Get Mystery Box with random crypto!

ትናንት በሰሜናዊ ሕንድ በተከሰተው የበረዶ ግግር ናዳ 14 ሰዎች ሲሞቱ ከ 150 በላይ ሰዎች ጠፍተ | YeneTube

ትናንት በሰሜናዊ ሕንድ በተከሰተው የበረዶ ግግር ናዳ 14 ሰዎች ሲሞቱ ከ 150 በላይ ሰዎች ጠፍተዋል!

በሰሜን ህንድ በምትገኘው ኡታራካንድ ግዛት በሁለት የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ፕሮጄክቶች ላይ የበረዶ ግግር ተደርምሶ የጎርፍ አደጋም አስከትሏል፡፡በዚህ የጎርፍ አደጋ እስካሁን የ14 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 150 ሰዎች ደግሞ የደረሱበት አልታወቀም፡፡ ጎርፉ የግድቡን የተወሰነ ክፍል ፣ ዛፎችን ፣ ድንጋዮችን እና ሌሎችንም በመንገዱ ያገኛቸውን ቁሶች እና ሰዎችን እየያዘ ሲምዘገዘግ በወቅቱ የተነሱ ፎቶዎች እና የቪዲዮ ምስሎች ያሳያሉ፡፡የነፍስ አድን ቡድኖች ሌሊቱን በሙሉ የተረፉ ሰዎችን እና አስከሬኖችን ለማግኘት ሲያፈላልጉ ማደራቸውን የሲኤንኤን ዘገባ ያሳያል፡፡ በዋሻ ውስጥ ውስጥ የተጠለፉ 15 ሰዎችን ማትረፍ እንደተቻለም ተገልጿል፡፡

Al ain
@YeneTube @FikerAssefa