Get Mystery Box with random crypto!

@Dawit Teshome

የቴሌግራም ቻናል አርማ yene_berhan — @Dawit Teshome D
የቴሌግራም ቻናል አርማ yene_berhan — @Dawit Teshome
የሰርጥ አድራሻ: @yene_berhan
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 274
የሰርጥ መግለጫ

✔️ ጥጋብ ከእግዚአብሔር የተቀበልነውን ጥበብ ይሰውርብናል ።
✔️_ባልደመቁ ብዕሮቼ፤ የነጠሩ ሀሳቦችን አነሳላቹሀለው
ከእናንተ ሚጠበቀው#join በማለት ቤተሰብ መሆን ብቻ ነው።💓
ለሀሳብ እና አስተያየት ስራዋን ለማቅረብ ከሻቱ 👉ይጠቀሙ @berhan_becha
https://www.facebook.com/100066012890073/posts/14365428117

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-04-24 00:40:37 ትርጉም አለው ለ'ኔ


የትንሣኤውን ቀን ፣ እኔ ሳስበው
ዝም ብዬ አይደለም ፣ ትርጉሙ
ገብቶኝ ነው
ስሜት አይደለችም፣ ይህች ቀን ' ለ'ኔ
ትልቅ ቦታ አላት፣ በህይወት ዘመኔ
ስዎች ባይገባቸው ፣ የመስቀሉ ምስጥር
ቢሳለቁበትም በዚያ ፣ታላቅ ፍቅር
እኔ ይገባኛል የትንሳኤው ክብር
እኔስ ይገባኛል የመስቀሉ ችንክር
በቀራኒዮ ላይ ፣አምላክ ተንገላቶ መራራውን ፅዋ፣ ለኔ ሲል ተግቶ
በዳግም መወለድ ፤በጦር ከወለደኝ
ከማይጠፋው ዘር ፤የራሱ ሊያደርገኝ
አላማ ኖሮት ነው፤ በኔ ላይ ያሰበው
በህይወት ዘመኔ ፣ሊያደርግ የፈቀደው
(ታዲያ!)
ንጉስ በመስቀል ላይ፤ ስለኔ
ሞተልኝ
እኔን ሃጥሀኑን ፣ ከሃጥ ሊያድነኝ
ከአጋንንት መንጋጋ ፣ጥርስ አስመለጠኝ
በቤቱ እንድቆም ዛሬን ሲያኖረኝ
የትንሳኤው ቀን ትርጉሙ ገብቶኝ
ለዚያ ከሳሽ ጠላት እንዲህ አስባለኝ
ተነስቷል ብዬ ፍሪዳን አልሰዋም
ጠጅና ጠላውን ከቤቴ አልጠምቅም
ቡና አላፈላም ጎረቤት አልጠራም
አንድ ቀን አስቤ በፌሽታ አልስቅም
ይህ ታላቅ ቅኔ ትርጉም አለው ለኔ
ድንጋይን ገፍትረ መቃብር ፈንቅለ
አዳፋውን ጨርቅ ከላዬ ላይ ጥለ
ከሞት ስትነሳ ህይወት አለበስከን
በትንሳኤው ቅኔ አዲስ ሰው አረ'ከን
ፋሲካ ትንሳኤ ትርጉም አለው ለ'ኔ


@yene_berhan
#Dawit Teshome
191 views@Dawit5020/2050, 21:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-26 11:53:00 መራራቅ ከ...

ከፍ እንበል ወደላይ
ላፍታ'ኳ ከሰማይ
ዝቅ አንበል ወደ ስር
መርዶውን ለማብሰር
መሀል ሰፋሪ እንሁን ከየትም ላንደመር
ከሰማይ እርቀን ከምድር ተኳርፈን
በራሳችን ስፍር ከሚዛኑ ሆነን
እንገኝ በባዶ
ማይቻለውን ወዶ
ማይነካውን መርጦ
በራስ አለም በውስጠት ተውጦ።
226 views@Dawit5020/2050, 08:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-25 10:06:47 ቅኔ_ነው

ለነጠረ ሃሳብ ፣ ምላሽ ቢዳግተን
አታሎ ማለፊያ ፣ ቅኔ ሆኖ ታየን
አንደበቱ 'ርቱ ፣ ሲያወራ ሚያሳምን
ቃሎቹ ፍካሬ ፣ ሆኖ ከተሰማን
ቅኔ_ነው አልን
ለተራ ፍልስፍና ፣ ሚዛን ለማይደፋ
አመክንዮ የለው ፣ ከረብ ላልተሳፋ
ቅኔ_ነው አልን
የቋንቋ ሊቁ ፣ ገለፃው ከበደ
ቃላትን ባሻው ፣ ይዞ ተራመደ ነጎደ
ሲባል ሲብጠለጠል
ከቅኔ ሳያጋድል ቃሉ ከበረታ
ከለመዱት ዘዬ ተለይቶ ቢመጣ
ቅኔ_ነው አልን ምንሰራው ብናጣ
እኛ ቅኔ ሆነን ሚፈታን ስናጣ
እንቆቅልህ እንጂ ምላሹ ከየት መጣ?
(ምክንያት)
የብዕሩ ቅኔ ፣ ሲፈታ በጥምረት
የመደቡ ውቅር ፣ ከመልሱ ደረሰ
አንዱ በሌላኛው ፣ ከቶ አልኮፈሰ
ብረ ቃል አሰረ
(የህያብ.......)
በገቡበት ማያሶጣ ፣ የድር ቤት የሆነ
ተሰውሮ ያለ ፣ ያለፍቺ የበነነ
ቅኔ ቢዳግተን የሰማነው ሁሉ፤
የተፃፈው ሁሉ
ቅኔ__ነው አልን
እኛ ቅኔ ሆነን

@berhan_becha
217 views@Dawit5020/2050, edited  07:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-23 22:09:35 ሰው

ከማህፀን ሲወጣ፤
ታቅፎ ታዘለ
ጦረኛ ነውና፤
በእቅፏ ዘለለ
ጥቂት እንደቆየ፤
በዳዴ አንፏቀቀ
ተራምዶ ሲቀና፤
መራመድ ዘለቀ
እንደ ጨቅላነቱ ፣ ፈክቶ አልደመቀ
በእርጅናው ተገን ፣ ጉልበት ተመዝምዞ
ጥገኝነት ይዟል ፣ ከራስ ግጭት ይዞ
____
449 views@Dawit5020/2050, 19:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-17 23:28:06 ማንነት

ማን ለምትሉ፣ የማንነት ትርጎም
ፍቺው ላልገባቹ
እኔስ ማን ልበል፣ እናንተስ ማን ናቹ
5020 Dawit
@yenebrhan
Repost#
210 views@Dawit5020/2050, 20:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-03 22:54:44 ጉልበቴ ለመንበርከክ ታከተው፤ እጆቼም ቃሉን ለመያዝ ሰነፉ፣ አእምሮዬም ዛለ፤ ልቤ በጠበኩት ነገር ሳይሆን ባላሰብኩት መንገድ ደከመ፤ የውስጤ ቁስል ወደ ማመርቀዝ ተቀየረ ነገሮችን የመርሳት ችግር እንዳለብኝ ሰመው ለታመመ መንፈስ ምን የሚባል ይሁን?ብቻ በዚህ ሁሉ መሀል ግን አጥርቼ የማውቀው አንድ እውነት አለ እርሱም
እንደገና የአምላኬን ፊት መፈለግና ማምለክ።

እንደገና አምልክሀለወው!
እንደገና...እንደገና.........

@yene_berhan
381 views@Dawit5020/2050, 19:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-24 21:46:47 ብዙ ክርክር ለማሸነፍ በታገልክ ቁጥር ወዳጅነትህን አደጋ ላይ ትጥላለህ።

#አትከራከር!

@yene_berhan
402 views@Dawit5020/2050, 18:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-18 21:08:29
እንግዲያውስ ዳዊት ማነው ምናምን ... ለምትሉ ስለኔ ለማወቅም የምትቋምጡ ነገ በደቡብ ቲቪ ከምሽቱ 2:00 ላይ ከፍሬያማ ስንኞች እንግዳ ስለሆንኩ ቁጭ ብላቹ ኮምኩሙኝ። የማታው ቢያልፋቹ እንኳ ሰኞ ከጥዋቱ 4:00 በድጋሚ ይተላለፋል።
400 views@Dawit5020/2050, edited  18:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-17 20:34:24 ነገርም ሲያበቃ

አንዳንድ ደካማዋች፤
የመኖር ቀሽሞች
ህይወት በከበደች ፣ ፍሬው በመረረ
ገመድ በረኪና ፣ ከውስጡ ጨመረ
እንደኔ አይነቱ ደ'ሞ
ሆኖ በአርምሞ...
ብዕር ከወረቀት ፣ ለማጣመር ያዘ
አንድ ሁለት እያለ ፣ ሁሉን አሰፈረ
በመረጣት ብዕር ፣ በዛች ከበረ


https://t.me/yene_berhan
323 views@Dawit5020/2050, 17:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-15 22:08:33 መለየት!

በዚህ ስል ጭንቀቱ
በዚያም ውጥረቱ
ሳልፈልግ ሳልመርጠው ከቦኛል በውነቱ
ራሴን ለማስከን ስገባ ከቤቱ
ለዘላለም ብሎ አንቀላፍቶ ሸኘኝ
ውጥረት ምናምኑ ዳግም ላያገኘኝ
ከዚች ከንቱ አለም በክብር አረገኝ
264 views@Dawit5020/2050, 19:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ