Get Mystery Box with random crypto!

በደቡብ አፍሪካ አንድ ኢትዮጵያዊ ሁለት ፖሊሶችን በሽጉጥ በማቁሰል ተጠርጥሮ ታሰረ፡፡ የኬፕታውን | Zehabesha

በደቡብ አፍሪካ አንድ ኢትዮጵያዊ ሁለት ፖሊሶችን በሽጉጥ በማቁሰል ተጠርጥሮ ታሰረ፡፡
የኬፕታውን ፖሊስ ቃል አቀባይ ኮሎኔል አንድሬ ትራኡት ዛሬ በሰጡት መግለጫ ኢትዮጵያዊው በስርቆት ወንጀል ተጠርጥሮ ሲፈለግ የነበረ ሲሆን በትላንትናው እለት ፖሊሶች አግኝተውት ሊያስሩት ሙከራ አድርገው እንደነበር አስረድተዋል፡፡ በዚህ ሙከራ ወቅት ተጠርጣሪው በሁለቱ ፖሊሶች ላይ ተኩስ በመክፈቱ ሁለቱም መቁሰላቸውንና አሁን በሆስፒታል እየታከሙ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የቆሰሉት የሰላሳ ስድስት አመቱ ሳጅንና የሀያ ስምንት አመቱ ኮንስታብል በአሁኑ ወቅት በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ያስረዱት ቃል አቀባዩ የሰላሳ አንድ አመቱ ኢትዮጵያዊም በጥይት ተመቶ ቆስሎ በእስር ላይ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
መግለጫቸውን ሲቀጥሉም ኢትዮጵያዊው ከሆስፒታል ድኖ ከወጣ በኋላ በመግደል ሙከራ፣ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ በመያዝና በስርቆት ወንጀሎች በፍርድ ቤት ክስ እንደሚቀርብበት የገለፁት ቃል አቀባዩ ይዞት የነበረው ሽጉጥ ያልተመዘገበ መሆኑ መረጋገጡን አመልክተዋል፡፡
ምንጭ፦ ዘሐበሻ የዕለቱ ዜና
ZehabeshaOriginal