Get Mystery Box with random crypto!

❍●◦─━•°°°•━─◦●❍ ወገኑን በጣም ያኰራል፥ በሰውነቱ  ዐማኑኤል፥ የጌታ ልጅ ነው ባባቱ፥ ለ | የማርያም መቀነት

❍●◦─━•°°°•━─◦●❍

ወገኑን በጣም ያኰራል፥
በሰውነቱ  ዐማኑኤል፥
የጌታ ልጅ ነው ባባቱ፥
ለማኝ ናት እንጂ  እናቱ ።

ወልደ እግዚኣብሔርን አግኝቼው፥
ርጥብ ሥጋውን በልቼው፥
ደሙን ጠጥቼ ሥጋውን፥
ምነዋ እሞት ቢሆን ።

ወልደ  አምላክ እንኳ መሞቱ፥
ለኛ  ብሎ ነው ለፍጥረቱ፥
በመለኮቱ ይነሣል፥
አብነቱን ያውቃል ።

ውዳሴ  ማርያም ሲታደል፥
ብርሃንን ለኔ በል።

ውዳሴ ማርያም  ስንማር፥
አግኝተን ነበር ደግ ምስጢር፥
ተገደፈ አሉኝ ተሳሳተ፥
ኦ ' አዳም መሬት አንተ ።

ወድቃ ተሰብራ ያለውሉ፥
ኂሩት ደቃለች አሉ ።

ውሃ ሲሞላ አረምሞ፥
መጠበቅ ያሻል ከዳር ቆሞ፥
የሚያውቀው የለም ምን ቢሆን፥
የሚጠራበትን ቀን።


═─────────────═
ሃሳብ @hadis_comment_bot
@hadis_comment_bot
@hadis_comment_bot
▬▬▬▬◉◉◉◦◦◦◉◉◉▬▬▬▬

ይቀላቀሉ @yemaryammekenet
@yemaryammekenet
@yemaryammekenet
━━━━━━━━━━━━━━━━━
 ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄