Get Mystery Box with random crypto!

​​❍●◦─━•⊰❀✿❀⊱•━─◦●❍ እግዚአብሔር ፈሪ ነው እኛ ብንበድለው ልጁን ልኮ ቀስ | የማርያም መቀነት

​​❍●◦─━•⊰❀✿❀⊱•━─◦●❍
እግዚአብሔር ፈሪ ነው እኛ ብንበድለው ልጁን ልኮ ቀስ ብለህ ተዛምደህ ና ብሎ በልጁ ታረቀን አሁን ምን ያደርጉኝ መስሎት ነው ለካ በየቤቱ ፍራት አይታጣም እኛ ስለበደልነው የምንከሰውን እርሱ ካሰን።


እንግዴህ ወዲህ ሥጋችን ከሆነ በሰበብ ባስባብ ብለን እርስቱን እንካፈለዋለን ጥቂት ሥጋ እንደ መርፌ ትወጋ እንደሚሉት እንኳን ልጁን ልኮ ተዛመድን።


የክርስቶስ ነገር እጅግ አስቸገረ፤ ልጅ ስለሆነ ይሆን አንድ ጊዜ ተርቤ አላበላችሁኝም ይላል አንድ ጊዜ አምስት እንጀራ ለአምስት ሽህ፥ ሰው አብልቶ አትርፎ ያስነሳል።


ለበሬ ቀንድ አለው ለንጉሥም ዘውድ አለው እረ ለእግዚአብሔር የምንሰጠው ክብር ምንድር ነው አንለይለትምን፤ አምልኮ ስግደት ምሥጋና ለርሱ ነው በጣም አንገዛው አንለማመጠውም። አንታጠቅለትም። ታላቅ ጌታ ሰጭ ነሽ ነውና።


አዳኝም ገዳይም እርሱ ነውና። በሰማይና በምድርም ከርሱ በቀር ሌላ የለም። ሁሉም ከርሱ ነው የተገኘው ሁሉም የሆነው በርሱ ነው። አለ ርሱ ምንም የሆነ የለም ምስጋና ይገባዋል ለዘለዓለሙ አሜን።


እግዚአብሔር ዕሩቅ ነው ጥበቡ አይታይምና እግዚአብሔር ቅርብ ነው ቶሎ ይሰማልና። እግዚአብሔር መኰንን ነው ቶሎ ይፈርዳልና። እግዚአብሔር እንግዳ ነው ቶሎ ወሬ ይሰማልና። እግዚአብሔር ትሑት ነው፤ ሰውን አይንቅምና። እግዚአብሔር መሐሪ ነው ቶሎ ይቅር ይላልና ርኅሩኅ ነው።


እግዚአብሔር ሐኪም ነው። ሁሉን በጥበብ አድርጓልና እግዚአሔር ምስጉን ነው ፀሐይን ጨረቃን ፈጥሮአልና። እግዚአብሔር ክቡር ነው ሰማይና ምድር የርሱ ናቸውና።


እግዚአብሔር ባለ ጸጋ ነው ለሁሉ ይመግባልና። እግዚአብሔር ረቂቅ ነው አይጨበጥምና። እግዚአብሔር ግዙፍ ነው በዓለሙ ሁሉ ሞልቷልና። እግዚአብሔር ብሩህ ነው ጨለማ የለበትምና። እግዚአብሔር ኃያል ነው የሚቋቋመው የለምና።


እግዚአብሔር እሳት ነው እጅግ ያስፈራልና። እግዚአብሔር መካር ነው መጻሕፍትን ሰጥቶናልና። እግዚአብሔር አባት ነው አሳድጐናልና። እግዚአብሔር ወንድም ነው ሰው ሆኖዋልና። እግዚአብሔር ወዳጅ ነው የሆዱን ነግሮናልና።


እግዚአብሔር አገር ነው እንኖርበታለንና። እግዚአብሔር ማርና ሱካር ነው ይጣፍጣልና። እግዚአብሔር ገናን ነው የሚያህለው የለምና። እግዚአብሔር ትልቅ ነው ስፍራ አይበቃውምና። እግዚአብሔር ጥልቅ ነው በዋና አይገኝምና። እግዚአብሔር ፋሲካ ነው ለሁሉ ታርዷልና። እግዚአብሔር ዓመት በዓል ነው። ለሁሉ ደስታ ነውና። እግዚአብሔር ጨው ነው ሁሉን ያጣፍጣልና። እግዚአብሔር ክረምት ነው ሁሉን ያበቅላልና። እግዚአብሔር አይጠረጠርም ሁሉን ያውቃልና። እግዚአብሔር አይዘነጋም በሁሉ ድካም የለበትምና። እግዚአብሔር አይሰጋም የሚሽረው የለምና።


እግዚአብሔር የሰው ሎሌ ነው በክረምት ለማብቀል በበጋ ለማብሰል የተዘጋጀ ነውና። እግዚአብሔር እንግዳ አይደለም ከጥንት የነበረ ነውና። ምስጋና ይሁን ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ጥንት ለነበረ አሁን ሳለ ኋላም ለሚኖር አሜን።




═──━━━━⊱✿⊰━━━━──═

ሃሳብ @hadis_comment_bot

▬▬▬▬▬❀✿❀▬▬▬▬▬

መጽሀፈ ጨዋታ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ

አለቃ ዘነብ ኢትዮጵያዊ

◦◦◦▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬◦◦◦
ይቀላቀሉ @yemaryammekenet

━━━━━━━━━━━━━━━━
 ̄ ̄ ̄ ̄ ̄  ̄ ̄ ̄ ̄ ̄
 ̄─━━━━⊱✿⊰━━━━─ ̄