Get Mystery Box with random crypto!

የኖርዌይ ስደተኞች ካውንስል በትግራይ ክልል ለስደተኞች የገነባኋቸው ሕንጻዎች ወድመውብኛል ወይም ከ | YeneTube

የኖርዌይ ስደተኞች ካውንስል በትግራይ ክልል ለስደተኞች የገነባኋቸው ሕንጻዎች ወድመውብኛል ወይም ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል ሲል ዛሬ ባሰራጨው መግለጫ አውግዟል።

በሒጻጽ እና ሽመልባ የኤርትራዊያን ስደተኛ ጣቢያዎች፣ በቅርብ ሳምንታት አንድ ትምህርት ቤት እና ክሊኒክም እንደወደሙ የድርጅቱ ዋና ሃላፊ ጃን ኢግላንድ ገልጠዋል። በተቋማቱ እና በዕርዳታ አቅርቦቶች ላይ የደረሰውን ጉዳት መንግሥት እና ለጋሽ ሀገራት እንዲያጣሩ እና ጥፋተኞችን ተጠያቂ እንዲያደርጉም ድርጅቱ ጠይቋል። ድርጅቱ በምንጭነት የተጠቀመው ግን ተቀማጭነቱን ለንደን ያደረገ ዲ.ኤክስ ኦፕን ኔትወርክ የተባለ ድርጅት ያሰራጫቸውን የሳተላይት ምስሎች ነው። በሌላ በኩል የተመድ ዐለም ምግብ ፕሮግራም በመላው ትግራይ ክልል ለረድዔት ሠራተኞች ተደራሽ እንዲሆን እና የዕርዳታ አቅርቦቱም እንዲያድግ ከመንግሥት ጋር ስምምነት ላይ እንደደረሰ የድርጅቱ ዋና ሃላፊ ዴቪድ ቢዝሊ በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል። አስገዳጅ ሁኔታ ሲያጋጥም የዕርዳታ ማጓጓዣዎች በወታደሮች እንዲታጀቡ ስምምነቱ ይፈቅዳል። መንግሥትም ወደ ክልሉ ለመግባት ፍቃድ ለሚጠይቁ የረድዔት ሠራተኞች አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት ተስማምቷል።

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa