Get Mystery Box with random crypto!

የማርያም መቀነት

የቴሌግራም ቻናል አርማ yemaryammekenet — የማርያም መቀነት
የቴሌግራም ቻናል አርማ yemaryammekenet — የማርያም መቀነት
የሰርጥ አድራሻ: @yemaryammekenet
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 367
የሰርጥ መግለጫ

...እግዚአብሔር ፍጥረቱን ዳግመኛ በውኃ ሙላት ፈጽሞ ላያጠፋዋስትና የሰጠበት ቃል ኪዳኑ ኪዳነ-ኖኅ ይባላል፤ ይህም ዘለዓለማዊ ምልክቱ በዚህ ዓለም "ቀስተ-ደመና" ሆኖ ይታያል። ...
ኢትዮጵያውያን ወላጆችም ልጃቸው ቀስተ-ደመናውን "የማርያም መቀነት" እያለ እንዲጠራ ያስተምሩታል። ከዚህም ትውፊት የተነሣ...

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-04-07 11:24:12
መጋቢት 29_2014
155 views01184 99400, 08:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-06 22:41:57 ❍●◦─━•°°°•━─◦●❍

ወገኑን በጣም ያኰራል፥
በሰውነቱ  ዐማኑኤል፥
የጌታ ልጅ ነው ባባቱ፥
ለማኝ ናት እንጂ  እናቱ ።

ወልደ እግዚኣብሔርን አግኝቼው፥
ርጥብ ሥጋውን በልቼው፥
ደሙን ጠጥቼ ሥጋውን፥
ምነዋ እሞት ቢሆን ።

ወልደ  አምላክ እንኳ መሞቱ፥
ለኛ  ብሎ ነው ለፍጥረቱ፥
በመለኮቱ ይነሣል፥
አብነቱን ያውቃል ።

ውዳሴ  ማርያም ሲታደል፥
ብርሃንን ለኔ በል።

ውዳሴ ማርያም  ስንማር፥
አግኝተን ነበር ደግ ምስጢር፥
ተገደፈ አሉኝ ተሳሳተ፥
ኦ ' አዳም መሬት አንተ ።

ወድቃ ተሰብራ ያለውሉ፥
ኂሩት ደቃለች አሉ ።

ውሃ ሲሞላ አረምሞ፥
መጠበቅ ያሻል ከዳር ቆሞ፥
የሚያውቀው የለም ምን ቢሆን፥
የሚጠራበትን ቀን።


═─────────────═
ሃሳብ @hadis_comment_bot
@hadis_comment_bot
@hadis_comment_bot
▬▬▬▬◉◉◉◦◦◦◉◉◉▬▬▬▬

ይቀላቀሉ @yemaryammekenet
@yemaryammekenet
@yemaryammekenet
━━━━━━━━━━━━━━━━━
 ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄
134 views01184 99400, 19:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-05 13:56:02 የማርያም መቀነት pinned «▬◉◉◉◦ “መጽሐፈ ጨዋታ”◦◉◉▬ ደመና ሰማይን እንዲሸፍነው ንጉሥም በሰራዊቱ እንደዚያ ነው። ሳማና አብላሊት ለምለም መስለው እንዲለበልቡ መናፍቃንም ሲቀርቧቸው እንደዚያ ናቸው። በቀስታና በዝግታ የተበጀ መዘውር ኋላ ጉልበት ይሆናል። ወረቀት መልካም እርሻ ነው ብዙ ነገር ይዘራልና። ጐታም አይሻ እርሱ ከቶት ይኖራልና። ማር ሁለት ጊዜ ያገለግላል አንድ ጊዜ መጠጥ አንድ ጊዜ መብራት ሆኖ። ምነው ቢሉ የብልሕ…»
10:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-05 13:54:37 የማርያም መቀነት pinned «❍●◦─━መጽሐፈ ጨዋታ (ቅንጫቢ)━─◦●❍ ❝ይሄ ድርሰት ከ150 አመታት በፊት የተጻፈ ውብ የአማርኛ ወግ መጽሐፍ ነው … ከአዲሱ የአንድምታ እትም እነሆ …❞ እግዚአብሔር እስቲሻር ሚካኤል እስቲሞት ምነው በኖርሁኝ? ገብርኤል ሲያንቀላፋ ሩፋኤል ሲደክም ሐሰተኛው ዲያብሎስ ንስሐ ይገባል። ክረምት ሲመጣ ሰማይ እንዲከብድ የጠሉትም ሰው ሲመጣ እንደዚያ ይከብዳል። ዘወትር ከሚያጋድል አህያ…»
10:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-05 12:44:37 ​​❍●◦─━•⊰❀✿❀⊱•━─◦●❍
እግዚአብሔር ፈሪ ነው እኛ ብንበድለው ልጁን ልኮ ቀስ ብለህ ተዛምደህ ና ብሎ በልጁ ታረቀን አሁን ምን ያደርጉኝ መስሎት ነው ለካ በየቤቱ ፍራት አይታጣም እኛ ስለበደልነው የምንከሰውን እርሱ ካሰን።


እንግዴህ ወዲህ ሥጋችን ከሆነ በሰበብ ባስባብ ብለን እርስቱን እንካፈለዋለን ጥቂት ሥጋ እንደ መርፌ ትወጋ እንደሚሉት እንኳን ልጁን ልኮ ተዛመድን።


የክርስቶስ ነገር እጅግ አስቸገረ፤ ልጅ ስለሆነ ይሆን አንድ ጊዜ ተርቤ አላበላችሁኝም ይላል አንድ ጊዜ አምስት እንጀራ ለአምስት ሽህ፥ ሰው አብልቶ አትርፎ ያስነሳል።


ለበሬ ቀንድ አለው ለንጉሥም ዘውድ አለው እረ ለእግዚአብሔር የምንሰጠው ክብር ምንድር ነው አንለይለትምን፤ አምልኮ ስግደት ምሥጋና ለርሱ ነው በጣም አንገዛው አንለማመጠውም። አንታጠቅለትም። ታላቅ ጌታ ሰጭ ነሽ ነውና።


አዳኝም ገዳይም እርሱ ነውና። በሰማይና በምድርም ከርሱ በቀር ሌላ የለም። ሁሉም ከርሱ ነው የተገኘው ሁሉም የሆነው በርሱ ነው። አለ ርሱ ምንም የሆነ የለም ምስጋና ይገባዋል ለዘለዓለሙ አሜን።


እግዚአብሔር ዕሩቅ ነው ጥበቡ አይታይምና እግዚአብሔር ቅርብ ነው ቶሎ ይሰማልና። እግዚአብሔር መኰንን ነው ቶሎ ይፈርዳልና። እግዚአብሔር እንግዳ ነው ቶሎ ወሬ ይሰማልና። እግዚአብሔር ትሑት ነው፤ ሰውን አይንቅምና። እግዚአብሔር መሐሪ ነው ቶሎ ይቅር ይላልና ርኅሩኅ ነው።


እግዚአብሔር ሐኪም ነው። ሁሉን በጥበብ አድርጓልና እግዚአሔር ምስጉን ነው ፀሐይን ጨረቃን ፈጥሮአልና። እግዚአብሔር ክቡር ነው ሰማይና ምድር የርሱ ናቸውና።


እግዚአብሔር ባለ ጸጋ ነው ለሁሉ ይመግባልና። እግዚአብሔር ረቂቅ ነው አይጨበጥምና። እግዚአብሔር ግዙፍ ነው በዓለሙ ሁሉ ሞልቷልና። እግዚአብሔር ብሩህ ነው ጨለማ የለበትምና። እግዚአብሔር ኃያል ነው የሚቋቋመው የለምና።


እግዚአብሔር እሳት ነው እጅግ ያስፈራልና። እግዚአብሔር መካር ነው መጻሕፍትን ሰጥቶናልና። እግዚአብሔር አባት ነው አሳድጐናልና። እግዚአብሔር ወንድም ነው ሰው ሆኖዋልና። እግዚአብሔር ወዳጅ ነው የሆዱን ነግሮናልና።


እግዚአብሔር አገር ነው እንኖርበታለንና። እግዚአብሔር ማርና ሱካር ነው ይጣፍጣልና። እግዚአብሔር ገናን ነው የሚያህለው የለምና። እግዚአብሔር ትልቅ ነው ስፍራ አይበቃውምና። እግዚአብሔር ጥልቅ ነው በዋና አይገኝምና። እግዚአብሔር ፋሲካ ነው ለሁሉ ታርዷልና። እግዚአብሔር ዓመት በዓል ነው። ለሁሉ ደስታ ነውና። እግዚአብሔር ጨው ነው ሁሉን ያጣፍጣልና። እግዚአብሔር ክረምት ነው ሁሉን ያበቅላልና። እግዚአብሔር አይጠረጠርም ሁሉን ያውቃልና። እግዚአብሔር አይዘነጋም በሁሉ ድካም የለበትምና። እግዚአብሔር አይሰጋም የሚሽረው የለምና።


እግዚአብሔር የሰው ሎሌ ነው በክረምት ለማብቀል በበጋ ለማብሰል የተዘጋጀ ነውና። እግዚአብሔር እንግዳ አይደለም ከጥንት የነበረ ነውና። ምስጋና ይሁን ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ጥንት ለነበረ አሁን ሳለ ኋላም ለሚኖር አሜን።




═──━━━━⊱✿⊰━━━━──═

ሃሳብ @hadis_comment_bot

▬▬▬▬▬❀✿❀▬▬▬▬▬

መጽሀፈ ጨዋታ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ

አለቃ ዘነብ ኢትዮጵያዊ

◦◦◦▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬◦◦◦
ይቀላቀሉ @yemaryammekenet

━━━━━━━━━━━━━━━━
 ̄ ̄ ̄ ̄ ̄  ̄ ̄ ̄ ̄ ̄
 ̄─━━━━⊱✿⊰━━━━─ ̄
140 viewsየማርያም_መቀነት, edited  09:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-05 00:04:31
'ሀሁ,,,በስድስት ወር' እንዲሁም 'እናት ዓለም ጠኑ'
ከጸጋዬ ገብረመድኅን
‘’. . .ይይዙብኝ ነገር፣ ያስሩብኝ፣ ይሰቅሉብኝ ሰበብ ቢያጡ ጀግና ነህ ብለዉ ከጀግና አቆራኝተዉ ገረፉኝ እንጂ እኔ ጀግና አይደለሁም!!’’
‘’. . .ልጆቻችን የነጻነት ግብሩን ሳይሆን ተረቱን እንዳወረስናቸዉ ባወቁብን በነቁብን ፈረድንባቸዉ፡፡. . .’’
‘’. . .አፍአዊ ሆንን፡፡ሕያዊ ሳንሆን አፍአዊ ቃለ-ሕይወት ሳንሆን ብኩን ቃለ--አፍ ብቻ. . . እንጂ ቤታችን አንድ ነዉ፡፡ቤት ብለን ለልጆቻችን ያወረስናቸዉ ፍቅር የሞተበት ቤታችን አንድ ነዉ፡፡ አባቶቻችን ልባም እኛ አፋም ‘እሳት ዐመድ ወለደ’ ሆንን እንጂ ቤታችንስ አንድ ነዉ፡፡. . . ነጻነት ብለን ባርነት፣ ሕይወት ብለን ሞት ለልጆቻችን አወረስን፡፡ብኩን ቃለ-አፍ፡፡ ፍቅር ብለን ንፍገት፣ ጀግንነት ብለን ፍርሃት ከተብናቸዉ፡፡ በወረረን ባእድ ሞት ማግሥት አዲስ ተስፋ ለተራበ ኅልዉና አዲስ ያገር ዉስጥ ሞት ለአዲስ ትንሳኤ በቃተተ ዓይን አዲስ መቃብር ከፈትን፡፡ አፍአዊ-- ጋዜጣዊ ብኩን የሃሰት ነጻነት ዘረጋን፡፡ ልጆቻችን በተስፋ ልክፍት ቃትተዉ መከኑ፡፡. . .’’
(ከእናት ዓለም ጠኑ ዳምበል ከሚናገረዉ ቃለ ተዉኔት ላይ የተቆነጠረ)
‘’. . .በ…በ…ፊደል ነዉየተለከፍኩት፡፡ በ…በ…በሀ…በሀ…በ..በ..በ..በሁ…በ.. በፊደል ነዉ የተለከፍኩት፡፡ አ…አ…አባዬ ነዉ ያስለከፈኝ፡፡ ተ…ተማር ሲለኝ፤ ሰዉ ሁን ሲለኝ፤ካ…ካልተማረ ደ…ደሀ ሰዉ..አ..አይሆንም ሲለኝ በ…በልጅነት አስለከፈኝ፡፡በ…በፊደል ቃልበ..በብርሀኑ፤በ…በነጻነቱ ተ…ተስፋ ነዉ ያስለከፈኝ፡፡ በ..በ…በፊደል በቀርበ…በትምህርት፤በበ.
.በ …በተስፋ በ..በቀር ነ…ነጻነት የለህም ሲለኝ፤ገ…ገና በ…በጨቅላ በ…በጋሜ አ..አ…አስለከፈኝ፡፡. . .’’
(ሀሁ በስድስት ወር ላይ ከሰሙ ቃለ ተዉኔት ላይ የተቆነጠረ)
1.3K views01184 99400, 21:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-05 00:03:40
ሙላ ነስሩዲን ከአንድ ሰው ላይ ፈረስ ለመግዛት ይስማማል። ሻጩ ግን ፈረሱን የምሸጥልህ አንድ ነገር ቃል ከገባህልኝ ነው ይለዋል። እሱም እኔ ፈረሴን በየቀኑ አራት ቁና እህል ነው የማበላው፤ አንተም በየቀኑ አራት ቁና እህል የምታበላው ከሆነ ውሰደው ይለዋል። ነስሩዲንም ይሄማ ቀላል ነው እንዳልከኝ አደርጋለሁ ብሎ ፈረሱን ወሰደ።

ከጥቂት ግዜ በኋላ ነስሩዲን እና ሻጩ መንገድ ላይ ተገናኙ። ሰውየው" ፈረሴ እንዴት ነው" ሲል ጠየቀው። ነስሩዲን" አይ ሞተ እኮ "አለው። "እንዴት?" አለው። መጀመርያ እንዳልከኝ አራት ቁና ሳበላው ነበር፤ ቀጥሎ እስኪ በሶስት ቁና ልሞክረው ብዬ ሞከርኩት። በሶስትም ይኖራል።እንዲህ ከሆነማ እስኪ ደግሞ በሁለት ልሞክረው ብዬ በሁለትም ስሞክረው ይኖራል።እንዲህ ከሆነማ በአንድም ይኖራል ብዬ በአንድም ስሞክረው ይኖራል።እንዲህ ከሆነማ ይሄ ፈረስ በባዶም ይኖራል ብዬ በባዶ ስሞክረው ሞተ አለው።
155 views01184 99400, 21:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-27 23:01:10 የሳማ ሰንበት ታሪካዊ ገዳም
ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ
የሳማ ሰንበት ታሪካዊ ገዳም ከምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ዋና ከተማ ከአረርቲ 21ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ሳማ የሚባል የገጠር ቀበሌ ዉስጥ ይገኛል፡፡ ይህ ገዳም የክርስቶስ ነገረ-ምጽዓት መታሰቢያ በዓል የሚከበርበት ሲሆን እንደ ሃገራችን ኢትዮጵያ ብቸኛዉ ክብረ በዓል ነዉ፡፡በዓሉም በመጋቢ ወር የአብይ ፆም እኩሌታ/ደብረዘይት/ ላይ የሚከበር ሲሆን ዘንድሮም መጋቢት 26/2013 ዓ.ም እሁድ ቀን ይከበራል፡፡ ገዳሙ ከ300 ዓመት በላይ እንዳስቆጠረ የታሪክ ፀሀፍት ይናገራሉ፡፡ገዳሙ በግራኝ መሃመድ ወረራ ጊዜ በጦርነቱ ምክንያት ካህናትና ቀሳዉስት ሲሰደዱ ፅላቱን ለማዳን ሲሉ ሙገሬዛላ በተባለ ስፍራ አንድ ትልቅ የጥድ ዛፍ ዉስጡን ሰንጥቀዉ(ቦርቡረዉ) በዚያ ይደብቁታል፣ከብዙ ግዜ ቆይታ በኋላ በአካባቢዉ የሚኖር አንድ አርሶ አደር ባልታወቀ ምክንያት የጥድ ዛፉን ለመቁረጥ ሲሞክር ከዛፉ ዉስጥ ወተትና ደም በማየቱ ተደናግጦ ለአካባቢዉ ህዝብና ለካህናት ሄዶ ይናገራል፡፡ ዛፉም ሲቆረጥ በዉስጡ ፅላት ገኛል ጽላቱም እንዲወጣ ከተደረገ በኋላ ታቦተ ህጉን በዘመኑ ለነበሩት ንጉስ ሳህለ ስላሴ ቤተ-መንግስት ድረስ በመዉሰድ እንዳስረከቡና ፅላቱም እዛዉ ንኮበር ቤተ መንግስት ልዩ ስፍራ ተሰቶት እዲቀመጥ ቢደረግም ፅላቱ አልረጋ ይላቸዋል፡፡ ካህናት ተጠርተዉ ፅላቱ የትቢተከል እንደሚረጋ ቢጠይቋቸዉ ካህናቱም ሱባኤ ገብተዉ (ጠቦ) ከተባለ ስፍራ በዋሻ ዉሰጥ የሚኖሩ 3 ባህታዉያን እንዳሉና ከነሱ ለአንዳቸዉ ፅላቱን ሰተዋቸዉ ቢተክሉት እንደሚረጋ ለንጉሱ ነገሯቸዉ፡፡ ንጉሱም በባለሟሎቻቸዉ አማካኝነት ጠቦ ወንዝ (ሳማ) አካባቢ ሲተክሉት እንደፀናላቸዉ ይነገራል፡፡ይህ ታሪካዊ ገዳም በጣልያን ፋሽሽት ወረራ ግዜ ነሓሴ 16 እና ጥቅምት 12 ቀን 1929 ዓ.ም
ወደ 66 ቦንቦች ተጥለዉበት በገቢረ ታምሩ ሳይቃጠል ተርፏል፡፡ እንዲሁም በዚህ ገዳም አካባቢ በሚገኝ ፀበል አማካኝነት በርካታ ህሙማን ከልዩ ልዩ ደዌ ፈዉስ እንዳገኙ ይናገራሉ፡፡ መምህር አባ ገብረ ህይወት የገዳሙን ሲያሰሩ ከእየሩስአሌም ድረስ ከጌታችን መዳኒታችን እየሱስ ክርስቶስ መቃብር አፈር ከተጠመቀበት ዮርዳኖስ ባህር ፀበል አስመጥተዉ መሰረት ማኖራቸዉን አባቶች ይናገራሉ፡፡ ይህ ታሪካዊ ገዳም በክብረ በአል ጊዜ ከተለያ የሀገራችን ክፍል የሀይማኖቱ ተከታዮች ለንግስ ይገኙበታል፡፡ ምንጭ
የኢትዮጵያ-ኦርቶዶክስ-ተዋህዶ-ዜናዎች-
173 viewsHaile Desalegn, 20:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-24 09:41:56
በደብራችን ከፊታችን ረቡዕ ጀምሮ የሚካሄደውን ዐውደ ወንጌል ዘተዋሕዶ የአንድነት ጉባኤ ላልሰማውና ላላየው እንድታደርሱልን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን
189 viewsHaile Desalegn, 06:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-14 18:00:40
149 viewsbini ba, 15:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ