Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopia Orthodox Mazmur & Sabkat

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopiaorthomazmur — Ethiopia Orthodox Mazmur & Sabkat E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopiaorthomazmur — Ethiopia Orthodox Mazmur & Sabkat
የሰርጥ አድራሻ: @ethiopiaorthomazmur
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.23K
የሰርጥ መግለጫ

"ድንግል ሆይ እናቴ ! አዛኝቱ ዛሬም እንደትናንቱ ቅደሚ ከፊት ከኋላዬ "
በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን መዝሙሮች ከነግጥሞቻቸው እና ስብከቶች ይሰጡበታል፡፡
For more contact
@eorthomazmur_Bot
👇👇👇👇 For Discussion👇👇👇👇
https://t.me/joinchat/Fe77ilHyDcn-td_xDU8Tkg

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-28 10:27:03 ​​​​ሰኔ 21 ለሚከበረው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

#ሰኔ_20_እና_21

ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት አንዱ ነው፤ ህንጸተ ቤተክርስቲያን ይባላል።

የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን የታነጸው በዛሬዋ ቀን ነው አናጺውም እራሱ ባለቤቱ ጌታችን መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ነው፤ ቦታው ፊልጰስዩስ ነው፤ ቤተክርስቲያኗ የተሰየመችው ደግሞ በእመቤታችን ስም ነው።

ጴጥሮስ፤ ዮሐንስ በርናባስና ሌሎችም ሐዋርያት በፊልጰስዩስ ተሰብስበው ሳለ ጌታችን መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በኪሩቤል ጀርባ ላይ ሆኖ እልፍ አእላፍ መልአክትን አስከትሎ ይወርዳል እመቤታችን በቀኙ ነበረች፤ 3 ድንጋዮችን አንስቶ ጎተታቸው እንደ ሰም ተለጠጡ እንደ ግድግዳም ሆኑ ዳግመኛም የብርሃን ምሰሶ ወረደ በሰማያዊቷ እየሩሳሌም አምሳያ አድረጎ አነጻት ሁለንተናዋም ተጠናቀቀ፤ ዳግመኛ በበነጋው ሰኔ 21 ቀን እመቤታችንን እና ቅዱሳን መልአክትን አስከትሎ ይወርዳል ቅዳሴ ቀድሶ ለሐዋርያቱ አቆረባቸው ፍጹም ደስታም ሆነ።

ከዚህ በኃላ ሐዋርያት ከጌታ እንዳዩት በዓለም ዞረው ቤተክርስቲያን አንጸዋል። ከዚያ በፊት የነበረው የነሶሎሞን ቤተ መቅደስ የአይሁድ ምኩራብ የአይሁድ ስርዓተ አምልኮ መፈጸሚያ እንጂ የአዲስ ኪዳን የቁርባንም ሆነ የጥምቀት ስርዓት መፈጸሚያ አልነበረም፤ ታዲያ ሐዋርያት የት ነበር ህዝቡን የሚያጠምቁት የሚያቆርቡት ካሉ በየሰው ቤት ነበር።

ዳግመኛ በዛሬዋ ቀን ታላቁ ነብይ ኤልሳዕ አረፈ። ይህ ነብይ በ 12 ጥማድ በሬ ሲያርስ ቴስቢያዊው ነብዩ ኤልያስ ተከተለኝ አለው ምንም ሳያቅማማ ሀብት ንብረቱን ትቶ ተከተለው፤ ኤልያስ በእሳት ሰረገላ ከማረጉ በፊት ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ ይለዋል ባንተ ላይ ያደረ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ እጥፍ ድርብ ሆኖ ይደርቢኝ ይለዋል፤ እንደ ቃሉ ሆነለት ተደረገለት፤ ኤልያስ አንድ ሙት ሲያስነሳ ኤልሳዕ ሁለት ሙት አስነስቷል፤ ኤልያስ አንድ ጊዜ ባህር ሲከፍል ኤልሳዕ ሁለት ጊዜ ባህር ከፍሏል።

የእምቤታችንን የኤልሳዕ ጋን ይላታል ኤልሳ የመረረውን ውኃ እንዳጣፈጠ እመቤታችንም ይህን መራራ ዓለም ጌታን በመውለዷ አጣፍጣዋለች፤ የዚህ ነብይ ድንቅ ታሪኩ 2ኛ ነገስት ላይ በስፋት ተጽፏል ሰኔ 20 ቀን እረፍቱ ነው ቤተክርስቲያን የዛሬውን ቀን እመቤታችንን እና ነብዩን አስባ ትውላለች።

ከበዓሉ ያሳትፈን የእመቤታችን ምልጃና ረዳትነት አይለየን!
2.9K views07:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-24 18:17:55
የሚመለከተው አካል መልስ ይስጥ
የቤተክርስቲያን የበላይ ጠባቂዎች ምላሽ እንዲሰጡን የሞከርነው ሙከራ አልተሳካም::
ቅድስት ቤተክርስቲያን ከምንጠጣበት ግሮሰሪ እኩል እንድትታይ አንፈቅድም ነገሮች ከመበላሸታቸው በፊት በጋራ እናቁማቸው!!

ሻሸመኔ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ሻሸመኔ ቅድስት ልደታ
ኩየራ ፊልቻ ማርያም
በሀገረስብከቱ አዘጋጅነት ነገሌ
አሁን ደሞ በቅድስ አርሴማ ቤተክርስቲያን ሰበካ አማካይነት አቡነ ተክለሀይማኖት ቤተክርስቲያንን ቢራ ማራጨታቸው ቀጥለውዋል
የኪዳነ ምህረት ሰበካ ግንቦት 13-21 ባዛር ማካሄድ ጀምሯል ከቢራ አምራቾች ጋ ጥንስስ ጥለዋል ።
ይህ እንዳበቃ ቅዱስ ኡራኤሌ በቀሲስ ዳንኤል ውብሸት የሚተዳደረው ደብር ያቀረበው እቅድ በላይኛው አካል ፀድቆለት ከቢራ ፋብሪካ 100 - 200 ሳጥን ለማግኘት ቋምጧል ። የሚያሳዝነው በዚህ ሁሉ ሒደት ውስጥ ቤተክርስቲያን እና ክብሯ ለማንኛውም አካል ግድ አልሰጠውም ።
። አሁንግን ነገሮች የሆነ ቦታ ላይ ማብቃት አለበት ።
በቤተክርስቲያን ውስጥ ምንም አይነት የአልኮል መጠጥ እንዲሸጥ አንፈቅድም ።
የቢራው ድንኳኑን አውጡልን
የቢራ ሳጥኖችን አውጡልን
ሼር በማድረግ እንቃወመው
3.8K views15:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-08 21:58:27 ✟✟
✟✟
✟✟✟✟✟✟
✟✟
✟✟
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@ethiopiaorthomazmur
@ethiopiaorthomazmur
@ethiopiaorthomazmur
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
3.7K views18:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-08 21:52:39 ዮም ፍሰሐ ኮነ

ዘማሪ ፍቃዱ አማረ


--------------------------------------
ዮም ፍሰሐ ኮነ
ፍሰሐ ኮነ
በእንተ ልደታ ለማርያም (2)
--------------------------------------

በባርነት ሳለን ----------- ፍሰሐ ኮነ
ኃጢአት በዓለም ነግሳ ----------- ፍሰሐ ኮነ
በድንግል መወለድ ----------- ፍሰሐ ኮነ
ቀረልን አበሳ ----------- ፍሰሐ ኮነ
እግዚአብሔር መረጠሸ ----------- ፍሰሐ ኮነ
ልትሆኚ እናቱ ----------- ፍሰሐ ኮነ
ይኸው ተፈጸመ ----------- ፍሰሐ ኮነ
የዳዊት ትንቢቱ ----------- ፍሰሐ ኮነ

-------------------------------------
ዮም ፍሰሐ ኮነ
ፍሰሐ ኮነ
በእንተ ልደታ ለማርያም (2)
-------------------------------------

የሰው ልጆች ተስፋ ----------- ፍሰሐ ኮነ
የአዳም ህይወት ----------- ፍሰሐ ኮነ
የኢያቄም የሐና ----------- ፍሰሐ ኮነ
ፍሬ በረከት ----------- ፍሰሐ ኮነ
ምክንያት ድኀነት ----------- ፍሰሐ ኮነ
ኪዳነ ምሕረት ----------- ፍሰሐ ኮነ
ድንግል ተወለደች ----------- ፍሰሐ ኮነ
የጌታዬ እናት ----------- ፍሰሐ ኮነ

-------------------------------------
ዮም ፍሰሐ ኮነ
ፍሰሐ ኮነ
በእንተ ልደታ ለማርያም (2)
-------------------------------------

በሔዋን ምክንያት ----------- ፍሰሐ ኮነ
ያጣነውን ሰላም ----------- ፍሰሐ ኮነ
ዛሬ አገኘነው ----------- ፍሰሐ ኮነ
በድንግል ማርያም ----------- ፍሰሐ ኮነ
የምስራች እንበል ----------- ፍሰሐ ኮነ
ሃዘናችን ይጥፋ ----------- ፍሰሐ ኮነ
ተወልዳለችና ----------- ፍሰሐ ኮነ
የዓለም ሁሉ ተስፋ ----------- ፍሰሐ ኮነ

-------------------------------------
ዮም ፍሰሐ ኮነ
ፍሰሐ ኮነ
በእንተ ልደታ ለማርያም (2)
-------------------------------------
✟✟
✟✟
✟✟✟✟✟✟
✟✟
✟✟
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@ethiopiaorthomazmur
@ethiopiaorthomazmur
@ethiopiaorthomazmur
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
3.6K views18:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-08 21:52:35 ግንቦት 1 - እንኳን አደረሳችዉ
የእመቤታችን የልደት በዓል
የእመቤታችን ታሪክ

የእመቤታችን ወላጆች በአብዛኛው አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ “ሃና” እና ኢያቄም /ዮአኪን በሚለው ስም የሚጠሩ ሲሆን ሃና በቤተልሔም ተወልዳ እንዳደገች ታሪክ ያስረዳል፡፡ በናዝሬት ገሊላ ለመሥዋዕት የሚሆኑ በጎች የሚያቀርብ እንዲሁም እረኛ የነበረውን ኢያቄምንም አግብታለች፡፡ ቅድስት ሃና ወደ ቤተ መቅደስ ስትሔድ አርጋብን አይታ ታለቅስ ነበር፡፡ ከብዙ ልመና በኋላ ቅድስት ድንግል ማርያምን ግንቦት አንድ ቀን በደብረ ሊባኖስ ወልደዋል፡፡

ስለ ሃና መካንነት ወደ ቤተ መቅደስ ሄደው መባዕ ሲያቀርቡ ካህኑ ያልተቀበላቸዉ መሆኑን በብስራተ መልአክ ልጅ እንደሚወልዱ እንደተነገራቸው በእኛ ቤተ ክርስቲያን የሚተረከውና በሌሎች ኦርቶዶክሳዊያን አብያተ ክርስቲያናት የሚነገረው ታሪክ ተመሳሳይ ነው፡፡

እመቤታችን የት ተወለደች?

እመቤታችን ስለተወለደችበት ስፍራ በዓለም የተለያዩ ሀሳቦች ይስተጋባሉ፡፡ ሌላው ቀርቶ በዶግማ አንድነት ባላቸው አኃት አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ በእንዲህ ዓይነት ታሪክ ነክ ጉዳዮች ላይ ልዩነት መኖራቸው የተለመደ ክስተት ነው፡፡ የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሁለት ሀሳቦች የሚያነሱ ሲሆን አንደኛው “ድንግል ማርያም ብስራተ መልአክ በሰማችበት ናዝሬት ተወልዳለች” የሚል ነው፡፡ ሁለተኛው ሀሳብ ደግሞ “ከሦስተኛው ክ/ዘመን ወዲህ የማርያም መግቢያ ተብሎ በሚታወቀው ከኢየሩሳሌም የቅድስት ሃና የክሩሲድ ቤተ ክርስቲያን በታች ነዉ የተወለደችው” የሚል ነው፡፡

የግብጽ ስንክሳር የእመቤታችን የትውልድ ስፍራ በናዝሬት ነው ይላል፡፡ የኢትዮጵያ ስንክሳር ግን በቀደምትነታቸው ተጠብቀው የቆዩ ከመሆናቸው አንጻር ተአማኒነታቸው የጎላ መሆኑን ያሳያል፡፡ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት የእመቤታችን የትውልድ ስፍራ ሊባኖስ የተባለው ተራራማ ሀገር ነው፡፡ ሊባኖስ ከገሊላ በስተ ሰሜንና ከፍንቄ በስተ ምስራቅ ይገኛል፡፡ “ሙሽራየ ሆይ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነይ” የሚለዉ ቃለ ትንቢት ምስጢርም የአመቤታችን መካነ ልደት የሊባኖስ ተራራ ስለመሆኑ የሚያጠይቅ እንደሆነ ምስክርነታቸው የታመነ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ያስረዳሉ፡፡ /መኃ 4፥7/

የልደታ ለማርያም በዓል መቼ ነው?

እንደተወለደችበት ሥፍራ የእመቤታችን የልደት ቀን እንዲሁ አወዛጋቢ ነው፡፡ በ 6ኛውና 7ኛው መቶ/ክ/ዘመን ነው የሚሉ የተለያዩ ሃሳቦች የተጻፉ ሲሆን Encyclopaedic of Christian antiquities ደግሞ በ431 ዓ/ም ከተካሄደውና ንስጥሮስ ከተወገዘበት ከጉባኤ ኤፌሶን በኋላ ነው ይላል፡፡ በዓለም ቅዱሳንን የሚያከብሩ አብያተ ክርስቲያናት የቅዱሳንን በዓለ እረፍታቸውን የሚያከብሩ ሲሆን ልደታቸው የሚከበረውም በሦስተኛ ደረጃ የመጥምቀ መለኮት ቅዱስዮሐንስ፤ በሁለተኛ ደረጃ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልደት ነው፡፡ በአንደኛ ደረጃ ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ነው፡፡ የአመቤታችን ልደት በምዕራባዊያን አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ኬክ በመጋገር፡ የአመቤታችን ትንሽ ሀውልት በማቆም ዐሥር ሻማዎችን በማብራት ያከብራሉ፡፡

የድንግል ማርያም ልደት ለምን ይከበራል?

• ስለ መጥምቁ ዮሐንስ ልደት በመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል አንደበት “በመወለዱ ብዙዎች ደስ ይላቸዋል” በማለት ተነግሯል /ሉቃ 1፥14/ ምክንያቱም ቅደስ ዮሐንስ የጌታ መንገድ ጠራጊ የአዋጅ ነጋሪ በመሆኑ ነው፡፡ የቅዱስ ዮሐንስ መወለድ ለብዙዎች ደስታ ምክንያት ከሆነ የድንግል ማርያም ልደት ምንኛ የሚያስደስት ይሆን፡፡ ስለሆነም ከጌታችን ቀን ቀጥሎ የምንደሰትበት ትልቁ ቀን የእርሷ የልደት ቀን ነው፡፡
• የቀርጤሱ ቅዱስ እንድርያስ ስለ ከበረ ልደቷ እንዲህ ብሏል “ይህ በዓል በሐዲስና በብሉይ ኪዳን መካከል መገኛ ሆነ፡፡ ምስሌዎቹ በእዉነታ፣ አሮጌው በአዲስ ቃል ኪዳን ተተኩ፡፡ ፍጥረት ሁሉ በደስታ ይዘምራል የዚህን ቀንም ደስታ ይካፈላል፡፡ ይህ መቅደሱን የሰራበት ዕለት ነው፡፡ ይህ ዕለት ትልቅ ሕንፃ የታነጸበትና ፍጡር የፈጣሪ ማደሪያ ለመሆን የተዘጋጀበት ዕለት ነው፡፡” ብሏል፡፡
• እመቤታችን ለፀሐዩ መምጣት የተዘረጋች ሰማይ፡ በቅድመ አያቶቿ በነቴክታና ጰጥሪቃ ህልም እንደታየችው በሌሊት የምታበራ ጨረቃ የብሉይ ኪዳን ማብቂያ የሐዲስ ኪዳን መጀመሪያ ናትና ልደቷ ለሰው ልጅ ሁሉ ደስታ ነው፡፡ ነቢያት በብዙ ሕብረ አምሳል የተናገሩላት “መሰረቶቿ የተቀደሱ ተራራዎች ናቸው” “ከእሴይ ስር በትር ትወጣለች አበባዋም ከግንዱ ይወጣል” “ሙሽራየ ሆይ ከሊባኖስ ነይ” .ብለው ተናገሩላት ቅድስት ድንግል ማርያም ልደቷ የትንቢታቸው ፍፃሜ ነውና ታላቅ ደስታቸው ነው፡፡ /መዝ86፥1፤ ኢሳ 11፥1/
• በዓለም ላይ የብዙ ታዋቂ ሰዎች ልደት ከሞቱም በኋላም ጭምር በታላቅ ድምቀት ይከበራል ታዋቂ ያልሆኑ ሰዎች ልደትም እንዲሁ ይታሰባል ለሰው ልጅ መዳን ምክንያት የሆነች የአምላክ እናት የተወለደችበት ቀን ምንኛ ሊከበር ይገባው ይሆን!

የግንቦት ልደታ በዓል አከባበር

በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት መሠረት ሃና እና ኢያቄም ከአይሁድ ለማምለጥ ተሰደው በአድባረ ሊባኖስ ሥር እመቤታችንን ወለዱ በወቅቱ ከቤት የወጡት ለሽሽት ነበርና ስንቅ ስላልያዙ ምግባቸው “ንፍሮና ጥራጥሬ” ነበር፡፡ ይኼንን ትውፊት በመያዝ በዓሉ ከቤት ዉጭ ንፍሮ እየተበላ ይከበራል፡፡ ሆኖም በበጎ ነገሮች ሰበብ ክፉ ዓላማውን ማስፈጸም የሚፈልገው ዲያብሎስ በማር መሃል መርዝን ከሚጨምርባቸው መንፈሳዊያት በዓላት አንዱ የግንቦት ልደታ የእመቤታችን በዓል ነው፡፡ አንዳንዶች በድፍረት ለአድባር ለዉጋር ነው፣ ቆሌውን ለመለመን ነው፣ እያሉ ንፍሮ የሚበትኑ፣ ቡና የሚረጩ፣ ቂቤ የሚቀቡ፣ የከብት ደም የሚያፈሱ፣ እነዚህ በእርግጥም ጣዖት አምላኪዎች ናቸው፡፡ እኛም ከእንደዚ ዓይነቶቹ አሰናካዮች በመለየት ይኼንን ታላቅ በዓል በተገባና በተረዳ ነገር እንድናከብረው የእመቤታችን ረድኤት በረከት አይለየን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
አሜን
8.5K views18:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-25 08:43:41 ​​ ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ

ሰኞ

ማዕዶት ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡

ማክሰኞ

ቶማስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29

ረቡዕ

አልአዛር ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡

ሐሙስ

አዳም ሐሙስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡

ዓርብ

ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡

ቅዳሜ

ቅዱሳት አንስት ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡

እሁድ

ዳግም ትንሣኤ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡
4.2K views05:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-28 13:12:09
6.2K views10:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-28 13:12:04 ​​እንኳን ለእመቤታችን ንጽሕት ድንግል ወላዲተ አምላክ ማርያም ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።

† † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! † †

† #ዕረፍተ_ድንግል †

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቅድመ ዓለም በአምላክ ልቡና ታስባ ትኖር ነበር:: ከነገር ሁሉ በፊት እግዚአብሔር እናቱን ያውቃት ነበር::

ዓለም ተፈጥሮ: አዳምና ሔዋን ስተው: መርገመ ሥጋና መርገመ ነፍስ አግኝቷቸው: በኃዘን ንስሃ ቢገቡ "እትወለድ እም ወለተ ወለትከ - ከ5 ቀን ተኩል (5500 ዘመናት) በሁዋላ ካንተ ባሕርይ ከምትገኝ ንጽሕት ዘር ተወልጄ አድንሃለሁ" ብሎ ተስፋ ድኅነት ሰጠው::

ከአዳም አንስቶ ለ5500 ዓመታት አበው: ነቢያትና ካህናት ስለ ድንግል ማርያም ብዙ ሐረገ ትንቢቶችን ተናገሩ:: መዳኛቸውን ሱባኤ ቆጠሩላት:: ምሳሌም መሰሉላት:: ከሩቅ ዘመን ሁነውም ሊያገኟት እየተመኙ እጅ ነሷት::
"እምርሑቅሰ ርእይዋ: ወተአምኅዋ" እንዲል::

የድንግል ማርያም ሐረገ ትውልድ
- ከአዳም በሴት
- ከያሬድ በሔኖክ
- ከኖኅ በሴም
- ከአብርሃም በይስሐቅ
- ከያዕቆብ በይሁዳና በሌዊ
- ከይሁዳ በእሴይ: በዳዊት: በሰሎሞንና በሕዝቅያስ ወርዳ ከኢያቄም ትደርሳለች::

ከሌዊ ደግሞ በአሮን: አልዓዛር: ፊንሐስ: ቴክታና በጥሪቃ አድርጋ ከሐና ትደርሳለች::

አባታችን አዳም ከገነት በወጣ በ5,485 ዓመት ወላዲተ አምላክ ንጽሕና ሳይጐድልባት: ኃጢአት ሳያገኛት: ጥንተ አብሶ ሳይደርስባት ከደጋጉ ኢያቄም ወሐና ትወለዳለች:: (ኢሳ. 1:9, መኃ. 4:7) "ወኢረኩሰት በምንትኒ እምዘፈጠራ" እንዳለ:: (ቅዱስ ቴዎዶጦስ ዘዕንቆራ)

ከዚያም ከእናት ከአባቷ ቤት ለ3 ዓመታት ቆይታ ወደ ቤተ መቅደስ ትገባለች:: በቤተ መቅደስም ለ12 ዓመታት ፈጣሪዋን እግዚአብሔርን እያመሰገነችና እያገለገለች: እርሷን ደግሞ መላእክተ ብርሃን እያገለገሏት: ሕብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ሰማያዊ እየመገቧት ኑራለች:: 15 ዓመት በሞላት ጊዜ አረጋዊ ዮሴፍ ያገለግላት ዘንድ ወደ ቤቱ ወሰዳት::

በዚያም መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ዜና ድኅነትን ነግሯት አካላዊ ቃልን በማሕጸንዋ ጸነሰችው:: ነደ እሳትን ተሸከመችው: ቻለችው:: "ጾርኪ ዘኢይትጸወር: ወአግመርኪ ዘኢይትገመር" እንዳለ:: (ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም ለብሐዊ)

ወልደ እግዚአብሔርን ለ9 ወራት ከ5 ቀናት ጸንሳ: እንበለ ተፈትሆ (በድንግልና) ወለደችው:: (ኢሳ. 7:14) "ኢየሱስ" ብላ ስም አውጥታለት በገሊላ ለ2 ዓመታት ቆዩ::

አርዌ ሔሮድስ እገድላለሁ ብሎ በተነሳበት ወቅትም ልጇን አዝላ በረሃብ እና በጥም: በላበትና በድካም: በዕንባና በኃዘን ለ3 ዓመታት ከ6 ወራት ከገሊላ እስከ ኢትዮዽያ ተሰዳለች:: ልጇ ጌታችን 5 ዓመት ከ6 ወር ሲሆነው: ለድንግል ደግሞ 21 ዓመት ከ3 ወር ሲሆናት ወደ ናዝሬት ተመለሱ::

በናዝሬትም ለ24 ዓመታት ከ6 ወራት ልጇን ክርስቶስን እያሳደገች: ነዳያንን እያሰበች ኑራለች:: እርሷ 45 ዓመት ልጇ 30 ዓመት ሲሆናቸው ጌታችን ተጠምቆ በጉባኤ ትምሕርት: ተአምራት ጀመረ:: ለ3 ዓመታት ከ3 ወራትም ከዋለበት እየዋለች: ካደረበትም እያደረች ትምሕርቱን ሰማች::

የማዳን ቀኑ ደርሶ ልጇ ክርስቶስ ሲሰቀልም የመጨረሻውን ፍጹም ሐዘን አስተናገደች:: አንጀቷ በኃዘን ተቃጠለ:: በነፍሷም ሰይፍ አለፈ:: (ሉቃ. 2:35) ጌታ በተነሳ ጊዜም ከፍጥረት ሁሉ ቀድማ ትንሳኤውን አየች:: ለ40 ቀናትም ሳትለይ ከልጇ ጋር ቆየች::

ከልጇ ዕርገት በሁዋላ በጽርሐ ጽዮን ሐዋርያትን ሰብስባ ለጸጋ መንፈስ ቅዱስ አበቃች:: በጽርሐ ጽዮንም ከአደራ ልጇ ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር ለ15 ዓመታት ኖረች:: በእነዚህ ዓመታት ሥራ ሳትፈታ ስለ ኃጥአን ስትማልድ: ቃል ኪዳንን ከልጇ ስትቀበል: ሐዋርያትን ስታጽናና: ምሥጢርም ስትገልጽላቸው ኑራለች::

ዕድሜዋ 64 በደረሰ ጊዜ ጥር 21 ቀን መድኃኒታችን አእላፍ ቅዱሳንን አስከትሎ መጣ:: ኢየሩሳሌምን ጨነቃት:: አካባቢውም በፈውስ ተሞላ:: በዓለም ላይም በጐ መዓዛ ወረደ:: እመ ብርሃን ለፍጡር ከዚያ በፊት ባልተደረገ: ለዘለዓለምም ለማንም በማይደረግ ሞገስ: ክብርና ተአምራት ዐረፈች:: ሞቷ ብዙዎችን አስደንቁአል::
"ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ::
ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኩሉ::" እንዲል::

ከዚህ በሁዋላ መላእክት እየዘመሩ: ሐዋርያቱም እያለቀሱ ወደ ጌቴሴማኒ: በአጐበር ሥጋዋን ጋርደው ወሰዱ:: ይሕንን ሊቃውንት:-
"ሐራ ሰማይ ብዙኃን እለ አልቦሙ ሐሳበ::
እንዘ ይዜምሩ ቅድሜኪ ወመንገለ ድኅሬኪ ካዕበ::
ማርያም ሞትኪ ይመስል ከብካበ" ሲሉ ይገልጡታል::

በወቅቱ ግን አይሁድ በክፋት ሥጋዋን እናቃጥል ስላሉ ቅዱስ ገብርኤል (ጠባቂ መልአክ ነው) እነርሱን ቀጥቶ: እርሷን ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር ወስዶ በዕጸ ሕይወት ሥር አኑሯታል:: በዚያም መላእክት እያመሰገኗት ለ205 ቀናት ቆይታለች::

ቅዱስ ዮሐንስ መጥቶ ለሐዋርያቱ ክብረ ድንግልን ቢነግራቸው በጐ ቅንአት ቀንተው በነሐሴ 1 ሱባኤ ጀመሩ:: 2ኛው ሱባኤ ሲጠናቀቅም ጌታ የድንግል ማርያምን ንጹሕ ሥጋ ሰጣቸው:: እየዘመሩም በጌቴሴማኒ ቀብረዋታል::

በ3ኛው ቀን (ነሐሴ 16) እንደ ልጇ ባለ ትንሳኤ ተነስታ ዐርጋለች:: ትንሳኤዋንና ዕርገቷንም ደጉ ሐዋርያ ቅዱስ ቶማስ አይቶ: መግነዟን ተቀብሏል:: ሐዋርያቱም መግነዟን ለበረከት ተካፍለው: እንደ ገና በዓመቱ ነሐሴ 1 ቀን ሱባኤ ገቡ::

ለ2 ሳምንታት ቆይተው: ሁሉንም ወደ ሰማይ አወጣቸው:: በፍጡር አንደበት ተከናውኖ የማይነገር ተድላ: ደስታና ምሥጢርንም አዩ:: ጌታ ራሱ ቀድሶ ሁሉንም አቆረባቸው:: የበዓሉን ቃል ኪዳን ሰምተው: ከድንግል ተባርከው ወደ ደብረ ዘይት ተመልሰዋል::

ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን: ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኚልን:: አእምሮውን: ለብዎውን: ጥበቡን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን::

#ቅዱስ_ጐርጐርዮስ_ሊቅ

ለዚህ ቅዱስ አባት ብጹዕ መባል ተገብቷል:: ክቡር: ምስጉን: ንዑድ ሰው ነውና:: በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በቂሣርያ ቀዸዶቅያ የተወለደው ቅዱሱ ሰው ለደሴተ ኑሲስ ብርሃኗ ነው:: አባቱ ኤስድሮስ: እናቱ ኤሚሊያ: ወንድሞቹ ቅዱሳን "ባስልዮስ: ዼጥሮስ: መክርዮስና መካርዮስ" ይባላሉ::

የተቀደሰች እህቱም ማቅሪና ትባላለች:: ከዚህ የተባረከ ቤተሰብ ለቅድስና ያልበቃ አንድም ሰው የለም:: ሊቁ ቅዱስ ጐርጐርዮስም ከማር በጣፈጠ ዜና ሕይወቱ እንደ ተጻፈው:-

በልጅነቱ ቅዱሳት መጻሕፍትን ተምሯል::
ሥጋውያን ጠቢባንን ያሳፍር ዘንድም የግሪክን ፍልሥፍና በልኩ ተምሯል:: በታላቅ ወንድሙ ቅዱስ ባስልዮስ መሪነት ገዳማዊ ሕይወትን ተምሯል:: በመንኖ ጥሪት ተመስግኗል::
ተገብቶትም በኑሲስ ደሴት ላይ ዻዻስ ሆኗል:: እርሱ ሲሔድ በከተማው የነበሩ ክርስቲያኖች 11 ብቻ የነበሩ ሲሆን እርሱ ሲያርፍ ክርስቶስን የማያመልኩ ሰዎች ቁጥር 11 ብቻ ነበር:: ቅዱስ ጐርጐርዮስ ፍጹም ሊቅ ነበርና ከቁጥር የበዙ ድርሳናትን ደርሷል:: ታላቁን ጉባኤ ቁስጥንጥንያን (በ381 ዓ/ም) መርቷል:: ብዙ መናፍቃንንም አሳፍሯል::

ከንጽሕናው የተነሳ መላእክት ያቅፉት: እመ ብርሃንም ትገለጥለት ነበር:: ለ33 ዓመታት እንደ ሐዋርያት ኑሮ በዚህ ቀን ድንግል ጠራችው:: ቀድሶ አቁርቦ: ሕዝቡን አሰናብቶ: የቤተ መቅደሱን ምሰሶ እንደ ተደገፈ ዐርፎ ተገኝቷል:: በዝማሬና በፍቅር ቀብረውታል::

@eorthomazmur
@eorthomazmur
@eorthomazmur
5.9K views10:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-03 22:18:08
5.7K views19:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-03 22:17:59 የገሃድ ጾም

የገና በዓል ዘንድሮ ዓርብ ይዉላል

ዓርብ ይጾማል?

ገሃድ ወይም ጋድ በጥምቀትም በልደትም አለ አገባቡ ግን ይለያል

ገሃድ ወይም ጋድ ትርጉሙ
መገለጥ፣ መለወጥ፣ ለውጥ፣ምትክ የሚሉ ስያሜዎችን ሲይዝ እንደ አገባቡ ለገናም ለጥምቀትም እንጠቀማለን።

ለገና ሲሆን ገሃድ ምትክ የሚለው ሳይሆን መገለጥ የሚለውን ትርጉም ይይዛል።

ለገና የገና ፆም እስከ በዓሉ ድረስ ስለሚፆም ፆሙ እስከ በዓሉ ዋዜማ ይፆማልና ከዚህ አንፃር በዓሉ በታህሳስ 29 ከሆነ ታህሳስ 28 መጀመሪያውኑ ፆም በመሆኑ ምዕመናን ይፆሙታል

የገና ፆም ምዕመናን ሁሉ ከሰባት ዓመት ጀምሮ እንዲፆሟቸው በአዋጅ ከተደነገጉ ሰባት አፅዋማት አንዱ በመሆኑ ሙሉውን መፆም እንጂ ሲበሉ ቆይተው የመጨረሻዋን ዕለት ገሃድ ናት ማለት ስህተትና ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን አለማወቅ ጭምር ነው
ለገና ገሃድ ስንል ምትክ ማለታችን አለመሆኑን መዘንጋት ፈፅሞ የለብንም እና አንዷን ቀን ብቻ መፆም ስርዓተ ቤተክርስቲያን አይደለም።

ለገና ገሃድ ለምን ተባለ ገሃድ መገለጥ፣መታየት ነው ብለናል የክርስቶስ ሰው መሆን መገለጡ፣
አምላክ በድንግል ማህፀን ተወስኖ መገለጡ ወይም መታየቱ ለማብሰር የመጨረሻዋ ቀን ገሃድ ትባላለች
ከላይ እንደ ተመለከትነው መገለጥ፣መታየት የሚለው ትርጉም እዚህ ላይ ግልፅ ይሆናል።

ልክ በአቢይ ፆም ፆመ ህርቃል እንዳለ ፆመ ህማማት እንደሚፆም ሁሉ በገና የጌታችንን ሰው መሆን የጌታን መገለጥ በማሰብ የመጨረሻዋን ቀን ገሃድ እንላታለን

"ልደት ዓርብና ረቡዕ ሲውል ዕለቱ ከጌታ ልደት በላይ ደስታ የለምና፣ከክርስቶስ መወለድ በላይ ሃሴት የለምና አርብ ረቡዕ ፆምነታቸው ይሻራል "

ፍስክ ይሆናል በክርስቶስ መወለድ ያዘነው ሄሮድስ እና ጭፍሮቹ እንጂ ክርስቲያኖች አያዝኑም ፆም ማዘን፣መተከዝ፣መጎሳቆል፣መራብ መጠማት፣መስገድ መድከም ማለት ነውና በጌታ ልደት እነዚህ አይኖሩም

አባቶች እንዲህ ይላሉ
"በጌታ ልደት ማዘን እንደ ሄሮድስና ጭፍሮቹ፣በስቅለቱ መዝፈን እንደ አይሁድ ያስቆጥራል።"

ስለዚህ የገና በዓል ከዘጠኙ ዓበይት በዓላት አንዱ ነውና ዓርብ ረቡዕ ላይ ቢውል ፆምነቱ ተሽሮ ፍስክ ይሆናል

ልደቱን መገለጡን በታላቅ ደስታና ሃሴት እናከብረዋለን።
ቅዳሜና እሁድ ላይ የልደት ዋዜማ ቢውል ከጥሉላት ምግቦች መፆም ግድ ሲሆን ከእህል ውሃ ግን አይጾምም።

በሰላም ያድርሰን፣ አምላካችን ይርዳን

ፍ/ነገሥት አን 15 ቁ 566ና 603
6.1K views19:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ