Get Mystery Box with random crypto!

ኩን ሰለፍያ አለልጀዳ አሰለፍይ መነሀጅ

የቴሌግራም ቻናል አርማ abuteqiypomechannel — ኩን ሰለፍያ አለልጀዳ አሰለፍይ መነሀጅ
የቴሌግራም ቻናል አርማ abuteqiypomechannel — ኩን ሰለፍያ አለልጀዳ አሰለፍይ መነሀጅ
የሰርጥ አድራሻ: @abuteqiypomechannel
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.14K
የሰርጥ መግለጫ

📚ይህ ቻናል
ግጥሞችን፣
ቁርዓንና ሀዲስ፣
ደርሶችን፣
ሙሀደራ
ሊንክ፣የመሳሰሉትንበኩን ሰለፍያ አለልጀዳ አሰለፍይ መነሀጅ ስር በተከፈቱት ቻናሎች ውስጥ የሚተላለፉ መልዕክቶች ከየሁሉም የተሰባሰቡ ትምህርቶች የሚላክበት ቻናል ነው።
አስተያየት 📞 @CommentAnd1_bot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-30 16:55:12 ፍቅርን በትዳር ውስጥ:
#እጠብቅሻለሁ

ምንም ነገር ብሆን ፈተና ቢበዛ፣
አላህ የፈቀደው እለት እስኪመጣ፣
እጠብቅሻለሁ ጣጣም አላባዛ፣



#ከተራራው_ማዶ

ከዚያ ከወዳኛው ከተራራ ማዶ፣
ከአድማሱ ሰፈር የሩቅ ሰውን ወዶ፣
ትዳር ሲመሰረት በፍቅራት ደምቆ፣
ይኖራል ያቤቱ ከጨለማ ወጥቶ።



ቆይ ቆይ ቆይ
#ሚስት በሏን ማወደስ የለባ ትም ያለው ማነው


የህይወት አካሌ
የግማሿ ግማሽ የሲሶዋ ሲሶ፣
የህይወት አካሌ ዋልታና ምሰሶ፣
ከሀራም ያ"ራከኝ የትዳር ቀን ደርሶ፣
ሁሌ እወድሀለሁ ልቤ ፍቅር ይዞ።

ፍቅርህ የኔ ፍቅር ሁለቱም አብቦ፣
በአይኔ ባየሁት አበባው አፍርቶ።


#ትዳር_እንድህ
እንደቀልድ


" አንዳንድ ወንዶች ትዳር እንደ ግሩፕ መስሏቸው ጆይን (join) ብለው ይገቡና ከወራቶች በኋላ ሊፍት ብለው ይወጣሉ።" ይላል

ያነበብኩት ፖስተር።

ትዳር እንድህ እንደ ቀልድ ከተያዘማ፣
አወ ሁሉም ቀሪ ነው ሳይ ወጣ ማማ።


#ግን_ትዳር
የነብያት ሱና
የአላህ ገፀበረከት
የፍቅር ዋልታ ማገር፣
የኢማን ማሟያ መስመር፣
የልጆች ማፍሪያ ሰፈር፣
የህይወት መምሪያ ቀመር፣

መሆኑን ለተረዳ የትዳር ጣእም ለናፈቀው፣
ከላይ ያለው አበባል ለሱ ምንም አይገልፀው።



#አረንጓዴ_አሻራ


"ለባሏ አረንጓዴ አሻራ ያስቀመጠች ማለት ጥብቅ ሆና የተገኘች እንስት ናት።"

#ከአንዲት_ሰለፍይ_እንስት_ያገኘሁት ፁሁፍ #አላህ_ይጠብቃት

እርግጥም እውነት አለች
ነፍሷን ለአላህ የገበረች፣
ከሰይጣን ጉትጎታ የራቀች፣
ከስሜት አሉቧልታ የተጥራራች፣
ጥብቅ ሆና በጥብቅነት የኖረች፣
የማይናወጥ ክብር ከባሏ ልብ የፃፈች፣
ከአላህ ዘንድ ተወዳጂ ሆና ከሰው ዘንድ የተወደደች፣
እሷናት የእውነትም አረንጓዴ አሻራ ያስቀመጠች።



#በሳር_ቤት_ጎጆዬ



እንደዘመነኛው ቪላቤት ባይኖረኝ፣
ኮከብ የሚመስለው መብራት ባይገባልኝ፣
ሳሎን አልጋቤቱ የሸዋር ባይኖረኝ፣
እቃቤቱ ሳይኖር ክፍሌ እንኳ ብጠበኝ፣

ከተወሂድ ከሱና ከዲን ጋር የኖረች፣
የአይን ማረፊያ እንቁ ሚስት ካለች
የሳር ቤት ጎጆዬ ምንም አትበድለኝ።

ያ የአላህ ባሪያ እንቁው አሽረፈል ሀልቅ፣
(ሱለሏሁ አለይሂ ወሰለም)
ሲኖሩ እንዴት ነበር ትዳራቸው ሲደምቅ

ህይወታቸው ሁሉ በመብቃቃት ሲዘልቅ፣
እስቲ ዘወር ብሎ ይሻላል መጠየቅ፣
እነዚያ ሶሀቦች የኖሩትን ህይወት፣


ሰለፍይ እኮነኝ ብለን ለምናስብ ፣
የእውነት እንሁን እንተግብረው ከልብ፣
ነጃ እንወጣለን በጋብቻ ሰበብ።

=========================

አቡ ተቅይ ቃዒድ
========================
ኩን ሰለፍያ አለልጀዳ አሰለፍይ መነሀጅ ኦፊሲላዊ ቻናል
https://t.me/AbuTeqiyPomeChannel

ግሩፕ
https://t.me/PomeChannelGroup

ኩን ሰለፍያ አለልጀዳ አሰለፍይ መነሀጅ ኦፊሲላዊ ፔጅ - Home
https://m.facebook.com/KunSelefiyeAllMineOfIniformation/?ref=bookmarks

የፌስቡክ ግሩፕ
https://facebook.com/groups/717908414984387/

105 viewsአቡ ተቅይ ቃዒድ, 13:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 11:25:58 በሀገሬ ምድር በርካታ ወጣ ውረዶች እየተስተናገዱ ነው።


አላህ መጨረሻችንን ያሳምርልን።
ወገን በዱዓችሁ አትርሱን።


አላህ ከመጣብን በላዕ እንዲያተርፈን ዱዓ አድርጉልን።
120 viewsአቡ ተቅይ ቃዒድ, edited  08:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 06:29:10 ግሩፕ
https://t.me/PomeChannelGroup

ኩን ሰለፍያ አለልጀዳ አሰለፍይ መነሀጅ ኦፊሲላዊ ፔጅ - Home
https://m.facebook.com/KunSelefiyeAllMineOfIniformation/?ref=bookmarks

የፌስቡክ ግሩፕ
https://facebook.com/groups/717908414984387/

129 viewsአቡ ተቅይ ቃዒድ, 03:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 06:29:10 ጃዕፈር ኢብን አቡጧሊብ ረዲየሏሁ ዐንሁ
┈┈•••✿❒ ❒✿•••┈┈

ክፍል አንድ
✿•••✿•••✿

《ጀዕፈርን፥ ጀነት ውስጥ ሁለት በደም የደመቀ ክንፎች ባለቤት ሆኖ አየሁት።》
« ነብዩ ሙሐመድ ﷺ»

ምንም እንኳን በቁረይሾች ታላቅ የክብር አይን ቢታዩም የረሱል ﷺ አጎት አቡ-ጧሊብ በሀብት ረገድ ድሀ ነበሩ።

ቤተሰባቸውን መቀለብ የተሳናቸው የብዙ ልጆች አባት የሆኑት አቡጧሊብ ምድረ ዓረቢያን ድርቅ ሲመታት ችግሩ ተባባሰባቸው። ሰብሎችን ያጠፋውና ከብቶችን የፈጀው ረሃብ፥ ህዝቡ ከሞት ለማምለጥ ሲል አጥንት እንዲቆረጥም አስገድዶት ነበር። ነብዩ ረሱል ﷺ ለነብይነት ገና ባልታጩበት በዚህ ቀውጢ ወቅት አጎታቸውን አባስን «የወንድምህ የአቡ-ጧሊብ ቤተሰቦች ብዙ ናቸው። ሰው በረሃብ እያለቀ ስለሆነ የተወሰኑትን በመውሰድ እንርዳው» በማለት ሀሳብ አቀረቡ።

አባስም በሀሳቡ ተስማማ አባስ ከረሱል ﷺ ጋር ወደ አቡ ጧሊብ ሄደው ሀሳባቸውን አቀረቡ። አቡ ጧሊብ የዓሊይን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) ታላቅን አቂልን ትተው ከሌሎቹ መርጠው መውሰድ እንደ ሚችሉ ነገሯቸው።

ረሱል ﷺ #ዓሊይን ረ.ዐ አባስ ደግሞ #ጃዕፈርን ረዲየሏሁ ዐንሁን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለመቀላቀል ወሰዷቸው።

ከሃሺም ጎሳ #አምስት ሰወች ነብዩ ሙሀመድን ﷺ በመልክ በጣም ይመስሉ ነበር ይባላል።

ያጎታቸው ልጆች #አቡሱፍያን ኢብን አል-ሃሪስና #ቁሳም ኢብን አል አባስ፤ የኢማሙ ሻፊኢይ አያት #አስ-ሳኢብ ኢብን ኡበይድ እንዲሁም ከሁሉም በጣም የሚመስሏቸው የልጃቸ ው ልጅ #ሐሰን ኢብን ዓሊይና የአጎታቸው ልጅ #ጀዕፈር ኢብን አቡ ጧሊብ ረዲየሏሁ ዐንሁም ነበሩ።

የትዳር እና የኢስላም ህይወት
┈┈•••✿❒ ❒✿•••┈┈

ጀዕፈር ረዲየሏሁ ዐንሁ በወጣት እድሜው #አስማ ቢንትዑመይስን ረዲየሏሁ ዐንሀ አግብቶ ከአባስ በመለየት ጎጆ መሰረተ። በአቡበክር አስ-ሲዲቅ ረዲየሏሁ ዐንሁ አማካኝነት ከሚስቱ ጋር ኢስላምን በመቀበል ከመጀመሪያወቹ ሙስሊሞች ሆነ። የጀነት መንገድ በሾክ መሞላቷን የተረዱት ጀዕፈርና ሚስቱ ረዲየሏሁ ዐንሁም በቁረይሽ የሚደርስባቸውን ጭካኔና ግፍ በትዕግስት ሊወጡት ቢሞክሩም ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ የመጣው የ ቁረይሽ ሴራ ከአቅማቸው በላይ በመሆኑ ፦
«ጌታችን አላህ አንድ ነው» ስላሉ ብቻ በደል እየተፈፀመባቸው ያሉት ንፁሃን ሰዎች ዕጣ ያሳዘናቸው ነብይ ﷺ ወደ ሀበሻ እንዲሰደዱ ትዕዛዝ ሰጡ።

ስደት ወደ ሐበሻ
┈┈•••✿❒ ❒✿•••┈┈

በጀዕፈር ረዲየሏሁ ዐንሁ መሪነት ወደ አቢሲኒያ (ኢትዬጵያ) የመጀመሪያው ስደት ተደረገ። በፍትሀዊው የኢትዮጵያ ንጉስ ነጃሺ ጥላ ስር በመሆን ሃይማኖታ ቸውን በነፃነት በመተግበር አላህን የመገዛትን ጣዕም ሊቀምሱ ቻሉ። የስደተኞቹ በሰላም መኖር የእግር እሳት የሆነባቸው የቁረይሽ ሹማምንት ወደ መካ የሚመልሱባቸውን መንገድ ያውጠ ነጥኑ ጀመር።

ለዚህ ተግባር የቁረይሽ ግፈኞች #አምር ኢብን አልአስና #አብዱላህ ኢብን አቢ ራቢያን በመወከል ከበርካታ ስጦታወች ጋር ወደ ንጉሱና ጳጳሳቱ ላኩዋቸው።

ኢትዮጵያ እንደደረሱ ለስጦታ ያመጧቸውን ንብረቶች ለጳጳሳቱ በመለገስ «በንጉሱ መሬት የሚንቀሳቀሱ አመፀኛ ወጣቶች አሉ። በአባቶቻቸው ሀይማኖት ላይ ያፌዛሉ፣ ይኮንኑታልም። በህዝባችን መካከል ሁከትና መከፋፈልን ፈጥረዋል። ንጉሱን ስናነጋግር ስለ ሃይማኖታቸው ምንነት ሳይጠይቋቸው እንዲያስረክቡን ጎትጉቱልን። የተከበሩት የህዝባችን መሪወች ስለ እነሱም ሆነ ስለ ሀይማኖታቸው ከሁሉም በላይ ያውቃሉ» አሏቸው። ጳጳሶቹም ተስማሙ።

አምርና ዐብደላህ ብስጦታቸው ለተደሰተው ነጃሽ 《ንጉስ ሆይ! ርኩሳን ወጣቶች ከኛ አምልጠው ወደ ግዛተዎ መጥተዋል። እኛም እርሶም የማናውቀውን ሃይማኖት ይከተላሉ። በወላጆቻቸው እና በህዝባቸው ላይ ያመፁ አፈንጋጮች እንድትመልሱልን የተከበሩ መሪዎቻችን ልከውናል።» ሲሏቸው ንጉሱ ወደ ጳጳሳቱ ዞር ብለው ሲመለከቷቸው።

«ንጉስ ሆይ! እውነታቸውን ነው የተንናገሩት። በህዝባቸው ላይ ምን ፈፅመው እንደመጡ ስለሚያውቁ ለፍትሀዊ ፍርድ ወደነርሱ ይላኩዋቸው» አሉ።

በአስተያየታቸው የተቆጡት ንጉስ ነጃሽ «በፈጣሪ ይሁንብኝ! ለምን እንደተወነጀሉ እራሴ ሳላጣራ አሳልፌ አላስረክባቸወም። እነዚህ ሁለት ሰዎች የሚሉት እውነት ከሆነ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ። ካልሆነ ግን የእኔን ጥበቃ እስከፈለጉ ድረስ በኔ ምድር ይኖራሉ።» በማለት አስደነገጧቸው።

ንጉሱ ሙስሊሞቹ ለችሎት እንዲቀርቡ
አዘዙ። ሙስሊሞቹ ከመሄዳቸው በፊት እነሱን ወክሎ #ጀዕፈር ኢብኑ አቢ-ጧሊብ ረዲየሏሁ ዐንሁ ብቻ እንዲናገር ተስማሙ በንጉሱ ቤተ መንግስት ጳጳሳቱ የሚያምር አረንጓዴ ልብስና ማራኪ ቆብ ደፍተው ከንጉሱ ወንበር ግራና ቀኝ ቁጭ ብለዋል ሙስሊሞቹ ሲገቡ ቁረይሾቹ ቦታቸውን ይዘው ነበር። ንጉሱ መጡ።

ቀሳውስት፣ ጳጳሳት፣ ቁረይሽ ወዘተ.. ከሙስሊሞች በስተቀር ሁሉም ለንጉሱ አጎነበሱ።

ንጉሱ ሙስሊሞቹን ለምን የክብር ሰላምታ እንዳልሰጡ ሲጠይቋቸው

«እኛ ለአላህ እንጅ ለሌላ የማናጎነብስ ህዝቦች ነን። »በማለት ነበር በታሪክ የማይረሳውን ቃል ጀዕፋር ረዲየሏሁ ዐንሁ የመለሱት።

ንጉሱ በመገረም «ለመሆኑ ከህዝቦቻችሁ ጋር ሆድና ጀርባ ያደረጋችሁ እምነት ምን አይነት ነው? ወደ እኔ ወይም ወደ ሌላ ህዝቦች ሃይማኖት ለምን አልገባችሁም?» በማለት ጠየቁ።

ጀዕፈር ረዲየሏሁ ዐንሁ ወደፊት ቀረብ በማለት በቅን ልሳን የመካ ሰውን ሁኔታ፣ የኢስላምንና የረሱልን ﷺ ሚና ቁልጭ አድርጎ አቀረበ።


እንዲህ ነበር ያለቸው፦ «ንጉስ ሆይ! በድንቁርናና በምግባረ ብልሹነት የተዘፈቀን፣ ጣዖት አምላኪ፣ የሞተ እንስሳ ተመጋቢ፣ አሰቃቂ እና አፀያፊ ስራወችን የምንፈፅም፣ ዝምድናን የምንቆርጥ፣ እንግዳ የምናስከፋ ህዝቦች ነበርን። ኃይለኛውም ደካማውን የሚበዘብዝ በት ሁኔታ ነበር። በዚህ ሁኔታ ላይ እያለን አላህ ማንነቱን፣ ቤተሰቡንና እውነተኝነቱን የማንክደው መልእክተኛ ላከልን።
እሱም ፦ እውነትን ብቻ እንድንናገር፣ ውለታችንን እንድናከብር፣ ለዘመድ መልካም እንድንውል፣ ጎረቤቶቻችንን እንድንረዳ፣ ከተከለከሉ ነገሮች ሁሉ እድንርቅ፣ ያለ አግባብ ደም ከማፍሰስ እንድንታገድ፣ ከብልግና ተግባሮች እንድንርቅ፣ በውሸት እንዳንመሰክር፣ የሙት ልጅ ሀብት አጭበ ርብረን እንዳንወስድ፣ የንፁህ ሴቶችን ስም እንዳናጠፋና በሀሜት እንዳንለውስ፣ በአላህ ሳናጋራ እሱን ብቻ እንድናመልክ፣ ሶላት እንድንሰ ግድ...አዘዘን። ያዘዘንን በመስራት፥ ከከለከለን ነገር በመከልከል ከእሱና ከአላህ በመጣልን መልዕክት አመን።»

« ክቡር ንጉስ ሆይ! ህዝባችን አሰቃየን ሃይማኖታችንን ክደን ወደድሮው አስፀያፊ ጣዖት አመልኮት እንድንመለስ ለማድረግ አሰቃቂ ቅጣቶች ፈፀመብን። ጨቆነን። ህይወታችንን መምራት አቃተን።የእምነታ ችንን ግዴታወች ማከናወን ተሳነን ለዚህ ነው ሀገራችንን ጥለን በመሰደድ ከሁሉም በፊት እርሰወን መርጠን በመሬትዎ በፍትህና በሰላም ለመኖር የመጣነው።»

ንጉሱ በገለፃው ተማርከዋል። ቢሆንም ነገሩ በዚህ አልተገታም፦

===========
ኢንሻኣላህ ይቅጥላል..........
=========================

አቡ ተቅይ ቃዒድ
========================
ኩን ሰለፍያ አለልጀዳ አሰለፍይ መነሀጅ ኦፊሲላዊ ቻናል
https://t.me/AbuTeqiyPomeChannel
105 viewsአቡ ተቅይ ቃዒድ, 03:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 06:04:54 አሰለሙአለይኩም ወረህመቱሏሂ ወበረካትሁ
ይህ የኩን ሰለፍያ አለልጀዳ አሰለፍይ መነሀጅ ኦፊሲላዊ ግሩፕ ነው።

በአድስ መልክ

ለቻናል እና ለግሩፕ አባላቶች የቀጥታ ስርጭት የሚተላለፉ ፕሮግራሞች

#ጁሙዓ
ቁርዓን እና ሐዲስ
ሽርክና ቢዲዓ
#ቅዳሜ
ፈትዋ
አፕልኬሽንና ፒዲኤፍ
#እሁድ
ሙሀደራ
የሱና ሊንኮች
#ሰኞ
ግጥም
ማስታወቂያ
#ማክሰኞ
ትዳር
ሃያቱ ሶሃባ
#ሮብ
የኪታቦች ደርስ
ፊርቃዎች
#ሀሙስ
ጥያቄ እና መልስ ከዋናው ማሰራጫ
የሳምንቱ የመወያያ ጊዜ ቀጥታ በመወያያ ግሩፕ

#የሰዓቱ_አጠቃቀም
እንደ አስፈላጊነቱ እና አንደየሁኔታው ከተመቻቸ ከጧቱ 12:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 4:30 ድረስ ይሆናል ኢንሻአላህ።
=========================
አቡ ተቅይ ቃዒድ
========================
ኩን ሰለፍያ አለልጀዳ አሰለፍይ መነሀጅ ኦፊሲላዊ ቻናል
https://t.me/AbuTeqiyPomeChannel

ግሩፕ
https://t.me/PomeChannelGroup

ኩን ሰለፍያ አለልጀዳ አሰለፍይ መነሀጅ ኦፊሲላዊ ፔጅ - Home
https://m.facebook.com/KunSelefiyeAllMineOfIniformation/?ref=bookmarks

የፌስቡክ ግሩፕ
https://facebook.com/groups/717908414984387/
85 viewsአቡ ተቅይ ቃዒድ, 03:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 18:25:36 አሰለሙአለይኩም ወረህመቱሏሂ ወበረካትሁ
...........................................................................
፠፠፠ሶላትሽን ስገጅ ብለሽ የመከርሽኝ፠፠፠
""""'''""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""
ያኔዬ ሳይረዝም እለታት ሲነጉዱ፣
ሶላቴን ሳልሰግድ ሳልውል በመንገዱ፣
አንቺ ነበርሽ እህት ያኔዬ እውነቲቱ፣


የኋሊት ላስታውሰው ያኔዬ ምክርሽ፣
ትይኝ ነበር እቱ አላህን ፈርተሽ፣

"ሞት አለብሽኮ የማይቀረው መርዶ፣
ለሁሉም መራራ የማይቀር ተለምዶ፣
ዛሬ ይምጣ ነገ የሌለው ቀጠሮ።

መቃብርም አለ አፈር እንትራሱ፣
ድንጋይና ጭቃ የአካልሽ ልባሱ፣
ምስጥና ትላትል ወድህ አጫዋቹ፣
ውለታ ከፋዮች እባብና ጉንጡ፣
የጅሀነም እሳት የዘላለም ጓዱ፣
አለ የማይቀረው ፍርድና ሚዛኑ።"""

ትይኝ ነበር እህት አምርረሽ ከልብ፣
""ሶላትሽን ስገጅ ለማይቀረው ቤት፣
ለቀብር ለአሄራ ለመግባት ጀነት፣
ከአዛብ ለመውጣት ከጅሀነም እሳት፣
በተውሂድ በሱና በዱኒያ ሰርተሽ፣
ሶላትሽን ሰግደሽ ሸርጡን አሟልተሽ፣
ቀጥብለሽ ቆመሽ አላህን ፈርተሽ፣
ዱኒያን ተላቀቂያት ከሙእሚን ሆነሽ""

እያልሽኝ ሁልጊዜ የመከርሽኝ ሁሉ፣
ዛሬ ላይ ታወሰኝ ሳልጓዝ በከንቱ።

አልሀምዱሊላህ ለአለማት ጌታ፣
በቼሩ ላኖረኝ ከኗሪዎች ተርታ፣
ሶላቴን ሳልሰግድ ሳልጓዝ ባንዳፍታ፣
ከመቃብር ቤቴ ካልወርድ በቀጥታ፣
እስቲግፋር ሳላደርግ የሞት ሞት ሳይመጣ፣
ተውበትን ወፈቀኝ ከዱኒያ ሳልወጣ።

እህቴ ጀዛሽን አላህ ይክፈልልኝ፣
በዱኒያም በአሄራ አላህ ያስመችልኝ፣
በጅህልና ኑሬ ካላህ ሳልገናኝ፣
በተውሂድ በሱና ህይወት ሳታምርልኝ፣
ሶላቴን ሳልሰግድ ጣረሞት ሳይዘኝ፣
አስታወሽኝና ይሄው ተመለስኩኝ፣
በብልጭልጭ ኑሮ በ ልቤ ሳይደማብኝ።
ሶላትሽን ስገጅ ብለሽ የመከርሽኝ፣
ከፊቴ እየመጣ ደግም ሲያስታውሰኝ፣
መንገዱን ይዣለሁ ባለሁበት ያፅናኝ፣
አንቺንም ያበርታሽ እስከለተ ሞትሽ።፠፠



=========================

አቡ ተቅይ ቃዒድ
========================
ኩን ሰለፍያ አለልጀዳ አሰለፍይ መነሀጅ ኦፊሲላዊ ቻናል
https://t.me/AbuTeqiyPomeChannel

ግሩፕ
https://t.me/PomeChannelGroup

ኩን ሰለፍያ አለልጀዳ አሰለፍይ መነሀጅ ኦፊሲላዊ ፔጅ - Home
https://m.facebook.com/KunSelefiyeAllMineOfIniformation/?ref=bookmarks

የፌስቡክ ግሩፕ
https://facebook.com/groups/717908414984387/

138 viewsአቡ ተቅይ ቃዒድ, edited  15:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 12:00:17 መሞት መጥፋት መስሎኝ

መሞት መጥፋት መስሎኝ፣
አካሌ በስብሶ በዛው ይቀር መስሎኝ፣
የወንጀል መርማሪ ሚዛን የለ መስሎኝ፣
ትርፉና ኪሳራው አይበጠር መስሎኝ፣
ከሞትኩኝ በኋላ
መሞት ማረፍ መስሎኝ፣

እራሴን ስሸውድ ሳታልለው ኑሬ፣
በወንጀል መኣበል እራሴ ዘፍቄ፣፣
ካአላህ ፊት እንዳልቆም ከወራዶች ሁኔ፣
እራሴን ላስተካክል ሳይደርስብኝ ሞቴ።

ያረቢ የአላህ ባንተ መንገድ ምራኝ
ዱኒያ አሄራዬን በተውሂድ አስውበኝ።


=========================

አቡ ተቅይ ቃዒድ
========================
ኩን ሰለፍያ አለልጀዳ አሰለፍይ መነሀጅ ኦፊሲላዊ ቻናል
https://t.me/AbuTeqiyPomeChannel

ግሩፕ
https://t.me/PomeChannelGroup

ኩን ሰለፍያ አለልጀዳ አሰለፍይ መነሀጅ ኦፊሲላዊ ፔጅ - Home
https://m.facebook.com/KunSelefiyeAllMineOfIniformation/?ref=bookmarks

የፌስቡክ ግሩፕ
https://facebook.com/groups/717908414984387/



149 viewsአቡ ተቅይ ቃዒድ, 09:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 07:20:54 በአላህ

እውነተኛ ፍቅር ያለው ፣
ከአላህ ዘንድ ብቻ ነው።።።።

ከሰው ቢገኝም

ሸክላ ነው ይደቃል።
ብርሌ ነው ይሰበራል።
እሾክ ነው ይዋጋል።፣
ወንፊት ነው ያፈሳል።
የበሰበሰ ነው ይሸታል።
ንፋስ ነው ያመልጣል።
ህመም ነው ያሰቃያል።
ቃል አፍራሽ ነው ይከዳል።

ብቻ
አውነተኛ ፍቅር
ከአላህ ዘንድ ከልተሰጠ፣

እኛ ፈልገን ለማግኘት ብንዋትትም
አይገኝም ኪሳራ ነው አይጥምም

ለህይወት ፈተና ነው አይምችም

እናማ

ውድ ወንድሜ ታገስ ፅና፣
አህቴም ታገሽ ፅኒ

ለሁሉም ነገር አላህን ለምን፣
አላህን ለምኒ


=========================

አቡ ተቅይ ቃዒድ
========================
ኩን ሰለፍያ አለልጀዳ አሰለፍይ መነሀጅ ኦፊሲላዊ ቻናል
https://t.me/AbuTeqiyPomeChannel

ግሩፕ
https://t.me/PomeChannelGroup

ኩን ሰለፍያ አለልጀዳ አሰለፍይ መነሀጅ ኦፊሲላዊ ፔጅ - Home
https://m.facebook.com/KunSelefiyeAllMineOfIniformation/?ref=bookmarks

የፌስቡክ ግሩፕ
https://facebook.com/groups/717908414984387/

158 viewsአቡ ተቅይ ቃዒድ, 04:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 23:04:35 بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው፡፡

ٱلْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ
ምስጋና ለአላህ ይገባው የዓለማት ጌታ ለኾነው፤

ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ

مَٰلِكِ يَوْمِ ٱلدِّينِ
የፍርዱ ቀን ባለቤት ለኾነው፡፡

إِيَّاكَ نَعْبُدُ وَإِيَّاكَ نَسْتَعِينُ
አንተን ብቻ እንግገዛለን፤ አንተንም ብቻ እርዳታን እንለምናለን፡፡

ٱهْدِنَا ٱلصِّرَٰطَ ٱلْمُسْتَقِيمَ
ቀጥተኛውን መንገድ ምራን፡፡

صِرَٰطَ ٱلَّذِينَ أَنْعَمْتَ عَلَيْهِمْ غَيْرِ ٱلْمَغْضُوبِ عَلَيْهِمْ وَلَا ٱلضَّآلِّينَ
የእነዚያን በነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን በነሱ ላይ ያልተቆጣህባቸውንና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ (ምራን፤ በሉ)፡፡

ሱረቱል ፋቲሃ
==========================
አቡ ተቅይ ቃዒድ
========================
ኩን ሰለፍያ አለልጀዳ አሰለፍይ መነሀጅ ኦፊሲላዊ ቻናል
https://t.me/AbuTeqiyPomeChannel

ግሩፕ
https://t.me/PomeChannelGroup

ኩን ሰለፍያ አለልጀዳ አሰለፍይ መነሀጅ ኦፊሲላዊ ፔጅ - Home
https://m.facebook.com/KunSelefiyeAllMineOfIniformation/?ref=bookmarks

የፌስቡክ ግሩፕ
https://facebook.com/groups/717908414984387/

161 viewsአቡ ተቅይ ቃዒድ, 20:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ