Get Mystery Box with random crypto!

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ ላይ የ10 ቀናት የምርመራ ጊዜ ፈቀ | Zehabesha

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ ላይ የ10 ቀናት የምርመራ ጊዜ ፈቀደ።
ያየሰው የተጠረጠረው “ኹከት እና ብጥብጥ በማነሳሳት ወንጀል” መሆኑን መርማሪ ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ ገልጿል።
“ኢትዮ ፎረም” የተሰኘው የዩቲዮብ መገናኛ ብዙኃን አዘጋጅ የነበረው ያየሰው በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በቁጥጥር ሥር የዋለው ትላንት ሐሙስ ግንቦት 18 ቀን 2014 ነበር። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያየሰውን ዛሬ አርብ ግንቦት 19 ፍርድ ቤት ያቀረበው ሲሆን የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ጠይቆበታል።
ጋዜጠኛ ያየሰውን ወክለው በችሎቱ የተገኙት ጠበቃው ታደለ ገብረመድህን፤ የተጠየቀው የምርመራ ጊዜ ውድቅ ተደርጎ ደንበኛቸው በዋስትና እንዲለቀቅ ጠይቀዋል።
የግራ ቀኙን አስተያየት ያደመጠው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት፤ መርማሪ ፖሊስ የጠየቀውን የምርመራ ጊዜ በአራት ቀናት አሳንሶ 10 የምርመራ ቀናትን መፍቀዱን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።
በጽህፈት ቤት በኩል የተካሄደውን የዛሬውን የችሎት ውሎ ጋዜጠኛ ያየሰው በአካል ተገኝቶ መከታተሉም ታውቋል።