Get Mystery Box with random crypto!

⚡️ Kerem Bedrudin ⚡️ ዐብዱል ከሪም_አልሀናኒ⚡️

የቴሌግራም ቻናል አርማ abdulkereem_alhanani — ⚡️ Kerem Bedrudin ⚡️ ዐብዱል ከሪም_አልሀናኒ⚡️
የቴሌግራም ቻናል አርማ abdulkereem_alhanani — ⚡️ Kerem Bedrudin ⚡️ ዐብዱል ከሪም_አልሀናኒ⚡️
የሰርጥ አድራሻ: @abdulkereem_alhanani
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.94K
የሰርጥ መግለጫ

وَقُلْ جَاءَ الْحَقُّ وَزَهَقَ الْبَاطِلُ ۚ إِنَّ الْبَاطِلَ كَانَ زَهُوقًا

በልም «እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና፡፡»
ለማንኛውም አስተያየትና ጥቆማ ከታቺ ያድርሱኝ
☞ @Abdulkereem_alhanani_bot

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-11 07:42:52 ማሀላ ጋር የተያያዙ 3 ነጥቦቺ

➊ ከአላህ ሌላ በሆነ ነገር የማለ ሰው ከሀዲ ወይም አጋሪ ይባላል ፡፡ መማል የፈለገ ሰው በአላህ ይማል ወይ ዝም ይበል ፡፡

➋ የአንድን ሙስሊም ገንዘብ ለመውሰድ ብሎ በሐሰት የማለ ሰው አላህ ተቆጥቶበት ይገናኛሉ ፡፡

➌ ገብያ ላይ ማህላን ተጠንቀቁ ፡ ምክንያቱም መሀላ እቃን ያስወድድና በረካን ይነሳል ፡፡

ነብዩ ሙሀመድ (ﷺ)

#አብዱልከሪም_አልሀናኒ
=====================
@AbdulKereem_AlHanani
@AbdulKereem_AlHanani
=====================
3.8K views04:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 08:05:58 ሙስሊሟ እህቴ ሆይ!

በዚህ ዘመን የኢስላም ጠላቶች ሂጃብሽን አስወልቀው ከተራ ዱርየዎች ተርታ ሊያሰልፉሽ ተዘጋጅተዋል፡፡

ለዚህ ተንኮላቸው ደግሞ ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱት ቴሌቪዥኖች፣ ሞባይሎች ፣ ጋዜጦች እና የተለያዩ ሚዲያዎች እንደነ ፌስ ቡክ ቲክቶክ ዩ ቲዩብ ናቸው፡፡

አጠቃቀማቸውን ካላወቅሺ እመኝኝ መጥፊያሺ ይሆናሉ ። ሀያዕሸን ትገፌለሺ በጭፈራና ሙዚቃ ልብሺ መነቃቃት ይጀምራል ፤ ነጮቺ ባጠመዱልሺ ወጥመድ ውስጥ ገብተሺ በአለባበስና አነጋገር ሳይቀር እነሱን ለመምሰል ትዳክሬለሺ። በስተመጨረሻም እንዳንቺ በሙዚቃና በሱስ የሰከረ ሂወት ያለው አራዳነት መጨፈር፤ ጫት መቃም ፤ ፊልም ማየት፤ፎቶ መነሳት፤ የሚመስለው ወንድ ላይ ትወድቄለሺ አለቀ።

ኢስላምሺን በሚገባ ሳትኖሪው ሳታቂው ሞት ይመጣል። ያኔ ምንድነው መልስሺ ?

ቁርአን መስማትና መቅራት መስጂድ ማዘውተር ልብሺ እየተወ ሲመጣ ቀልብሺ ይደርቃል ያኔ አትጠራጠሪ አንቺ የኢስለም አስተምህሮትን ጥሰሻል ከአፈንጋጮቹ ሁነሻል። የሰይጣንን መንገድ መከተል ጀምረሻል።

አሏህም እንዲህ ይለናል :-

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا ادْخُلُوا فِي السِّلْمِ كَافَّةً وَلَا تَتَّبِعُوا خُطُوَاتِ الشَّيْطَانِ ۚ إِنَّهُ لَكُمْ عَدُوٌّ مُّبِينٌ

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ሁላችሁም በመታዘዝ ውስጥ ግቡ፡፡ የሰይጣንንም እርምጃዎች አትከተሉ፤ እርሱ ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና፡፡


ነቃ በይ !!! እህቴ

ምርጥና እውነተኛ ያአሏህ ባሪያ ሁኝ ! አስመሳይ አትሁኝ ማሰመሰል ይበቃሻል ፎርጂድ አትሁኝ እውነቱን ሀቁን እያወቅሺ እውነተኛና ምርጥ ሴት ከመሆን አትዘናጊ የአንድ ቀን መዘናጋትሺ ሂወትሺን ሙሉ የማትመልሽው የማይቃና ቺግር ሊሆን ይቺላልና ወደ አሏህ ተመለሺ ።

ስለሆነም አንዲት ሙስሊም ሴት አሏህ ባዘዛት መሰረት ቀጥ ካለችና ሒጃቧን ባግባቡ ከለበሰች በኢማኗ ጥንካሬ የሚከሰቱ ውዝንብሮችን እና የሰይጣን ተንኮሎችን በአሏህ ፈቃድ ትከላከላለች፡፡


ኢማኗ የደከመባት ሴት በተቃራኒው አንድ ስንዝር ወይም አንድ ክንድ ወይም ከዚያ በላይ እንደ ኢማኗ ድክመት አካሏን ትገልጣለች፡፡

ለቅኑ ጎዳና እንዲመራሽ ፤ ግልጽም ከሆነ ስውር ፈተና እንዲጠብቅሽ እርሱን በመታዘዝ ላይ እንዲያግዝሽ ፤ በሐቁ ላይ እንዲያጸናሽ አላህን እማጸናለሁ፡፡ እነሆ አሏህ ዱዓን ሰሚና ተቀባይ ነውና ፡፡

#ዐብዱልከሪም_አልሀናኒ
=====================
@AbdulKereem_AlHanani
@AbdulKereem_AlHanani
=====================
5.1K viewsedited  05:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 08:44:10 ምንኛ ልብ የሚነካ ሀዲስ ነው !!!

------------------------------------------------------- @AbdulKereem_AlHanani
-------------------------------------------------------

አቡዘር አል-ገፋሪ በዘገበው ሓዲስ ነብዩ (ﷺ) ከጌታቸው ሲዘግቡ እንዲህ አሉ፡-

አላህ እንዲህ አለ “
እናንተ ባሮቼ ሆይ! እኔ በደል መፈጸምን በራሴ ላይ እርም አድሪጌዋለሁ። በናንተ መካከልም በደልን መፈጸም እርም አድርጌዋለሁ። ስለዚህ አትበዳደሉ።

እናንተ ባሮቼ ሆይ!እኔ የመራሁት ሲቀር ሁላችሁም ጠማሞች ናችሁ። ስለዚህ ቀጥተኛ መንገድ እንድመራችሁ ለምኑኝ እመራችኋለሁ።

እናንተ ባሮቼ ሆይ!እኔ የመገብኩት ሲቀር ሁላችሁም ረሃብተኞች ናችሁ። እንድመግባቹህ ጠይቁኝ እመግባችኋለሁ።

እናንተ ባሮቼ ሆይ!እኔ ያለበስኩት ሲቀር ሁላችሁም እርቃናችሁ ናችሁ። እንዳለብሳቹህ ጠይቁኝ አለብሳችኋለሁ።

እናንተ ባሮቼ ሆይ!እናንተ ቀንና ለሊት ትሳሳታላችሁ እኔ ደግሞ ወንጀሎችን ሁሉ እምራለሁ። ስለዚህ መሃርታን ጠይቁኝ እምራችኋለሁ።

---------------------------------------------------
@AbdulKereem_AlHanani
-------------------------------------------------------

እናንተ ባሮቼ ሆይ!እናንተኮ እኔን የመጉዳት ደረጃ ደርሳችሁ እኔን መጉዳት አትችሉም ደግሞም እኔን የመጥቀም ደረጃ ደርሳችሁ እኔን መጥቀም አትችሉም።

እናንተ ባሮቼ ሆይ!እናንተ እኮ የመጀመርያችሁ፣ የመጨረሻችሁ፣ ሰዋችሁ፣ ጋኔናችሁ ሁሉ ከናንተ ውስጥ ካለው የአንዱን ጌታን ፈራሂ ልብ ሁላችሁም ቢኖራችሁ ይህ ስልጣኔ ላይ ምንም አይጨምርም።

እናንተ ባሮቼ ሆይእናንተ እኮ የመጀመርያቹህ፣ የመጨረሻችሁ፣ ሰዋችሁ፣ ጋኔናችሁ ሁሉ ከናንተ ውስጥ ካለው የአንዱን ወንጀለኛ ልብ ሁላችሁም ቢኖራችሁ ይህ ስልጣኔ ላይ ምንም አይቀንስም።

እናንተ ባሮቼ ሆይ!እናንተ እኮ የመጀመርያችሁ፣ የመጨረሻችሁ፣ ሰዋችሁ፣ ጋኔናችሁ ሁሉ አንድ ሜዳ ላይ ቆመው ቢጠይቁኝና ሁሉንም የጠየቁኝን ብሰጣቸው፥ ይህ ስልጣኔ ላይ ልክ መርፌ ባህር ላይ ገብቶ ከባህሩ እንደሚያጎድለው ቢሆን እንጂ ምንም አያጎድልም።

እናንተ ባሮቼ ሆይ!ስራችሁን ነው የምቆጥርላችሁ ከዛም በስራችሁ መሰረት እከፍላችኋለሁ። መልካምን ያገኘ አላህን ያመስግን ከዚህ ውጭ ሌላን ነገር ያገኘ ግን ራሱን እንጂ ሌላን አይውቀስ።”

ሐዲሱን ሙስሊም ዘግቦታል።

#ዐብዱልከሪም_አልሀናኒ
=====================
@AbdulKereem_AlHanani
@AbdulKereem_AlHanani
=====================

አላህ አንብበው ከሚጠቀሙት ያድርገን !!!!!!

https://t.me/AbdulKereem_AlHanani
5.5K viewsedited  05:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 22:42:54 ምርጥ መልዕክት ከሐዲስ !!! ከዚህ በላይ ብስራት አለ እንዴ ?

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ عَنْ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ: "مَنْ نَفَّسَ عَنْ مُؤْمِنٍ كُرْبَةً مِنْ كُرَبِ الدُّنْيَا نَفَّسَ اللَّهُ عَنْهُ كُرْبَةً مِنْ كُرَبِ يَوْمِ الْقِيَامَةِ، وَمَنْ يَسَّرَ عَلَى مُعْسِرٍ، يَسَّرَ اللَّهُ عَلَيْهِ فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ، وَمَنْ سَتَرَ مُسْلِما سَتَرَهُ اللهُ فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ ، وَاَللَّهُ فِي عَوْنِ الْعَبْدِ مَا كَانَ الْعَبْدُ فِي عَوْنِ أَخِيهِ، وَمَنْ سَلَكَ طَرِيقًا يَلْتَمِسُ فِيهِ عِلْمًا سَهَّلَ اللَّهُ لَهُ بِهِ طَرِيقًا إلَى الْجَنَّةِ، وَمَا اجْتَمَعَ قَوْمٌ فِي بَيْتٍ مِنْ بُيُوتِ اللَّهِ يَتْلُونَ كِتَابَ اللَّهِ، وَيَتَدَارَسُونَهُ فِيمَا بَيْنَهُمْ؛ إلَّا نَزَلَتْ عَلَيْهِمْ السَّكِينَةُ، وَغَشِيَتْهُمْ الرَّحْمَةُ، وَذَكَرَهُمْ اللَّهُ فِيمَنْ عِنْدَهُ، وَمَنْ أَبَطْأَ بِهِ عَمَلُهُ لَمْ يُسْرِعْ بِهِ نَسَبُهُ"

. رَوَاهُ مُسْلِمٌ [رقم:2699] بهذا اللفظ

.አቡ ሁረይራ በዘገበው ሓዲስ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ አሉ

“ከዱንያ ችግሮች ውስጥ አንድን ችግር ለሙእሚን ያስወገደ አላህ በትንሳኤው ቀን ከችግሮች ውስጥ አንድን ችግር ያስወግድለታል።

ለከበደው ያቀለለ አላህ ደግሞ በዱንያም በአኼራም ያቀልለታል።

የሙስሊም ወንድሙን ነውር የሸፈነ አላህ በዱንያም በአኼራም ነውሩን ይሸፍንለታል።

አንድ ባርያ ሙስሊም ወንድሙን በማገዝ ላይ እስካለ ድረስ አላህ እሱን ከማገዝ አይወገድም።

እውቀትን በመፈለግ መንገድን የተከተለ አላህ የጀነት መንገድን ያቀልለታል።

ሰዎች የአላህን መጽሃፍ እያነበቡ፣ እየተማማሩ በአላህ ቤት ውስጥ አይሰባሰቡም እርጋታ በላያቸው ላይ ቢወርድባቸው፣ እዝነት ቢያካባቸው፣ መላኢኮች ቢያካቧቸው፣ አላህ እርሱ ዘንድ ቢያወሳቸው እንጂ።

ስራው ወደኋላ ያስቀረው ዘሩ (ብሄሩ) ወደፊት አያስቀድመውም።”

ሐዲሱን ሙስሊም ዘግቦታል።

#ዐብዱልከሪም_አልሀናኒ
=====================
@AbdulKereem_AlHanani
@AbdulKereem_AlHanani
=====================
3.5K viewsedited  19:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 07:38:52 قال الأوزاعي رحمه الله:

اصبر نفسك على السنة، وقف حيث وقف القوم، وقل بما قالوا، وكف عما كفوا، واسلك سبيل سلفك الصالح، فإنه يسعك ما وسعهم
‏شرح اعتقاد أهل السنة للالكائي
( 315 )

አሏህ ይዘንላቸወና ኢማሙል አውዛዒይ እንድህ አሉ

ነፍስህን በሱና ላይ እንድትታገስ አድርጋት፥ሠሀቦችና ደጋግ ቀደምት ህዝቦች ከቆሙበት ቁም፣እነሱ የተናገሩበት ላይ ተናገር፣እነሱ ዝም ያሉበት ላይ ዝም በል፣ደጋግ ቀደምቶች በተጓዙበት ተጓዝ፣እነሱን የሰፋቸው ይሰፋሃልና .
2.2K viewsedited  04:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ