Get Mystery Box with random crypto!

አጫጭር ልብ ወለድ

የቴሌግራም ቻናል አርማ achirlebwlod — አጫጭር ልብ ወለድ
የቴሌግራም ቻናል አርማ achirlebwlod — አጫጭር ልብ ወለድ
የሰርጥ አድራሻ: @achirlebwlod
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.91K

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-03-04 21:19:23
ስዕሉ በሮማን ቻርቲ ውስጥ ይገኛል። ምንም እንኳን ስዕሉን ለመጀመሪያ ጊዜ ስናየው የማይመች ስሜት የሚያሳድር ቢሆንም የተሳለበትን አላማ እና ከስዕሉ ጀርባ ያለውን ታሪክ ስንሰማ በርግጥ ድንቅ ስሜት ያጭራል።
°°°
በአውሮፓ ምድር በፈረንሳይ ሀገር lious XIV በነገሰበት ዘመን ሲሞን የተባለ አንድ ሰው በፈፀመው ወንጀል የሞት ፍርድ ይበየንበታል። የሞት ፍርዱም በርሃብ እንዲፈፀም ወይም እንዲተገበር ፤ ርሃቡ እስኪገድለው ድረስም ወይኒ ቤት እንዲቆይ ወደ ማቆያው ይወረወራል።
ይኸን የሰማችው ፖሮ የምትባል ሴት ልጁ የሚሞትበት ቀን እስኪደርስ ድረስ ለመጎብኘት መንግስቱን ትማፀናለች። መንግስቱም ምንም አይነት የሚበላ ነገር ሳትይዝ እንድትጎበኘው ፈቃዱን ይሰጧታል።
°°°
ልጁም ለወራት በየቀኑ ምግብ ሳትይዝ ገብታ ጎብኝታው ትወጣለች። በወራት ውስጥ በርሃብ የተነሳ የሲሞን መጠውለግ መክሳት እንዲሁም ሞት ቢጠበቅም ሰውዬው ወዙ የተሻለ እየወጣ እያማረበት ለ6 ወራት ይቀጥላል። ይኸን ያስተዋሉ ፓሊሶችም ምን እየበላ እንደሆነ ሲሰልለሉ የገዛ ልጁ ጡቷን ከጨቅላ ልጇ አትርፋ የአባቷን ህይወት ለማሰንበት ስትል እያጠባችው እንደሆነ አዩ።
°°°
ይኸን ነገር ሪፓርት ሲያደርጉ ስለፍቅሯ ሲባል ሰውዬውን በነፃ እንዲለቀቅ ተወስኗል።
°°°
ይኸ ስዕል በ30 ሚሊዮን ዩሮ የተሸጠ ሲሆን የምንጊዜ ውድ ስዕሎች ውስጥ ይመደባል።
°°°
ሀውልቱም David klndt በተባለ ዲዛይነር 1741 ማቆያ ቤቱ ወደዚህ ከአንድ ዓመት በፊት የቀረፀው ነው።
°°°
ስዕሉ እና ሀውልቱ ሴት ልጅ ለአባቷ ያላትን ከፍተኛ ፍቅር ያሳያል ተብሎም ይታመናል።
98 views18:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-28 11:15:39
ሰንፔር ፊልም ፕሮዳክሽን እንኳን ለአድዋ በዓል አደረሳችሁ በዚህ ፕሮዳክሽን ውስጥ ከሚሰሩ ተጨማሪ የ አደባባይ በአላቶች ላይ በመገኘት በዓሉን የሚያስመለክቱ ምርጥ ውብ እና ማራኪ የሆኑ ፎቶዎችን ለማንሳት የፎቶ ፓኬጅ ያዘጋጀን ሰለሆነ ለመነሳት
አድዋ ፎቶ ፓኬጅ :- 5 ፎቶ በ150 ብር
በካፕል እና በግሩፕ ለሚመጡ ልዩ ቅናሽ አዘጋጅተናል ።
ቅድሚያ መነሳት ለምትፈልጉ ወረፋ ለማስያዝ ከስር ባለው ስልክ ቁጥሮች ማነጋገር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
+251 920 59 46 52
+251 9 45 918772
193 views08:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-11 14:08:29
" ብፁዕ አቡነ አብረሃም በዕውነት እርስዎ ይለያሉ

እስኪ በአንድ ቃል ስለ ብፁዕነታቸው የተሰማችሁን ግለጡ

እኔ ግን አንድ ነገር ማለት እፈልጋለሁ መንፈሳዊ ዕውቀታችው ልበ ሰፊነታቸው እርጋታቸው ለእውነት ያላቸው ቆራጥነት የአላማ ፅናታቸው የንግግር ችሎታቸው የቃል ሙላታቸው ....
203 views11:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-11 12:49:46 https://www.facebook.com/100064458415522/posts/pfbid02qxtVE2cN57Digeb4HXxCyWWJUQ1bd5eT73qDcyTmGAJ4oXywRbPsiDsZq23fZT7yl/?sfnsn=mo
209 views09:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-06 00:01:45
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን!

"የነነዌም ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ ለጾም አዋጅ ነገሩ!
ከታላቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ።"
ትንቢተ ዮናስ ምዕራፍ 3 ቁጥር 5

ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ባቀረበችው ጥሪ መሰረት ከነገ በሚጀመረው ጾመ ነነዌን ምክንያት በማድረግ በመላው ዓለም የሚገኙ ሕዝበ ክርስቲያን ጥቁር ልብስ ብቻ በመልበስ በጾምና በጸሎት ምሕላ በመያዝ በቤተ ክርስቲያን ዓውደ ምሕረት በመገኘት ወደ እግዚአብሔር ጾም፤ ጸሎትና ምሕላ እንድታቀርቡ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

ጥቁር ልብስ የምንለብሰው በመከራ መጽናት ለመግለጽ ነው፡፡
እንደሚታወቀው ጥቁር የእውቀት ምልክት ነው ተማሪዎች አውቀናል ሲሉ ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ፡፡ እኛ ከእውቀት በላይ የሆነውን አምላካችንን በመማፀን ከዚህም ማንም ሊያናውጽን እንደማይችል የምናረጋግጥበት፤ ጥቁር የእውነት ምልክት ነው ዳኞች እውነት እንፈርዳለን ሲሉ ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ፡፡ እኛም መከራው የሚያሰቅቀን ሳይሆን ይበልጥ ልንጸናና ልንበረታ የሚገባ መሆኑን ለዓለም ሕዝብ የምናሳይበት በመሆኑ ከጥር 29 እስከ የካቲት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ለሦስት ቀናት በጾምና በጸሎት በአንድ ልብ ሆነን ወደ ፈጣሪያችንን እንድንጮህ አደራ እንላለን፡፡

ቅድስት ቤተ-ክርስቲያን ማቅ ለብሳለች
እኛም ከቅድስት ቤተ-ክርስቲያን ጎን ነን..
90 views21:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-26 21:04:29 የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 18 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ፡፡

በዚህም ተፈታኞች ከዛሬ ሌሊቱ 5 ሰዓት ከ30 ጀምሮ በ በዌብ ሳይት https://eaes.edu.et/ ፤

በ6284 አጭር የጽሑፍ መልዕክት መላኪያ ላይ የምዝግባ ቁጥራቸውን (Registration Number) ብቻ በመላክ ወይም በቴሌግራም https://t.me/eaesbot ማየት የሚችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ተፈታኞች ከተመሳሳይ እና የተዛባ መረጃ ለማሰራጫት ከሚሞክሩ አካላት እራሳቸውን እንዲጠብቁም አገልግሎቱ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡
833 views18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-19 08:09:06
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ 2015 ዓ ም ለከተራ በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ አደረሰን።❖❖❖✣✣✣✥✥✥☩☩☩☩
1.4K views05:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-13 13:50:23 " ️በዚህ ምድር ላይ ሌላውን ለመምሰል እንደመሞከር ከባድ ነገር ምን አለ?

️ሌላውን ለመምሰል ስትሞክር፤ #የምትጣላው ከሰው ጋር ሳይሆን ከገዛ እራስህ ጋር ነው።

️እናም እራስህን አታስቀይመው፤ እውነተኛ ወዳጆችህ አንተን ባንተነትህ ይቀበሉሃል…..ከምንም በላይ እራስህን በመሆን ከራስህ ጋር #ሰላም ፍጠር፤

"ሁሉን ለማስደሰት አትሞክር!"
<>~ ~<> <>~<>

አንድ ነገር ስታደርግ ሰዎች ደስ እንዲላቸው ብለህ ሳይሆን ትክክለኛ እና አንተ ያመንክበት ነገር ስለሆነ ይሁን።

በዚህ ምድር ላይ ምንም አይነትጻዲቅ ሰው ብትሆን እንኳን ሁሉንም ሰዎች ማስደሰት አትችልም።

ስለዚህ የምታደርጋቸው ነገሮች ከህሊናህ ጋር እስከተስማሙ ድረስ በቂ ነው።

ለሰው ሳይሆን ለህሊናህ ኑር።


የውሸት ደስታን አትፈልግ!"
<>~ ~<> <>~ <>
በውሸት ደስታና በእውነተኛ ደስታ መካከል ትልቅ ልዩነት አለ።

የውሸት ደስታ፤ ጊዜያዊ በሆኑና ከውጪ በምናገኛቸው ነገሮች የሚመጣ ነው።

ሃዘናችንን ለጊዜው የሚጋርድ ጊዜያዊ ማስታገሻ፤ እውነተኛ ደስታ ግን ሃሳባችን፤ አላማችን፤ ምግባራችን ሲጣመር የሚፈጠር ስሜት ነው።

ሃዝን እና መከራችንን ሳንደብቅ የምንጽናናበት ደስታ፤

"ለሁሉም ሰው ቅንሁን
<>~ ~<> <>~ <>

ከመንገደኛው አንስቶ እስከ ቅርብ ወዳቻችን ድረስ፤ ሰዎች በኛ ላይ ትልቅ አስተዋጽዎ አላቸው።

በህይወትህ የምታሰፍራቸው ነጥቦች ሁሉ በኋላ ላይ ተያይዘው መስመር መስራታቸው አይቀርም።

የተናቀው ድንጋይ የማዕዘን ራስ ይሆናል ተብሏልና ሰዎችን አትናቅ።

በየትኛውም አጋጣሚ ለምታገኛቸው ሰዎች ትክክለኛውን ነገር አድርግ፤

"መለወጥ የማትቻለውን ነገሮችን ተቀበላቸው!"
<>~ ~<> <>~ <>
ብዙሰዎች ጭንቀት ውስጥ የሚገቡት መለወጥ የማይችሏቸውን ነገሮች ለመለወጥ ስለሚጥሩ ነው።

ምንም እንኳን በህይወታችን ውስጥ አብዛኛው ነገሮች ላይ ስልጣን ቢኖረንም፤ መለወጥ የማችላቸው ነገሮች አሉ።

ከአቅምህ በላይ በሆኑ ነገሮች እራስህን አታስጨንቅ።

ከአቅምህ በላይ የሆነውን ነገር ለአምላክህ ለፈጣሪ ስጠው።


"የራስህ እውነተኛ ወዳጅ ሁን!"
<>~ ~<> <>~ <>
ምንም እንኳን ሰዎች በአንተ ቢያምኑብህም እና ቢመኩብህም ፤ አንተ በገዛ እራስህ ካላመንክ ህይወትህ ምንም ዋጋ የለውም።

ከሰዎች ፍቅር በላይ የራስህ ፍቅር ወሳኝ ነው።

የሚገርመው ሰዎች እራሱ ሊወዱህ የሚችሉት አንተ በመጀመሪያ እራስህን መውደድ ስትችል ነው።

እራስህን በደንብ ተንከባከበው።

ሲያጠፋ ይቅር በለው፤ ሲደክም አበርታው፤ ሲሳካለት አሞካሸው።

ላንተ ካንተ የቀረበ ማን አለህና?


"መልካም አስብ መልካም ተናገር!"
<>~ ~<> <>~ <>
በመጀመሪያ ሰው ያስተሳሰቡ ውጤት መሆኑን እመን፤ አሁን የምንኖረው ህይወት ያመለካከታችን እና ያስተሳሰባቸን ውጤት ነው።

ይህን ካወቅክ አስተሳሰብህን በጥንቃቄ አጢነው።

ደስተኛ ለመሆን የተመረጠ አስተሳሰብ ሊኖርህ ይገባል።

"ለምን እንደምትኖር እወቅ!"
<>~ ~<> <>~ <>
ህይወት ማለት የተሰጠህን ሃላፊነት ለመጨረስ የተሰጠችህ ጊዜ ናት።

ሃላፊነትህ ምንድንነው? በህይወትህ ማድረግ የምፈልገው ነገር ምንድን ነው? መልሱ ካወቅክ ለህይወት ያለህ አመለካከት ይለወጣል።

"እራስህን ከሌላ ሰው ጋር አታፎካክር!"
<>~ ~<> <>~ <>
ሁላችንም እንደ አሻራችን ሁሉ ባህሪያችን እና ፍላጎታችንም በጣም ይለያያል።

ደስታን ከሚያጠፉ ምክንያቶች አንደኛው እራስን ከሰው ጋር ማፎካከር ነው።

አሳ ደስታዋን እንደ ወፍ በሰማይ ልፈልግ ብትል፤ወፍ ደግሞ እንደ አሳ በውሃ ውስጥ ልፈልግ ብትል፤ ሁለቱም ሳይደሰቱ ይቀራሉ።

ስለዚህ ደስታህን በራስህ መለኪያ ለካው።

አንተ በሌሎች ስትቀና ሌሎችም ባንተ እንደሚቀኑ እወቅ።

አትኩሮትህ ባለህ ነገር ላይ አድርግ!"
<>~ ~<> <>~<>

የጎደለህ ምንድን ነው?

ያለህስ ምንድን ነው?

ብታመዛዝነው የቱ ይበልጣል?

ብዙዏቻችን ሃሳብ እና አትኩሮቶቻችን በሌለን ነገር ላይ ስለሆነ፤ ያለንን ነገር ሳንጠቀምበት እንቀራለን።

ደስተኛ ለመሆን ሁሉም ነገር ሊኖርህ አይገባም።

በደንብ ካስተዋልከው አሁን ያለህ ነገር ደስተኛ ለመሆን በቂ ነው። ምክንያቱም አንተ ያለህን የሚመኙ ምስኪኖች ብዙ ናቸው እና ።።።።

መልካም ጁምዓ

@Achirlebwold
319 views10:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-13 13:49:39
283 views10:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-13 13:49:03
" ️በዚህ ምድር ላይ ሌላውን ለመምሰል እንደመሞከር ከባድ ነገር ምን አለ?

️ሌላውን ለመምሰል ስትሞክር፤ #የምትጣላው ከሰው ጋር ሳይሆን ከገዛ እራስህ ጋር ነው።

️እናም እራስህን አታስቀይመው፤ እውነተኛ ወዳጆችህ አንተን ባንተነትህ ይቀበሉሃል…..ከምንም በላይ እራስህን በመሆን ከራስህ ጋር #ሰላም ፍጠር፤

"ሁሉን ለማስደሰት አትሞክር!"
<>~ ~<> <>~<>

አንድ ነገር ስታደርግ ሰዎች ደስ እንዲላቸው ብለህ ሳይሆን ትክክለኛ እና አንተ ያመንክበት ነገር ስለሆነ ይሁን።

በዚህ ምድር ላይ ምንም አይነትጻዲቅ ሰው ብትሆን እንኳን ሁሉንም ሰዎች ማስደሰት አትችልም።

ስለዚህ የምታደርጋቸው ነገሮች ከህሊናህ ጋር እስከተስማሙ ድረስ በቂ ነው።

ለሰው ሳይሆን ለህሊናህ ኑር።


የውሸት ደስታን አትፈልግ!"
<>~ ~<> <>~ <>
በውሸት ደስታና በእውነተኛ ደስታ መካከል ትልቅ ልዩነት አለ።

የውሸት ደስታ፤ ጊዜያዊ በሆኑና ከውጪ በምናገኛቸው ነገሮች የሚመጣ ነው።

ሃዘናችንን ለጊዜው የሚጋርድ ጊዜያዊ ማስታገሻ፤ እውነተኛ ደስታ ግን ሃሳባችን፤ አላማችን፤ ምግባራችን ሲጣመር የሚፈጠር ስሜት ነው።

ሃዝን እና መከራችንን ሳንደብቅ የምንጽናናበት ደስታ፤

"ለሁሉም ሰው ቅንሁን
<>~ ~<> <>~ <>

ከመንገደኛው አንስቶ እስከ ቅርብ ወዳቻችን ድረስ፤ ሰዎች በኛ ላይ ትልቅ አስተዋጽዎ አላቸው።

በህይወትህ የምታሰፍራቸው ነጥቦች ሁሉ በኋላ ላይ ተያይዘው መስመር መስራታቸው አይቀርም።

የተናቀው ድንጋይ የማዕዘን ራስ ይሆናል ተብሏልና ሰዎችን አትናቅ።

በየትኛውም አጋጣሚ ለምታገኛቸው ሰዎች ትክክለኛውን ነገር አድርግ

"መለወጥ የማትቻለውን ነገሮችን ተቀበላቸው
291 views10:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ