Get Mystery Box with random crypto!

⚡️ Kerem Bedrudin ⚡️ ዐብዱል ከሪም_አልሀናኒ⚡️

የቴሌግራም ቻናል አርማ abdulkereem_alhanani — ⚡️ Kerem Bedrudin ⚡️ ዐብዱል ከሪም_አልሀናኒ⚡️
የቴሌግራም ቻናል አርማ abdulkereem_alhanani — ⚡️ Kerem Bedrudin ⚡️ ዐብዱል ከሪም_አልሀናኒ⚡️
የሰርጥ አድራሻ: @abdulkereem_alhanani
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.94K
የሰርጥ መግለጫ

وَقُلْ جَاءَ الْحَقُّ وَزَهَقَ الْبَاطِلُ ۚ إِنَّ الْبَاطِلَ كَانَ زَهُوقًا

በልም «እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና፡፡»
ለማንኛውም አስተያየትና ጥቆማ ከታቺ ያድርሱኝ
☞ @Abdulkereem_alhanani_bot

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-07-24 08:08:17 ገንዘብን የመስጠት ጥቅም

ገንዘብን በኢክላስ የሰጠ ሰው አሳማሚ ከሆነ ቅጣት እንደሚጠብቀው እና ትልቅ ምንዳ እንደሚመነዳው እንዲሁም ፍርሀትና ሀዘንም እንደሌበት አሏህ ነግሮናል

አሏህ እንዲህ ይላል

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا هَلْ أَدُلُّكُمْ عَلَىٰ تِجَارَةٍ تُنجِيكُم مِّنْ عَذَابٍ أَلِيمٍ


«እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከአሳማሚ ቅጣት የምታድናችሁ የኾነችን ንግድ ላመላክታችሁን?» (በላቸው)፡፡


تُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ وَتُجَاهِدُونَ فِي سَبِيلِ اللَّهِ بِأَمْوَالِكُمْ وَأَنفُسِكُمْ ۚ ذَٰلِكُمْ خَيْرٌ لَّكُمْ إِن كُنتُمْ تَعْلَمُونَ


(እርሷም) በአሏህና በመልክተኛው ታምናላችሁ፣ #በአሏህ #መንገድም #በገንዘቦቻችሁ #በነፍሶቻችሁም #ትታገላላችሁ፣ #ይህ #የምታውቁ #ብትኾኑ #ለእናንተ #የተሻለ ነው፡፡


الَّذِينَ يُنفِقُونَ أَمْوَالَهُم بِاللَّيْلِ وَالنَّهَارِ سِرًّا وَعَلَانِيَةً فَلَهُمْ أَجْرُهُمْ عِندَ رَبِّهِمْ وَلَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ

#እነዚያ #ገንዘቦቻቸውን #በሌሊትና #በቀን #በድብቅም #በግልጽም #የሚለግሱ #ለእነርሱ #በጌታቸው #ዘንድ #ምንዳቸው #አላቸው፡፡ በእነርሱም ላይ #ፍርሃት #የለባቸውም #እነርሱም #አያዝኑም፡፡

➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾➾
ስለሆነም ገንዘባቺንን በመስጠት ላይ እንበርታ !!!!

#አብዱልከሪም_አልሀናኒ
=====================
@AbdulKereem_AlHanani
@AbdulKereem_AlHanani
=====================
3.0K viewsedited  05:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 16:05:54 ሙዓዝ ኢብን ጀበል ለነብዩ (ﷺ) ጀነት አስገብቶ ከእሳት የሚያርቀኝን ስራ ንገሩኝ አላቸው።

እሳቸውም እንዲህ አሉ፦”በእርግጥም ትልቅ ነገር ጠይቀሃል። ነገሩ ደግሞ አላህ ላቀለለለት ቀላል ነው።

አላህን ምንም ሳታጋራ ታመልከዋለህሶላትን ቀጥ አድርገህ ትሰግዳለህዘካን ታወጣለህረመዳንን ትጾማለህየአላህን ቤት ትጎበኛለህ።”

ከዚያም እንዲህ አሉ “የመልካም በሮችን ላመላክትህ ?

ጾም ጋሻ ነው። ሰደቃና በሌሊት የሚሰገድ ሶላት ደግሞ ልክ ውሃ እሳትን እንደሚያጠፋው ስህተትን ያጠፋሉ።”

ከዛም ይህንን አነበቡ


تَتَجَافَىٰ جُنُوبُهُمْ عَنِ الْمَضَاجِعِ يَدْعُونَ رَبَّهُمْ خَوْفًا وَطَمَعًا وَمِمَّا رَزَقْنَاهُمْ يُنفِقُونَ

ጌታቸውን ለመፍራትና ለመከጀል የሚጠሩት ሆነው ጎኖቻቸው ከመጋደሚያ ስፍራዎች ይራራቃሉ፡፡ ከሰጠናቸውም (ጸጋ) ይለገሳሉ፡፡


فَلَا تَعْلَمُ نَفْسٌ مَّا أُخْفِيَ لَهُم مِّن قُرَّةِ أَعْيُنٍ جَزَاءً بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ

ይሠሩትም በነበሩት ለመመንዳት ከዓይኖች መርጊያ ለእነርሱ የተደበቀላቸውን (ጸጋ) ማንኛይቱም ነፍስ አታውቅም ፡፡

ከዚያም እንድህ አሉ ሰለ ነገሮች ሁሉ ራስ፣ ስለ ምሶሰው እና ስለ ሻኛው ጫፍ ምን እንደሆኑ አልነግርህምን ?” አዎን ንገሩኝ አለ። ነብዩ (ﷺ) እንዲህ አሉ “

የነገራት ሁሉ ራስ እስልምና ነው። ምሶሰውም ሶላት ነው። የሻኛው ጫፍ ደግሞ ጅሃድ ነው።

ከዚያም እንዲህ አሉ “ይህንን ሁሉ ጠቅልሎ የሚይዘውን አልነግርህምን ?” አዎን ንገሩኝ አለ።

ምላሳቸውን ያዙና “ይህንን ተጠንቀቅ” አሉ። እኔም በምንናገረው ነገር እንጠየቃለን እንዴ አልኳቸው?እሳቸውም “እናትህ ትጣህና (እንዲከሰት ተፈልጎ አይደለም ልብ በሉት)ሰዎች በፊቶቻቸው እሳት ውስጥ የሚወረወሩት በምላሳቸው ውጤት አይደለምን ?”

ሓዲሱን ቲርሚዚይ ዘግቦታል።

#አብዱልከሪም_አልሀናኒ
=====================
@AbdulKereem_AlHanani
@AbdulKereem_AlHanani
=====================
981 views13:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 08:22:20 《 ጥሩ ሙስሊም ሴቶችን ከጥሩ ሴቶች ጋር እንዲቀማመጡ እመክራለሁ። ይህን በማድረጓ ኢማኗን፣ እውቀቷን እና ግንዛቤዋን ትጨምራለች》ይላሉ።

ሸይኽ ሙቅቢል አልዋዲዒይ

غارةالأشرطة ٤٧٤/٢/
955 viewsedited  05:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 23:36:25 ምርጥ መልዕክት ከሐዲስ !!! ከዚህ በላይ ብስራት አለ እንዴ ?

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ عَنْ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ: "مَنْ نَفَّسَ عَنْ مُؤْمِنٍ كُرْبَةً مِنْ كُرَبِ الدُّنْيَا نَفَّسَ اللَّهُ عَنْهُ كُرْبَةً مِنْ كُرَبِ يَوْمِ الْقِيَامَةِ، وَمَنْ يَسَّرَ عَلَى مُعْسِرٍ، يَسَّرَ اللَّهُ عَلَيْهِ فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ، وَمَنْ سَتَرَ مُسْلِما سَتَرَهُ اللهُ فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ ، وَاَللَّهُ فِي عَوْنِ الْعَبْدِ مَا كَانَ الْعَبْدُ فِي عَوْنِ أَخِيهِ، وَمَنْ سَلَكَ طَرِيقًا يَلْتَمِسُ فِيهِ عِلْمًا سَهَّلَ اللَّهُ لَهُ بِهِ طَرِيقًا إلَى الْجَنَّةِ، وَمَا اجْتَمَعَ قَوْمٌ فِي بَيْتٍ مِنْ بُيُوتِ اللَّهِ يَتْلُونَ كِتَابَ اللَّهِ، وَيَتَدَارَسُونَهُ فِيمَا بَيْنَهُمْ؛ إلَّا نَزَلَتْ عَلَيْهِمْ السَّكِينَةُ، وَغَشِيَتْهُمْ الرَّحْمَةُ، وَذَكَرَهُمْ اللَّهُ فِيمَنْ عِنْدَهُ، وَمَنْ أَبَطْأَ بِهِ عَمَلُهُ لَمْ يُسْرِعْ بِهِ نَسَبُهُ"

. رَوَاهُ مُسْلِمٌ [رقم:2699] بهذا اللفظ

.አቡ ሁረይራ በዘገበው ሓዲስ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ አሉ

“ከዱንያ ችግሮች ውስጥ አንድን ችግር ለሙእሚን ያስወገደ አላህ በትንሳኤው ቀን ከችግሮች ውስጥ አንድን ችግር ያስወግድለታል።

ለከበደው ያቀለለ አላህ ደግሞ በዱንያም በአኼራም ያቀልለታል።

የሙስሊም ወንድሙን ነውር የሸፈነ አላህ በዱንያም በአኼራም ነውሩን ይሸፍንለታል።

አንድ ባርያ ሙስሊም ወንድሙን በማገዝ ላይ እስካለ ድረስ አላህ እሱን ከማገዝ አይወገድም።

እውቀትን በመፈለግ መንገድን የተከተለ አላህ የጀነት መንገድን ያቀልለታል።

ሰዎች የአላህን መጽሃፍ እያነበቡ፣ እየተማማሩ በአላህ ቤት ውስጥ አይሰባሰቡም እርጋታ በላያቸው ላይ ቢወርድባቸው፣ እዝነት ቢያካባቸው፣ መላኢኮች ቢያካቧቸው፣ አላህ እርሱ ዘንድ ቢያወሳቸው እንጂ።

ስራው ወደኋላ ያስቀረው ዘሩ (ብሄሩ) ወደፊት አያስቀድመውም።”

ሐዲሱን ሙስሊም ዘግቦታል።

#አብዱልከሪም_አልሀናኒ
=====================
@AbdulKereem_AlHanani
@AbdulKereem_AlHanani
=====================
1.0K views20:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 18:01:14 የጀመአ ሰላት ጥቅም

"አቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል:-

‹‹አንድ ሰው በጀመዓ (በህብረት) የሚሰግዳት ሶላት ከስራ ቦታው ወይም ከቤተሰቡ ከሚሰግድባት ሶላት ከሀያ ሶስት እስከ ሰላሳ ብልጫ አላት ይህም የሚሆነው በተሟላ መልኩ ውዱዕ ከፈፀመና ከዚያም ሰላትን እንጂ ሌላን ባለመሻት ከቤቱ የወጣበት አላማ ሶላት ብቻ ሆኖ ወደ መስጊድ ከመጣ ነው::


ወደ መስጊድ በሚያደርገው ጉዞ በእያንዳንዱ እርምጃ አንድ ደረጃ ከፍ ይደረግለታል::

በዚያችው እርምጃ አንድ ኃጢአት ይታበስለታል፡፡

መስጊድ እስኪገባ ድረስ መስጊድ ከገባ በኋላ መስጊድ ውስጥ ለመቆየቱ
ምክንያት ሶላት ብቻ እስከሆነች ድረስ ሶላት ውስጥ እንዳለ ይቆጠርለታል፡፡

ከእናንተ አንዳቹ የሰገደበትን ቦታ እስካለቀቀ ሰዎችን እስካላወከና ውዱእ እስካልፈታ መላይኮች አላህ ሆይ! ምህረትን ለግሰው አላህ ሆይ! ጸጸቱን ተቀበለው እያሉ ዱዓ ያደርጉለታል፡፡››

~ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበዉታል"

#አብዱልከሪም_አልሀናኒ
=====================
@AbdulKereem_AlHanani
@AbdulKereem_AlHanani
=====================
1.9K views15:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 11:37:20 እንደ ታዘዝከው ቀጥ በል/በይ !

የሰው ልጂ እንደፈለገው ልቅና ገደብ አልባ መሆን የለበትም የታዘዘውን መታዘዝ የተከለከለውን መከልከል ያስፈልጋል ፡፡ በአንድ ነገር ላይ ከታዘዝን ወይም ከተከለከልን አሚን ብሎ መቀበልና ቀጥ ብሎ መተግበር ግዴታ ነው ፡፡



አላህ በተከበረው ቃሉ ምን ይለናል ፡


فَاسْتَقِمْ كَمَا أُمِرْتَ وَمَن تَابَ مَعَكَ وَلَا تَطْغَوْا ۚ إِنَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ

እንደ ታዘዝከውም ቀጥ በል፡፡ ከአንተ ጋር ያመኑትም (ቀጥ ይበሉ)፡፡ ወሰንንም አትለፉ፤ እርሱ የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና፡፡


#አብዱልከሪም_አልሀናኒ
=====================
@AbdulKereem_AlHanani
@AbdulKereem_AlHanani
=====================
2.3K views08:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ