Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሰራተኞቹ ጥቅማ ጥቅም የሚያስገኝ ስምምነት ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ማህበር | YeneTube

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሰራተኞቹ ጥቅማ ጥቅም የሚያስገኝ ስምምነት ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ማህበር ጋር ተስማማ!

ስምምነቱ የባንክ ብድር አገልግሎት በማመቻቸት ሰራተኞች ጥቅማ ጥቅም ያገኙ ዘንድ የሚያስችል ነው።አየር መንገዱ ወደ 17ሺ የሚጠጉ ሰራተኞች ያሉት ሲሆን ፤ ከዚህ ቀደም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር የነበረው ስምምነት ለሁሉም ሰራተኞች ተደራሽ አልነበረም ተብሏል።በመሆኑም የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ጋር የተደረገው ስምምነት ሁሉም ሰራተኞችን ተጠቃሚ ሊያደርግ ታሳቢ ያደረገ ነው ሲሉ የአየር መንገዱ ቀዳማዊ መሰረታዊ ሰራተኛ ማህበር ፕሬዚዳንት ኢ/ር ተሊላ ደሬሳ ተናግረዋል።

ስምምነቱ አብዛኛው ሰራተኛ በተሻለ መልኩ የቤት፣ተሽከርካሪ እና ሌሎችም ጥቅማ ጥቅሞችን እንዲያገኙ ያስችላል።የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገ/ማርያም ይህ ስምምነት እውን ይሆን ዘንድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውንም በመድረኩ ገልፀዋል። ኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንኩም ይህንኑ ሲቀርብላቸው ከሌሎች ባንኮች ይልቅ ሃሳቡን በመቀበል ስምምነቱ እውን እንዲሆን በማስቻሉ ለባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ደርቤ አስፋው ምስጋና ቀርቧል።

በዚህ በኮቪድ 19ወረርሽኙ በቅት ታላላቅ አየር መንገዶች ሰራተኞቻቸውን ሲያባርሩ ፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግን 1,600 ሰራተኞች ቋሚ እንዲሆኑ ማደረጉንም አንስተዋል።የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ በዚህ በአስቸጋሪ ወቅት ምንም እንኳ የአየር መንገድ ኢንዱስትሪ ቢጎዳም ፤ ያለምንም ድጋፍ አሁንም ስራውን በተገቢው መልኩ ማስቀጠሉን አንስተዋል።ለውጡ እየመጣ የሚገኘው በሰራተኞች ልፋት መሆኑን በመግለፅም ፤ አየር መንገዱ 1,200 ቤቶች ከዚህ ቀደም ለሰራተኛው ሰርቶ አስረክቧል ብለዋል።

@YeneTube @FikerAssefa