Get Mystery Box with random crypto!

በኢትዮጵያ ወደ ሰሜንና ሰሜን ምዕራብ አንዳንድ ከተሞች ተቋርጦ የነበረው የአየር በረራ ተጀመረ! | YeneTube

በኢትዮጵያ ወደ ሰሜንና ሰሜን ምዕራብ አንዳንድ ከተሞች ተቋርጦ የነበረው የአየር በረራ ተጀመረ!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተፈጥሮ ሰሞኑን ተፈጥሮ ነበር ባለው አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ምክንያት ተቋርጦ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በሚገኙ አብዛኞቹ ከተሞች የአየር በረራ ማቋረጡን አስታውቆ ነበር።ነገር ግን ዛሬ እንደተሰማው ከአዲስ አበባ ባህርዳር፣ ጎንደር እና ላሊበላ የአየር በረራ ትናንት መጀመሩን አየር መንገዱና ተሳፋሪዎች ገልፀዋል፡፡

አንድ የአየር መንገዱ ባልደረባ ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት ሰሞኑን ተፈጥሮ በነበረው ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ ምክንያት ከአርብ ከሰኣት ጀምሮ ከአዲስ አበባ ባህር ዳር፣ ጎንደርና ላሊበላ ይደረጉ የነበሩ በረራዎች ተቋርጠው ቆይተዋል፡፡ይሁን እንጂ የአየር ሁኔታው የተሰተካከለ በመሆኑ እሁድ ወደ ላሊበላ በረራ መጀመሩን፣ ባህርዳርና ጎንደር ደግሞ ትናንት ሰኞ የበረራ አገልግሎት መቀጠሉን ገልፀዋል፡፡አንድ ከአዲስ አበባ ወደ ባህር ዳር ለመምጣት ሲጠባበቁ የነበሩ የአየር መንገዱ ደንበኛ ትናንት በረራ መጀመሩ ከአየር መንገዱ ተነግሯቸው በነበረው የበረራ መስተጓጎል በተፈጠረ ወረፋ በረራቸው ተዛውሮ ዛሬ ባሕር ዳር መግባታቸውን ለዶይቼ ቬለ በስልክ ተናግረዋል፡፡

የዶይቼ ቬለ ዘጋቢ እንዳረጋገጠውም ከትናንትና ጀምሮ በባህር ዳር አውሮፕላን ማረፊያ አውሮፕላኖች እየተነሱ ሲያርፉ ነበር፡፡ሆኖም ያለው የአየር ሁኔታ ሞቃታማነቱን እየጨመረ ስለሚሄድ በቅርቡ ተመሳሳይ የአየር ሁኔታ ለውጥ ሊኖር እንደሚችል በኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ አጀንሲ የባህር ዳር ቅርንጫፍ የትንበያና ትንተና ቡድን አስተባባሪ አቶ ጥላሁን ውቤ የትንበያ ሪፖርቶችን ጠቅሰው ተናግረዋል፡፡

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa