Get Mystery Box with random crypto!

የዓለም ጤና ድርጅት ኮቪድ የመጣው ከውሃን ቤተ ሙከራ ሳይሆን ከእንስሳት መሆኑን አስታወቀ! የዓለ | YeneTube

የዓለም ጤና ድርጅት ኮቪድ የመጣው ከውሃን ቤተ ሙከራ ሳይሆን ከእንስሳት መሆኑን አስታወቀ!

የዓለም ጤና ድርጅት የኮሮና ቫይረስ መነሻ ከውሃን ቤተ ሙከራ ሳይሆን ከእንስሳት መሆኑን በጥናቱ አረጋገጠ፡፡የድርጅቱ ልዑክ ቻይና በመገኘት የኮሮና ቫይረስን መነሻ ሲያጠና መቆየቱ ይታወቃል፡፡የልዑክ ቡድኑ መሪ ፒተር ቤን ኢምባረክ መነሻውን ለማወቅ ተጨማሪ ስራዎች መሰራት እንዳለባቸውም ገልጸዋል፡፡ጥናቱን የድርጅቱ ልዑክ እና ቻይና የጤና ኮሚሽን በጋራ ማጥናታቸው ነው የተነገረው፡፡ውሃን በቻይና ምዕራባዊ ሁቤ አውራጃ የምትገኘ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ኮሮና ቫይረስ የተገኘባት ከተማ መሆኗ ይታወሳል፡፡ባለሙያዎች ወረርሽኙ ወደ ሰዎች ከመሰራጨቱ በፊት ከእንስሳ እንደመጣ ቢያምኑም እንዴት ሊከሰት እንደቻለ እርግጠኞች አይደሉም ተብሏል፡፡

(ኤፍ ቢ ሲ)
@YeneTube @FikerAssefa