Get Mystery Box with random crypto!

ዛሬ በሑመራ ከተማ በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መደበኛ የመማር ማስተማር መጀመሩን የከተማዋ ጊ | YeneTube

ዛሬ በሑመራ ከተማ በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መደበኛ የመማር ማስተማር መጀመሩን የከተማዋ ጊዜያዊ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

በሕግ ማስከበር ሂደቱ ከተማዋ ነፃ ከወጣች በኋላ ማኅበረሰቡ ልጆቹን ወደ ትምህርት እንዲመለሱ ተደጋጋሚ ጥያቄ ማንሳታቸውን የጊዜያዊ አስተዳደሩ ሥራ አስፈፃሚ አባል በሪሁን እያሱ ተናግረዋል፡፡ይሕንን ተከትሎም በከተማዋ ትምህርት ለማስጀመር ጊዜያዊ አስተዳደሩ የተለያዩ ተግባራት ማከናወኑን አስታውቀዋል፡፡

አቶ በሪሁን እንዳሉት በትምህርት ቤቶች የነበሩ ችግሮችን በመለዬት ቁሳቁስ እንዲሟሉ ተደርጓል፤ መምሕራንን በማሟላትም ደመወዝ እስከመክፈል ተደርሷል፡፡ በመሆኑም ዛሬ በአምስት ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ሂደቱ መጀመሩን ተናግረዋል፡፡

የአማራ ክልል መንግሥትም ባለሙያዎችን በመመደብ፣ መምሕራንን በማሟላትና ማኅበረሰቡን በማወያዬት ትምህርት ቤቶችን መልሶ በማደራጀት ሥራው ስኬታማ እንዲሆን ደግፏል ብለዋል፡፡ አሁንም ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ነው አቶ በሪሁን ያስታወቁት፡፡

Via Walta
@YeneTube @FikerAssefa