Get Mystery Box with random crypto!

ለሥራ ወደ ውጭ አገሮች ለሚሄዱ ከ500 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የመድን ዋስትና መስጠት ተጀመረ | TIKVAH-MAGAZINE

ለሥራ ወደ ውጭ አገሮች ለሚሄዱ ከ500 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የመድን ዋስትና መስጠት ተጀመረ

ወደ ውጭ አገሮች በሥራ ስምሪት ለሚጓዙ ከ500 ሺሕ በላይ ለሚደርሱ ኢትዮጵያውያን የሕይወት የመድን ሽፋን አገልግሎት ለመስጠት፣ ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር ለሁለት ዓመታት ውል የተፈራረመው ኒያላ ኢንሹራንስ አገልግሎቱን በይፋ መጀመሩን ገለፀ።

በዚህም ኒያላ ኢንሹራንስ ኩባንያ ወደ ተለያዩ አገሮች ተጉዘው የሥራ ቅጥር ውል ለሚፈጽሙ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ለሚደርስባቸው የሞት፣ የአካል ጉዳት፣ የአዕምሮ መታወክና ሌሎች ተጓዳኝ ጉዳቶችን የሚሸፍን መሆኑን ሪፖርተር አስነብቧል።

ለእነዚህ የመድን ሽፋኖችም ተጠቃሚዎች በዓመት እንዲከፍሉ የሚጠበቅባቸው 500 ብር ብቻ መሆኑ ሲጠቆም ይህ የመድን ሽፋን በአንድ ክፍያ ሰው እስከ 1.35 ሚሊዮን ብር ድረስ የሕይወት መድን ሽፋን አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑንም ተነግሯል።

@TikvahethMagazine