Get Mystery Box with random crypto!

ለመጭው ሀገር ዐቀፍ ምርጫ የምርጫ ክልል እና የዞን ማስተባበሪያ ቢሮዎችን አዘጋጅተው ለቦርዱ ባላስ | YeneTube

ለመጭው ሀገር ዐቀፍ ምርጫ የምርጫ ክልል እና የዞን ማስተባበሪያ ቢሮዎችን አዘጋጅተው ለቦርዱ ባላስረከቡ የክልል መስተዳድሮች በተቀመጠው የጊዜ መርሃ ግብር የዕጩዎች ምዝገባ እንደማያካሂድ ዛሬ ለመገናኛ ብዙኀን በላከው መግለጫ አስታውቋል። እስካሁን የክልል እና ዞን የምርጫ ቢሮዎችን ባላሳወቁት አማራ፣ አፋር፣ ሱማሌ፣ ደቡብ እና ሲዳማ ክልሎች፣ የዕጩዎች ምዝገባ፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች ሥልጠና እና የምርጫ ቁሳቁሶች ስርጭት ማከናወን አልቻልኩም- ብሏል ቦርዱ። በተጠቀሱት ክልሎች ሌላ ጊዜ የዕጩዎች ምዝገባ እንዲደረግ፣ እስከ የካቲት 5 ቢሮዎችን እንዲያሳውቁም አሳስቧል።

@YeneTube @FikerAssefa