Get Mystery Box with random crypto!

👉የ ብዕር ጠብታ

የቴሌግራም ቻናል አርማ yebeir_tebta — 👉የ ብዕር ጠብታ
የቴሌግራም ቻናል አርማ yebeir_tebta — 👉የ ብዕር ጠብታ
የሰርጥ አድራሻ: @yebeir_tebta
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 563
የሰርጥ መግለጫ

እንኳን ወደ ቻናላችን በሰላም መጣችሁ
በቻናላችን ማንኛውም ከመጽሐፍት የተገኙና እናንተን ይጠቅማሉ ፣ ያዝናናሉ ፣ ያነቃሉ ያልናቸውን ነገሮች ከማካፈል አንቦዝንም ለአስታየት @Tom90my_Bot

@yebeir_tebta👈
Join US👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat/AAAAAE1HDLi1GR4snH-4gA
Live ማለት በጥብቅ የተከለከለ ነው

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-01 12:43:24 ፉክክሩን አቁም!

የፉክክር ቤት ሳይዘጋ ያድራል፤ ራስህን ከሰዎች ጋር የምታወዳድር ከሆነ መቼም አትደሰትም፤ ደስ ቢልህ እንኳን ደስታህ ብዙ አይቆይም! ከራሱ ጋር የሚወዳደር ሰውን ግን ማንም አያቆመውም።

በራስህ ለውጥ ደስ ይበልህ፤ ዛፎች ሁሉ እኩል አያድጉም ግን ማደግ እስከሚችሉት ከፍ ይላሉ። ወዳጄ አይንህን ከሌሎች ላይ ነቅለህ ወደ ራስህ ባየህ ቁጥር እድገትህ ፈጣን ነው፤ ከሁሉ በላይ ደግሞ የአይምሮ ሰላም አለህ!

ሰላማዊ ቀን ተመኘንላችሁ
#የብዕር_ጠብታ
99 views09:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 00:48:46 ሁሌም እድል አለ !

በህይወትህ ያሰብከው የተመኘኸው እና የለፋህበት ነገር አልሳካ ቢልህ እና ነገሮች የተበላሹ ቢመስልህ ተስፋ ቆርጠህ ህይወቴ ተበላሸ ብለህ እንዳትቀመጥ ሁሌም ቢሆን የተሻለ መንገድ አለ! ሁሌም ቢሆን ፈጣሪ እድል ይሰጠናል ለኛ ያመቻቸው ትልቅ ነገር አለ አዘጋጅቶልናል!

የተባረከ ቀን ተመኘን
#የብዕር_ጠብታ
135 views21:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 18:55:36 መጨከን አለብህ!

ሁሌም ለውጥ የምትፈልግ ከሆነ ከማትፈልገው ነገር ጋር መጋፈጥ ተለማመድ፤ ምቾት ውስጥ ሆነህ ለውጥ የለም! አንተን የሚያሳድጉህ ነገሮች ያሉት ከምቾትህ ጀርባ ነው።

በጠዋት መነሳት፣ ከሚጠበቅብህ በላይ መስራት፣ ፊልሙን ዘግተህ ማንበብ ራስን ማስጨነቅ ነው፤ ግን ለውጥ እና እድገት ያለው እየመረረህ እንኳን ጨክነህ በምታደርጋቸው ነገሮች ውስጥ ነው! እድገት የምትፈልግ ከሆነ መጨከን አለብህ ወዳጄ!

አስገራሚ ምሽት ተመኘንላችሁ
#የብዕር_ጠብታ
149 views15:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 18:55:36 ወስን!

ህይወትህን እስከመጨረሻው የሚቀይረው አንድ ውሳኔ ሊሆን ይችላል! በቃ ህይወቴን የምቀይረው እኔ ነኝ! ማንንም አልጠብቅም ከፈጣሪ ጋር ለራሴ ያለሁት እኔ ነኝ። ያኔ አይምሮህ ራሱ የምትፈልገውን እንታሳካ ክፍት ይሆናል! ወዳጄ ወስንና ወደ ተግባር ግባ!

#የብዕር _ጠብታ
135 views15:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 23:37:40 የደስተኝነት ሚስጥር

ደስተኛ የመሆን ትልቁ ሚስጥር ገና የሚመጣውን ማሰብ ብቻ አይደለም፤ ወደ ህይወታችን የመጣውንም ማሰብ ነው። ወደ ህይወታችን ከመጣው ምርጥ ስጦታ አንዱ የዛሬው ቀን ነው።

የዛሬዋን ቀን ከዚህ በፊት ቀድሞ ያየው አለ? የለም! ስለዚህ አዲስ ስጦታ ነው። ለሀብታሙም ለደሀውም፣ ለትልቁም ለትንሹም፣ ለሴቱም ለወንዱም እኩል ከፈጣሪ የተሰጠ ልዩ ስጦታ! ይሄን ያደረገ አምላክህን ስታመሰግን እውነተኛ ደስታ ልብህን ይሞላዋል።

#የብዕር_ጠብታ
257 views20:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 23:14:37 ሰበብ መደርደሩን አቁም!

አሁን ለገጠመህ ችግር ሰዎችን መውቅስ አቁም! በሁኔታዎች ማማረር አቁም! በኑሮህ፣ በገቢህ፣ በትዳርህ ወይ በፍቅር ግንኙነትህ ደስተኛ ካልሆንክ በራስህ ምክንያት ነው፤ እኔ ራሴ ከፈጣሪ ጋር ሁሉንም አስተካክለዋለው በል!

አንተ ለራስህ ካልሆንክ ሌላ ማን እንዲሆንልህ ትፈልጋለህ? ይህቺ አለም ወደ ውስጡ ለሚያይና ራሱን ለሚቀይር ታሽቃብጣለች፤ በሰዎችና በሁኔታዎች ለሚያሳብብ ደግሞ ፊቷን ታዞራለች። ችግሩም መፍትሄውም እኔ ነኝ በል ወዳጄ!

የለውጥ ቀን ተመኘንላችሁ
#የብዕር_ጠብታ
258 views20:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 23:14:37 ትሰጣለህ፡ትቀበላለህ ህይወት አዙሪት ናት ትላንት በነበርከት ላይ አትቆምም አብረሃት ትዞራለህ ለምድር ዘርህን ትሰጣለህ ተቀብለህ ደሞ ቆርጠኽ ትበላለህ!!!

ሳትሰጥ ለመቀበል መሞከር ልፋት ነው።አለመንቀሳቀስም አይቻልም!
#የብዕር_ጠብታ
229 views20:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 18:39:07 አሁንም ታገስ!

የምትችለውን እያደረክ ይሆናል ግን የፈለከውን ውጤት ማየት አልቻልክም፤ "ለምን እባክናለው? እንደውም አቆመዋለው!" ልትልም ትችላለህ፤ እውነት አለህ ወዳጄ።

ግን አቁመህስ ምን ትፈጥራለህ? ማቆም መፍትሄ ሆኖ አያውቅም፤ ስለዚህ ታገስ! ካልታገስክ ተዓምር አታይም። ደግሞ አትጓጓ! ከጓጓህ ከመንገድ ትቀራለህ።
#የብዕር_ጠብታ
278 views15:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 23:50:30 ሰው ሰውን ሲያጣ ፣ ንብረቱን ሲያጣ ፣ የሚያስፈልገውን ሲያጣ መኖር ማይችል ይመስለዋል! ግን ሰው መኖሩን የሚያቆመው ሕልሙንና ተስፋውን ያጣ ቀን እና ለሽንፈት እጅ የሰጠ ዕለት ነው!!! ያኔ እድሜው የልጅ ቢሆን እንኳ ኑሮው የድካምና ያዛውንት ይሆንበታል!!!

ወዳጄ ሕይወትህ ሳይቋጭ ፣ መዝገብህ ሳይከደን ስርኽን መሬት ለመሬት እየሰደድክ ባቅምህ እንደ ዛፉ ተወዛወዝ!!! ዛፍ ተገንድሶ እስካልወደቀ ድረስ እንቅስቃሴውን አያቆምም!!!
#የብዕር_ጠብታ
221 views20:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-20 20:58:25 ሁሉም ለበጎ ነው!

ፈጣሪ በነገሮች በሁኔታዎች ነው የሚናገርህ፤ በጆሮህ መጥቶ እንዲህ አድርግ አይልህም፤ በህይወት እየሆነ ያለው ነገር በሙሉ ለምክንያት ነው።

ንቁ ሆነህ በህይወትህ የሚሆነውን ሁሉ ማስተዋል አለብህ! ደግሞ አትርሳ ተማሪ ካለ አስተማሪ የትም ቦታ አለ።

#የብዕር_ጠብታ
183 views17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ