Get Mystery Box with random crypto!

የምርጫ ሥልጠና ያልወሰዱ ፖሊሶች በምርጫ ወቅት ሕግ ለማስከበር አይሰማሩም ተባለ! በምርጫ ወቅት | YeneTube

የምርጫ ሥልጠና ያልወሰዱ ፖሊሶች በምርጫ ወቅት ሕግ ለማስከበር አይሰማሩም ተባለ!

በምርጫ ወቅት ሰላም ለማስከበር በ55,220 የምርጫ ጣቢያዎች የሚሰማሩ የፀጥታ አካላት ተልዕኳቸውን ሳይረዱና አስፈላጊውን ሥልጠና ሳያገኙ እንደማይመደቡ፣ የፌዴራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር አስታወቁ፡፡

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ጄኔራል ዘለዓለም መንግሥቴ ሐሙስ ጥር 27 ቀን 2013 ዓ.ም. በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ‹‹የኮሙዩኒኬሽን መንገዶቻችን ለምርጫ ሰላምና ደኅንነት›› በሚል ርዕስ በተካሄደ ውይይት ላይ፣ ‹‹ምርጫ በመንግሥት ቅድሚያ የሚያገኝ ተግባር ነው፤›› ብለዋል፡፡ ለምርጫው ሰላምና ደኅንነት መጠበቅ የፀጥታ ኃይሉ ሚናውን ለይቶ ይሰማራ ዘንድ፣ መመርያዎችና የሥልጠና ማኑዋሎች ተዘጋጅተዋል ሲሉ አስረድተዋል፡፡

በእነዚህ መመርያዎችና ማኑዋሎች መሠረት ሥልጠናዎች እየተሰጡ እንደሚገኙ፣ ሥልጠናዎችን ያላለፈና ሚናውን ያልለየ አንድም ፖሊስ ሥምሪት እንደማይሰጠው አስታውቀዋል፡፡

የምርጫ ወቅት ደኅንነትን የሚከታተልና የሚመራ ኮሚቴ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መቋቋሙንና በጠቅላይ ሚኒስትሩ የደኅንነት አማካሪ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው እንደሚመራ ያስታወቁት ምክትል ኮሚሽነር ጄኔራሉ፣ ‹‹በዚህ ኮሚቴ ውስጥ የአገር መከላከያ ሠራዊት፣ የክልል ፖሊስ ኮሚሽነሮችና የፌዴራል ፖሊስ በአባልነት ይገኛሉ፤›› ብለዋል፡፡

[Reporter]
@YeneTube @FikerAssefa