2024-02-15 12:08:36
እግዚአብሔር የረሳን ለምን ይመስለናል?1.
እኛ ስለምንረሳው የመከራ ጽናት የዘመን ብዛት እግዚአብሔር ረስቶኛል ብቻ ሳይሆን (ሎቱ ስብሐት) እግዚአብሔር የለምም ያስብላል። የሰው ልጅ መከራው ጽኑ በሆነ ጊዜ፣ ዘመን በራቀበት ጊዜ፣ ለጥያቄው መልስ ባጣ ጊዜ በእነዚህ በሦስቱ በሃይማኖት እንቅፋት ይገጥመዋል። ስለዚህ እግዚአብሔር ረስቶኛል፣ አይወደኝም ይልና ቀቢጸ ተስፋ ላይ ሲደርስ ደግሞ እግዚአብሔር ባይኖር ነው እንጂ ቢኖርማ ማለት ይጀምራል። በመጨረሻም የለም ብሎ ይክዳል።
ሰይጣን ሰውን ወደ ምንፍቅና ወደ ክህደት የሚወስድባቸው 3ቱን መንገዶች መጠንቀቅ ይገባል። ይህንን ይበልጥ ለመረዳትም የሚከተሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሀሳቦችን እንመልከት:-
ሀ.
"ስለምን ጦምን? አንተም አልተመለከትከንም? ሰውነታችንንስ ስለምን አዋረድን? አንተን አላወቅህም?" (ኢሳ58÷3)
እዚህ ላይ ጹመው ለጥያቄያቸው ምላሽ በማጣታቸው እግዚአብሔርን አልተመለከትከንም፣ አላወቅኸንም እስከማለት ደርሰው ነበር። "የእግዚአብሔር ዓይኖች ምን ሆነው አልተመለከቱም?፣ አይወሰኑ ምሉዓን፣ አይሞቱ ሕያዋን፣ አያዳሉ ጻድቃን ናቸው። ታዲያ ለምን አልተመለከትከንም አሉ?" ብንል መልሱ "ጥያቄያቸው ባለመመለሱ እግዚአብሔር የተዋቸው የገፋቸው የረሳቸው መስሏቸዋል" የሚል ይሆናል።
የፈለጉትን በማጣታቸው በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት እግዚአብሔር የሌለ እየመሰላቸው ወዲያ ወዲህ የሚቅበዘበዙ ወገኖች በዚህ ዘመንም አይታጡም። ግን እግዚአብሔር አላይ ብሎ ሳይሆን እኛ አንታይም አትየን ብለነው ነው። "ገዳም ሄድኩ፣ ንስሐ ገባሁ፣ እጸልያለሁ፣ እጦማለሁ፣ በቅዱሳን አምናለሁ፣ እቆርባለሁ ነገር ግን እስከዛሬ ከነበርኩበት ነኝ ምን ይሻለኛል?" የሚሉ ብዙዎች ናቸው። መልሱን ለእነዚህ ጦመኞች የመለሰውን እንስማ!
"በውኑ ሴት ከማኅፀንዋ ለተወለደው ልጅ እስከማትራራ ድረስ ሕፃንዋን ትረሳ ዘንድ ትቾላለችን? አዎ እርስዋ ትረሳ ይሆናል፣ እኔ ግን አልረሳሽም" ይላል (ኢሳ 49÷15)። እናት 9 ወር ፀንሳ፣ ከደምዋ ተከፍሎ፣ በምጥ በፃዕር በጭንቅ የወለደችውን፣ 3 ዓመት ያጠባችውን፣ ሁሉን ታግሳ በንጽሕና ያሳደገችውን ልጇን ትረሳለችን? አትረሳም። ዳሩ ግን ቢያንስ ሙቶ እንኳን አልቅሳ አልቅሳ ስታንቀላፋ በዕለቱም ቢሆን ትረሳለች። እግዚአብሔር ግን ይህ ሁሉ በባሕርዩ የለበትምና አይረሳም። "እንግዲያውስ ስለምን አልተመለከትከንም ሰውነታችንንስ ስለምን አዋረድን? አንተም አላወቅኸንም?
ጥያቄ:- ስለምን ጦምን? አንተም አልተመለከትከንም ሰውነታችንንስ ስለምን አዋረድን? አንተም አላወቅኸንም?
መልስ.......
ይቀጥላል
ከጸያሔ ፍኖት (በአባ ገብረ ኪዳን) ከገጽ 68-69 የተወሰደ
http://t.me/abagebrekidan
http://t.me/abagebrekidan
13.8K viewsÃńŧęŋəĥ, 09:08