2022-02-20 11:09:28
የአዕምሮ ጭንቀት ያለበት ሰው የሚሰማው ስሜት
በሥነ አዕምሮ ክልል ውስጥ "በሽታ" የሚለው ሀሳብ ብዙ ክርክር ፈጥሯል። "የአዕምሮ በሽታ" የሚለውን ሀሳብ ለመቀበል ብዙ ሰዎች ያስቸግራቸዋል። ምክንያቱም "አዕምሮ" የሚለው ቃል የሰውየውን ልምምድና አስተሳሰቡን የሚጠይቅ በመሆኑ ፣ ያም ግላዊ የሆነውን የሰው ሕይወት የሚነካ ስለሆነ ነው። ሁለተኛው ቃል ፣ ማለትም "በሽታ" ተጨባጭ በሆነ ሁኔታ መለካት አይችልም በሚል ሀሳብ ነው።
የአዕምሮ ጭንቀት በሽታ መሆኑንና አለመሆኑን ለመረዳት ከዚህ በታች ያሉትን
ሦስት ጥያቄዎች መጠየቅ ይረዳናል። ይኸውም
1ኛ፣ የአዕምሮ ጭንቀት ያለበት ሰው የሚሰማው ልዩ የሆነ ስሜት አለ ወይ? የአዕምሮ
ጭንቀትን ፣ ጊዜያዊ የሆነ "ትካዜ"፣ ወይንም "መጨፍገግ" ብቻ እንደሆነ አድርገን ከወሰድነው ፤ በእርግጥም የአዕምሮ ጭንቀት "በሽታ ነው" አንልም። ይሁን እንጂ የአዕምሮ ጭንቀት የደረሰበት ሰው ከጊዜያዊ ትካዜና ከመጨፍገግ ስሜት በላይ ብዙ የተለያዩ የስሜት ለውጦች ይታዩበታል።
በአዕምሮ ጭንቀት ውስጥ ያለ ሰው የሚታይበትን የስሜት ለውጦች በሌላ ፅሁፍ በሰፊው የዘረዘርናቸው በመሆኑ እነርሱን መመልከት ይጠቅማል።
"የስኳር በሽታ" ያለበት ሰው ብዙ ውሃ እንደሚጠጣው ፣ ክብደት እንደሚቀንስና ቶሎ ቶሎ ሽንት እንደሚያሸናው ሁሉ ፣ በአዕምሮ ጭንቀት የተያዘ ሰውም ስለ ራሱ የዝቅተኛነት ስሜት፣ የጉልበት ማነስ ፣ በአንድ ነገር ላይ ማተኮር እንደማይችል ተገንዝበናል።
የሥነ አዕምሮ አዋቂ በአዕምሮ ጭንቀት የተያዘው ሰው የሚሰማውን የስሜት መለዋወጥ ሲያይ የመጀመሪያውን የምርመራ ደረጃ አጠናቀቀ ማለት ነው።
2ኛ፣ ሰው በአካሉ ላይ በሽታ እንዳለበት ማወቅ ይቻላል?
"የስኳር በሽታ" እንዳለበት ሰው የአዕምሮ ጭንቀት ያለበትም ሰው የትኛው የሰውነት ክፍሉ እንደታመመ ወይንም ለጭንቀቱ ምክንያት እንደሆነ ማወቅ ይቻላል?
እዚህ ላይ በአዕምሮ ጭንቀት ውስጥ የሚያልፉ ሰዎች ሁሉም አንድ ዓይነት የሰውነት ለውጥ ይታይባቸዋል ብሎ መናገር ያዳግታል። አንዳንዶቹ ሚዛናቸውን ጠብቀው መራመድ ያቅታቸዋል።
ይህ ከሆነ በሰውነታቸው ውስጥ ያለው የንጥረ- ነገሮች (ኬሚካልስ) መዛባት እንዳለ ስለሚታወቅ ፣ እንዲህ ዓይነቶቹን ሰዎች የአዕምሮ ጭንቀታቸውን በመድሀኒት መቋቋም ወይንም ማከም ይቻላል።
የአዕምሮ ጭንቀት ያለበት ሰው በሰውነቱ ውስጥ የሚያሳየው መዛባት ምን እንደሆነ ለማወቅ በቅርቡ በተደረገው ልዩ ጥናት የተገኘ አዲስ ሀሳብ አለ።
ይኸውም የሰውን አንጎል በፎቶግራፍ የሚያሳይ መሣሪያ ፤ (pet scanner's) አንጎል ያለበትን ይዞታ ከማሳየቱ አልፎ ፣ አንጎል ምን ያህል ግሉኮስ እንደሚጠቀምና፣ ምን ያህል ኦክስጅን እንዳቃጠለ፣ ጨምሮ ያሳያል። የአዕምሮ ጭንቀት ያለባቸው ሰዎች በዚህ ከላይ በገለጽነው መሣሪያ አንጎላቸው ሲታይ ፤ በተለያዩ የአንጎል ክፍላቸው ላይ ጤናማ ያልሆነ እንቅስቃሴ እንዳለ ያሳያል።
አሜሪካ ውስጥ "በደም መርጋት በሽታ" (stroke) ተመተው ከተረፉ ሰዎች መካከል ቢያንስ ቢያንስ ከመቶ ሃያ አምስቶቹ በአዕምሮ ጭንቀት በሽታ ይያዛሉ።
እኛ ሀገር መረጃዎችን በስነስርዓት ለማግኘት ይከብዳል
"ከደም መርጋት በሽታ" (ከስትሮክ) በኋላ በሰዎች ላይ የሚደርሰው የአዕምሮ ጭንቀት ዋና ምክንያት የአንጎል ክፍላቸው መዛባት እንደሆነ ተረጋግጧል።
እንዲህ እስካሁን እንዳየነው በአዕምሮ ጭንቀት የተያዘ ሰው ፤ የተለያየ የስሜት ለውጥና ፣ እንዲሁም አንዳንዶቹ በአንጎላቸው ውስጥ ያለው ቲሹ መታወክ እንደሆነ ተገንዝበናል።
3ኛ፣ የአዕምሮ ጭንቀትን ያስከተለው ምክንያት ምን እንደሆነ እናውቃለን?
ለዚህ ጥያቄ መልስ ለመስጠት መጀመሪያ የአዕምሮ ጭንቀት በሽታው በዘር የመጣ ወይንም በዘር ያልመጣ መሆኑን ለይተን ማወቅ ያስፈልጋል።
በዘር የሚመጣ (deoxyriborucleic acid - DNA) ከአባት ወደ ልጅ ከዚያም ወደ ልጅ ልጅ የሚተላለፍ በሽታ አለ።
በሰው አካል ውስጥ 46 ክፍሎች የያዙ "ክሮሞሶምስ" እየተባሉ የሚጠሩ ነገሮች እንዳሉ የታወቀ ነው። ክሮሞሶምስ ደግሞ የተገነባው "ጂንስ" እየተባሉ በሚጠሩ ነገሮች ነው።
የአዕምሮ ጭንቀት በሚያይልበት ቤተሰብ ውስጥ ፣ በሁሉም የቤተሰብ አባል ውስጥ ፣ አንድ ዓይነት DNA አላቸው።
ይህም ጂን እንዳለበን ግልጽ ነው። በአሁኑ ጊዜ በጥናትና ምርምር ውስጥ ያለው ፣ የትኛው "ጂን" እንደሆነ ለይቶ ለማወቅና እንዲሁም የአንጎልን አቋም ምን ያህል እንደሚነኩት ለመረዳት ይቻላል።
በዘር የማይመጣ የአዕምሮ ጭንቀት በሽታ ደግሞ የአመጣው ምክንያት ብዙ ነው። ከደም መርጋት (ከስትሮክ) በኋላ የሚደርስ የአዕምሮ ጭንቀት ፣ ምክንያቱ "የደም ግፊት" (ብለድ ፕሬዦር) ነው።
የብዙዎቹ ግን ምክንያታቸው ሙሉ በሙሉ የታወቀ አይደለም። እንግዲህ "የአዕምሮ ጭንቀት" በሽታ መሆን አለመሆኑን ጠይቀን የምንረዳበት ብዙ መመሪያዎች እንዳሉ ተረድተናል።
"የስኳር በሽታ" ያለበት ሰው ፤ በደሙ ውስጥ ያለውን ስኳር በራሱ ሀይል መቆጣጠር እንደማይችለው ሁሉ ፣ በአዕምሮ ጭንቀት ውስጥም የሚያልፍ ሰው የሚሰማውን ልዩ ልዩ ስሜቶች እንዳይሰማው ለማድረግ አይችልም።
ስለዚህ በአዕምሮ ጭንቀት የተያዘ ሰው የራሱ ችግር (ጥፋት) ድክመት ነው በማለት ሊፈረድበት አይገባም።
የሰው ብርታት በዘር የሚወርሰውን ሁኔታ ሊለውጥ አይችልም።
የአዕምሮ ጭንቀትን ባህሪ ማወቅ ፣ በሽታው የያዘውን ሰው እንደ "ዕብድ" እንዳይታይ ወይንም እንዳይቆጠር ይረዳል።
በዚህ በሽታ ሳይያዙ የሚቀሩ ሰዎች ከሌሎች የበለጠ ብርቱዎች ስለሆኑ አይደለም።
ሁሉም ሰው ለዚህ በሽታ የተጋለጠ ነው። ስለዚህ በበሽታው የተያዙትን ሰዎች ልዩ ስም መስጠት ተገቢ አይደለም።
የአዕምሮ ጭንቀት "በሽታ" ስለሆነ ፤ ህክምና ያስፈልገዋል። በአዕምሮ ጭንቀት የተያዙ ሰዎች በህክምና ከመቶ ሰማኒያዎቹ መዳን ሲችሉ ፣ ከመቶ 20ዎቹ ግን አይድኑም።
ማወቅ የሚያስፈልገን የአዕምሮ ጭንቀት አንድ ጊዜ ብቻ መጥቶ የሚሄድ አለመሆኑን ነው።
ከዚህ ሌላ መገንዘብ የሚያስፈልገን ነገር ቢኖር በአዕምሮ ጭንቀት የተያዘ ሰው እራሱን የመግደል ዝንባሌ እንዳለው ነው።
የሰው ተፈጥሮአዊ ባህሪ ከአዕምሮ ጭንቀት ጋር የሚኖረው ግንኙነት
#ይቀጥላል ሌሎችም ሼር በማድረግ ግንዛቤ ይፈጠሩ
@achirlebwold
ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!
ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን
2.1K views08:09