተጠርጣሪው የተያዘው በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው 22 አንድ ተብሎ በሚጠራው ባቡር ጣቢያ ላይ ነው።

ግለሰቡ በወቅቱ 30 ሺህ 204 የአሜሪካ ዶላር ይዞ ባቡር ሊሳፈር ሲል በባቡር ጣቢያው ላይ ተመድበው ሲሠሩ የነበሩ የፖሊስ አባላት ባደረጉት ፍተሻ ከነዶላሩ በቁጥጥር አውለውታል።

ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና የውጪ ሀገራት ገንዘቦችን በሕገ-ወጥ መንገድ የመመንዘር ወንጀል የኑሮ ውድነት እንዲያሻቅብ ከማድረግ ባሻገር በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያሳድረው አሉታዊ ጫና ከፍተኛ በመሆኑ ኅብረተሰቡ ይህንን ሕገ-ወጥ ድርጊት ባለመፈፀም እና የሚፈፅሙ አካላትንም ለሕግ አሳልፎ በመስጠት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት እንዲወጣ የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል።

@Adis news
@Adisnews
2.6K views09:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-15 16:32:20
የደቡብ ክልል ልዩ ኃይል ግዳጅ ቀጠና መድረሱን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል

የደቡብ ክልል ልዩ ሀይል የቀረበለትን ሀገራዊ ጥሪ በመቀበል እና ፈጣን ምላሽ በመስጠት በግዳጅ ቀጠና መድረሱን የክልሉን ፖሊስ ኮሚሽን ጠቅሶ የደቡብ ሬድዮና ቴሌቪዥን ዘግቧል፡፡

@Adisnews
@Adusnews
@Adisnews
ሼር በማድረግ ይተባበሩን
2.7K views13:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-14 15:00:01
የራያ ዋጃ፣ የራያ አላማጣ እና ኮረም አካባቢዎች በህወሃት ኃይሎች መያሳዛቸውን ተከትሎ በርካታ ነዋሪዎች ስፍራውን ለቅቀው ለስደት መዳረጋቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ

መንግሥት የአንድ ወገን የተኩስ አቁም አውጆ መከላከያ ሠራዊቱን ከመቀሌና ከተለያዩ የትግራይ ክልል አካባቢዎች ካስወጣ ወዲህ ህወሀት በአማራ ክልል የተያዙ ላለፉት 30 ዓመታት በትግራይ ክልል ስር የቆዩ ግዛቶችን ለማስመለስ ውጊያውን እንደሚቀጥል በይፋ ገልጿል።

የህልውና አደጋ አጋጥሞናል ሲል መግለጫ ያወጣው የአማራ ክልላዊ መንግሥት «የህልውና አደጋውን አንድነታችንን ጠብቀን በትግላችን እንቀለብሳለን» በማለት «በየትኛውም ዘመን ሰልጥናችሁ፣ የአገርና የህዝብ ሉአላዊነት ለማስከበር በማንኛውም የመንግሥት ጸጥታ መዋቅር ውስጥ ተሰልፋችሁ ስታገለግሉ የቆያችሁና በታሪክ አጋጣሚ የሙያ ዘርፍ የቀየራችሁ የክልላችን ነዋሪዎች ለህልውናችን የምናደርገውን የትግል ጥሪ ተቀብላችሁ በክልሉ ጸጥታ መዋቅር ውስጥ እንድትቀላቀሉ» ሲል ጥሪ አቅርቧል። ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ታዛቢዎች ይበርዳል ተብሎ የተገመተው ግጭት ጦርነት መልኩን ቀይሮ በአማራ እና ትግራይ ክልሎች እንዳይስፋፋ ስጋታቸውን መግለጽ ጀምረዋል።

@Adisnews
@Adisnews
2.6K views12:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ