Get Mystery Box with random crypto!

የቡድን 20 አገሮች የውጭ ዕዳ ክምችት ለተጫናቸው ታዳጊ አገሮች ማቅለያ ካመቻቹት ዕድል በተጨማሪ፣ | YeneTube

የቡድን 20 አገሮች የውጭ ዕዳ ክምችት ለተጫናቸው ታዳጊ አገሮች ማቅለያ ካመቻቹት ዕድል በተጨማሪ፣ ከውጭ የግል አበዳሪዎች ተመሳሳይ የዕዳ ጫና ማቅለያ ኢትዮጵያ ልትጠይቅ እንደምትችል መንግሥት አስታወቀ።

የገንዘብ ሚኒስቴር ባለፈው ሰኞ ጥር 24 ቀን 2013 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው በዓለም አቀፉ የገንብ ተቋም አይኤምኤፍ አማካይነት የቡድን 20 አገሮች እ.ኤ.አ. 
በ2020 አጋማሽ ላይ በከፍተኛ የዕዳ ጫና ውስጥ ለሚገኙ ታዳጊ አገሮች ካመቻቹት የዕዳ ማቅለያ በተጨማሪ የውጭ የግል አባደሪዎች ተመሳሳይ የዕዳ ጫና ማቅለያ እንደሚጠይቅ አስታውቋል። 

መንግሥት ይህንን የሚያደርገው የኢትዮጵያን የውጭ ዕዳ ጫና ለመቀነስ እንደሆነ የገለጸው መግለጫው፣ ከዚህ በተጨማሪ የአገሪቱን የውጭ ዕዳ ጫና ለመቀነስ በዓለም ዓቀፉ የገንዘብ ድጋፍ የተለያዩ ጥረቶችን በማድረግ ላይ እንደሆነ አመልክቷል።

የግል የውጭ አበዳሪዎች ለኢትዮጵያ የሰጡት ብድር የመክፈያ ጊዜ እንዲራዘም ወይም የመክፈያ ጊዜ እፎይታ እንዲሰጡ የሚጠይቀው የኢትዮጵያን የወደፊት የውጭ ብድር የማግኘት ዕድል በሚያስጠብቅ መንገድ እንደሚሆንም ገልጿል። 

[Reporter]
@YeneTube @FikerAssefa