Get Mystery Box with random crypto!

አዲሰ ነገር አለም አቀፍ ዜና 🌎🌏🌍

የቴሌግራም ቻናል አርማ adisnews — አዲሰ ነገር አለም አቀፍ ዜና 🌎🌏🌍
የቴሌግራም ቻናል አርማ adisnews — አዲሰ ነገር አለም አቀፍ ዜና 🌎🌏🌍
የሰርጥ አድራሻ: @adisnews
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.65K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የዉጭ እና የሀገር ዉሰጥ አዳዲሰ
ዜናዎች የምናቀርበት ቻናል ነዉ።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
አለምአቀፋዊ 🌎🌏🌍
ወቅታዊ 🔊🔊🔊🔊
መረጃ የሚደርስበት ቻናል ነዉ
@Adisnews
@Adisnews
@Adisnews
እዉነተኛ የመረጃ ምንጭ

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2021-10-20 21:31:33
ዛሬ የህወሓትን የጦር መሳሪያ ማምረቻዎች በአየር መደብደቡን መንግስት አስታወቀ

ጥቃቶቹ ዒላማ ያደረጉት የህወሓት የጦር መሣሪያ ማምረቻ እና የጦር ትጥቅ ጥገና ጣቢያዎችን ብቻ ነው

በፌዴራል መንግስት ሥር ያለው የ "ወቅታዊ መረጃ ማጣሪያ ገፅ" በትግራይ ክልል ስለሚፈፀሙ የአየር ድብደባዎች መረጃ አጋርቷል። በዚህም መከላከያ ሠራዊት እያካሄደ ያለው የአየር ድብደባን በተመለከተ የተዛባ ግንዛቤ ቢኖርም፣ በተቃራኒው ጥቃቶቹ ዒላማ ያደረጉት የህወሓት የጦር መሣሪያ ማምረቻ እና የጦር ትጥቅ ጥገና ጣቢያዎችን ብቻ ነው ብሏል።

አክሎም "የመከላከያ ሠራዊት የሚያከውናቸው እነዚህ ሥራዎች የሽብር ድርጅቱ ከባድ የጦር መሣሪያዎችንና ሌሎች ሕገወጥ የጦር መሣሪያዎችን ለመሸሸግ የሚጠቀምባቸውንና ወደ ወታደራዊ መገልገያነት የቀየራቸውን የተወሰኑ ቦታዎች ከጥቅም ውጭ ለማድረግ ያለመ ነው" ሲል ገልጿል።
ወቅታዊ መረጃ ማጣሪያ ገፅ

@Adisnews
@Adisnews
@Adisnews
4.0K views18:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-07 14:17:07 በትናትናሁ እለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ለከፍተኛ የመንግስት ሃላፊነት ቦታዎች ሹመቶች ሠጡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በዛሬው እለት አቶ ተፈሪ ፍቅሬን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ሃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር አድርገው በድጋሚ የሾሙ ሲሆን ለ4 ከፍተኛ የሃላፊነት መደቦችም በሚኒስቴር ማእረግ የሚከተሉትን ሹመቶች ሰጥተዋል፡-

1. አቶ አደም ፋራህ - በሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ዋና አስተባባሪ

2. አቶ ተስፋዬ ቤልጅጌ - በሚኒስትር ማዕረግ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ

3. ዶ/ር ስለሺ በቀለ - በሚኒስትር ማዕረግ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞችና የህዳሴግድብ ዋና ተደራዳሪና አማካሪ

4. ዶ/ር ለገሰ ቱሉ - በሚኒስትር ማዕረግ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ
በተጨማሪም፡

ዶ/ር ምህረት ደበበ - የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚዳንት፤

አቶ ፍሰሃ ይታገሱ - የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ፤

እንዲሁም አቶ አብዱራህማን ሩቤ - የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆነው ተሹመዋል፡፡

@Adisnews
@Adisnews
3.6K views11:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-19 16:30:13 በቆቦ ከተማ በሲቪል ሰዎች ላይ ያነጣጠረው ጥቃት አሳሳቢ መሆኑ ተገለፀ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰማኮ) በቆቦ ከተማና በዙሪያው ካሉ የገጠር ከተሞች የሚደርሱትና በህወሓት ሃይሎች እንደተፈፀመ የሚነገር በሲቪል ሰዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት በእጅጉ የሚያሳስብ መሆኑን ገልጿል።

የሲቪል ሰዎች መኖሪያ አካባቢዎችን ፣ የቤት ለቤት አሰሳና ግድያ ፣ ዝርፊያና የመሰረተ ልማቶች ጥቃት ጭምር መፈፀሙን ለሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ሪፖርት መድረሱን ብስራት ራዲዮ ሰምቷል።

ኮሚሽኑ የሚያደርገውን ምርመራ እንደሚቀጥልና በግጭቱ ሁሉም ወገኖች በማናቸውም ወቅት ሲቪል ሰዎችን የመጠበቅ ፣ ያለባቸው ግዴታ እንዲያከብሩ በጥብቅ አሳስቧል።

@Adisnews
ሼር ሼር
3.4K views13:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-14 08:57:09
ለስኳር ታማሚዎች ቆሽትን ተክቶ የሚሰራ ቴክኖሎጂ ሊቀርብ ነው

የዓይነት 1 የስኳር በሽታን መቆጣጠር የሚያስችል ሰው ሰራሽ የቴክኖሎጂ ሙከራ ላይ አስደናቂ ውጤት መገኘቱ ተሰማ፡፡

ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ውጤት የሆነው ይህ መሳሪያ በሰውነት ቆዳ ውስጥ በሚቀበሩ ሴንሰሮች አማካኝነት ቆሽታቸው ኢንሱሊን ማምረት ያቆመ የስኳር ታማሚዎችን (የዓይነት 1 የስኳር ሕመም ተጠቂዎችን) የስኳር መጠን ባለማቋረጥ የሚከታተል ይሆናል ነው የተባለው፡፡

አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም በቆሽት አማካኝነት አስፈላጊው የኢንሱሊን መጠን በደም ስሮች እንዲሰራጭ ትዕዛዝ ይሰጣል ተብሏል፡፡
መሳሪያውን ታማሚዎቹ የደም ስኳር መጠናቸውን ለመለካት፣ለመቆጣጠር የሚወስዱትን ጊዜ ፣በአጋጣሚ የስኳር መጠናቸው ዝቅ ብሎ ለሕይወታቸው አስጊ ሆኖ ቢገኝ ወደ ሕክምና እንኪደርሱ የሚደረሰውን ጉዳት ያስቀራልም ነው የተባለው፡፡

እስካሁን ድረስም የዓይነት 1 የስኳር ሕመም ያለባቸው 1ሺህ ሰዎች ተለይተው የመቆጣጠሪያ ቴክኖሎጂው እየተገጠመላቸው መሆኑን ዴይሊ ሜይል አመላክቷል።

@Adisnews
3.3K views05:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-13 10:21:12
ሰሜን ኮሪያ አዲስ የረጅም ርቀት ተወንጫፊ ሚሳኤል ሙከራ አደረገች

ሰሜን ኮሪያ አዲስ የረጅም ርቀት ተወንጫፊ ሚሳኤል ሙከራ ማድረጓ ተሰምቷል፡፡
ሙከራ የተካሄደባቸው አዲሶቹ ሚሳኤሎች 1 ሺህ 500 ኪሎ ሜትር ርቀት መምዘግዘግ መቻላቸው ነው የተገለጸው፡፡

በዚህም አብዛኛውን የጃፓን መልክዓምድር ማዳረስ እንደሚቻል ኮሪያን ሴትንራል የተሰኘው የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል፡፡

የሚሳኤል ሙከራው በሀገሪቱ ላይ የሚቃጣን ማንኛውንም ትንኮሳ ለመመከት እና የጠላት ኃይሎችን ወታደራዊ እንቅስቃሴ መቆጣጠር የሚያስችል መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ሙከራው ሀገሪቱ በተጣለባት የኢኮኖሚ ማዕቀብ ሳቢያ አሁን ካለችበት የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ ሆናም አውዳሚ የጦር መሳሪያዎችን የማምረት አቅም እንዳላት ያመላከተ ነው ተብሏል።

በሌላ በኩል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ሰሜን ኮሪያ የባለስቲክ ሚሳኤል ሙከራዎችን ከማድረግ እንድትቆጠብ በተደጋጋሚ ማስጠንቀቁ ይታወሳል፡፡

ይሁን እንጂ ፒዮንግያንግ የተመድ የጸጥታው ምክር ቤትን ማስጠንቀቂያ ችላ በማለት የምታደርገውን የባለስቲክ ሚሳኤል ሙከራ ለማስቆም በሀገሪቱ ላይ ተጨማሪ ማዕቀቦችን መጣል እንደሚስፈልግ ተንታኞች እየተናገሩ ነው፡፡
BBC
@Adisnews
@Adisnews
እወነተኛ የመረጃ ምንጭ
2.7K views07:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-12 15:27:13
የደቡብ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳው በአሸባሪው የሕወሓት ወራሪ ኃይል ጥቃትና ዝርፊያ የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመደገፍና የሽብር ቡድኑን እየተፋለመ ላለው የወገን ራዊት ያላቸውን ደጀንነት ለማረጋገጥ ባህር ዳር ጓብተዋል

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገርን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በባሕር ዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም ዐቀፍ አየር ማረፊያ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

አሸባሪው በአማራና በአፋር ክልል ባደረገው ወረራ በመቶ ሺሕዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ተፈናቅለዋል፤ ከ1 ነጥብ 7 ሚሊዮን በላይ ዜጎችም ለከፋ ችግር ተጋልጠዋል። ኢትዮጵያዊያንም የሽብር ቡድኑን አገር የማፍረስ ተግባር በመመከትና ለተጎዱ ዜጎች ድጋፍ በማድረግ አጋርነታቸውን እያሳዩ ነው።

@Adisnews
@Adisnews
2.3K views12:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-12 11:45:56
ባለፋት 100 ዓመታት ያልተገነባ ሠራዊት ለመገንባት እየሰራን ነው

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

ምእራብ እዝ ጥቅምት 24 የሰሜን እዝን የወጋውን እኩይ ቡድን አይቀጡ ቅጣት የቀጣና ሰሞኑንም በውቅንና ጭና ተራሮች ስር የሽብር ቡድኑን ድባቅ በመምታት ኢትዮጵያውያንን ያኮራ ታላቅ ገድል መፈፀሙን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማይጠምሪ ግንባር በመገኘት ለሠራዊቱ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።ከሁሉም የኢትዮጵያ ጫፍ መጥታችሁ የሀገር ክብር አስጠባቂ፣ ለህልውናዋ ተዋዳቂ በመሆናችሁ ልትኮሩ ይገባችዋል ብለዋል።

ባለፋት 100 ዓመታት ያልተገነባ ሠራዊት ለመገንባት እየሰራን ነው ብለዋል።የአሁኑ ሽፍታ መለማመጃችን ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያችንን ሰላምና ብልፅግናዋን የሚዳፈር ሁሉ ደጋግሞ እንዲያስብ ከአሸባሪ ቡድኑ ሊማር እንደሚገባ ገልፀዋል።ትኩረታችን ሰላምና ብልፅግና ቢሆንም የአየር ኃይላችንን፣ ኮማንዶውንና ሌሎችንም የመከላከያ ክፍሎች እያጠናከርን ነውም ብለዋል።

@Adisnews
2.2K views08:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-10 17:14:45 ብርቄ:
ወሬ በጣም ትወዳለች፡ ቅድም ወደ ስራ እየሔደች...

የሆነ የመኪና አደጋ ደርሶ ቦታው በሰዎች ተከቦ ደረሰች። "እባካችሁ አሳልፉኝ" "እባካችሁ አሳልፉኝ" የተገጨው ዘመድ ነኝ አለች።
የተሰበሰበው ሰው ገለል ብሎ ወደፊት እንድትቀርብ እድሉን ሰጣት።


የሚገርመው ተገጭቶ የወደቀው አህያ ነበር!
3.2K views14:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-10 10:53:40
የወያኔ ቡድን በራያ ግንባር በሶስት አቅጣጫዎች በላካቸው ኃይሎቹ ላይ የማያዳግም እርምጃ መወሰዱን የአማራ ክልል አስታወቀ

የወያኔ ቡድን በራያ ግንባር በሶስት አቅጣጫዎች በላካቸው ኃይሎቹ ላይ የማያዳግም እርምጃ መወሰዱን የአማራ ክልል መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ አስታውቀዋል፡፡

ቡድኑ እንደ ማዕበል ገፍቶ የደፋቸው የጥፋት መልእክተኞቹ በአማራ ልዩ ኃይል፤ ሚሊሻ፣ በብሔር ብሔረሰቦች ጥምር ኃይል እና በሀገር መከላከያ ሠራዊት በኩል በተሠጣቸው አጸፋ በወጡበት ለመቅረት እንደተገደዱ ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

በቡድኑ ኃይል አባላት ላይ በተወሰደባቸው ራስን የመከላከል እርምጃ የሽብር ቡድኑ እንደማዕበል በማትመም የአማራ ክልልን ለመውረር የሚጠቀምበት የሰው ኃይል እንዲያጣ መደረጉንም አመልክተዋል፡፡

@Adisnews
@Adisnews
#አዲሰ ነገር አለም አቀፍ ዜና
ሼር በመድረግ ይተባበሩን
2.9K views07:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-06 13:59:49
ላሊበላ ከተማ የገባው የህወሓት ቡድን አሁን ላይ በመከላከያ ሰራዊትና በክልሉ ልዩ ሃይል እየተመከተ መሆኑን የአማራ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ገለጹ

ህብረተሰቡ በጁንታው የሃሰት ፕሮፓጋንዳ አካባቢውን ለቆ መውጣት የለበትም ያሉት አቶ ግዛቸው÷  ሳይሸበር ራሱን ሊከላከልና  አካባቢውን በንቃት ሊጠብቅ ይገባል ብለዋል።

የህወሓት ጁንታ አሁን ላይ በክልሉ ሶስት ግንባሮች ውጊያ ከፍቷል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ÷አሁን ላይ  በመከላከያ ሰራዊት፣ ልዩ ሃይል ፋኖ እየተደመሰሰና እየተመታ ነው ብለዋል።በአሁኑ ሰዓት  በርካታ የህወሓት ቡድን አባላት መማረካቸውንም ጠቅሰዋል።

@Adisnews
@Adisnews
@Adisnews
2.7K views10:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ