2022-06-11 23:04:00
በመላኢኮቺ ማመን ምን ማለት ነው ?
መላዕክት የተባሉ ፍጡሮቺ እንዳሉና አላህ (ﷻ)ን ሊገዙትና ትዕዛዙን ሊተገብሩ የተፈጠሩ ፍጡራኖቺ መኖራቸውን ማመን ነው ፡፡
አላህ በቁርአን
عِبَادٌ مُّكْرَمُونَ
(መላእክት) የተከበሩ ባሮች ናቸው፡፡
لَا يَسْبِقُونَهُ بِالْقَوْلِ وَهُم بِأَمْرِهِ يَعْمَلُونَ
በንግግር አይቀድሙትም፤ (ያላለውን አይሉም)፡፡ እነርሱም በትእዛዙ ይሠራሉ፡፡
ይለናል ፡፡
በመላዕክት ማመን ሲባል ብዙ ነገሮቺን ያጠቃልላል ፡፡
• መኖራቸውን ማመን
• ስማቸውን ማወቅ
• ባህሪናቸውና ግዙፍነታቸው ከሰው የተለየ መሆኑን መረዳት
• ለመለኢኮቺ የተሰጠውን የስራ ድርሻ ማወቅና ሌሎቺንም ይይዛል፡፡
ሰለዚህ በቁርዐን ዉስጥ የተጠቀሱትን አሥሩ
መላዕክቶችና የሥራ ድርሻቸዉን ለማወቅ ከታቺ ባሉት ዝርዝሮቺ ማወቅ የምትቺሉ ይሆናል
1 ጂብሪል ~መልዕክትን ማድረስ
2 ሚካኤል ~ የዝናብ ተወካይ
3 አስራፊል~ የትንሳኤ ቀን ነፊ (ጥሩንባነፊ)
4 መለከል መዉት~ነፍስ አዉጭ
5 ረቂብ ና አቲድ ~
ጥሩ ና መጥፎ ስራችንን መዝጋቢዎቺ
6 ነኪር ና ሙንከር ~ቀብር ዉሥጥ ጥያቄ ጠያቂዎች
7 ማሊክ ~የጀሀነም በር ዘበኛ
8 ሪድዋን ~ የጀነት በር ዘበኛ
መላእክት እነዚህ ብቻ አይደሉም በቁጥር እጂግ በጣም ብዙ ናቸው፡፡
#አብዱልከሪም_አልሀናኒ
=====================
@AbdulKereem_AlHanani
@AbdulKereem_AlHanani
=====================
2.7K viewsedited 20:04