Get Mystery Box with random crypto!

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ቡሩንዲ ገቡ! የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ዛሬ ቡሩንዲ መግባታ | YeneTube

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ቡሩንዲ ገቡ!

የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ዛሬ ቡሩንዲ መግባታቸው ተገልጿል፡፡ ፕሬዝዳንቷ ቡጁምቡራ እንደደረሱ በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት ለተለዩት የቀድሞው የቡሩንዲ ፕሬዚዳንት ፒዬሬ ንኩሩንዚዛ የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል፡፡ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት የቀድሞው የቡሩንዲ ፕሬዚዳንት ንኩሩንዚዛ ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ አዲስ አበባ በሚገኘው የቡሩንዲ ኤምባሲ በመገኘትም የአበባ ጉንጉን ማስቀመጣቸው ይታወሳል፡፡

ንኩሩንዚዛ በ55 ዓመታቸው በድንገተኛ የልብ ህመም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይታወሳል፡፡ በፈረንጆቹ 1963 የተወለዱት ንኩሩንዚዛ እ.ኤ.አ ከ2005 ጀምሮ ህይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ ቡሩንዲን መርተዋል።ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ በሁለቱ ሀገረታት እና በቀጣናዊ ጉዳዮች ከቡሩንዲ መሪዎች ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

[Al-ain]
@YeneTube @FikerAssefa