Get Mystery Box with random crypto!

#CholeraUpdate በኢትዮጵያ ባለፈው ወር ከአፍሪካ ሀገራት ከፍተኛ የኮሌራ ታማሚዎች ቁጥር | TIKVAH-MAGAZINE

#CholeraUpdate

በኢትዮጵያ ባለፈው ወር ከአፍሪካ ሀገራት ከፍተኛ የኮሌራ ታማሚዎች ቁጥር እንደተመዘገበ ተነገረ

በአፍሪካ ባለፈው መጋቢት ወር በኮሌራ በሽታ ከተያዙ 14,441 አዲስ የኮሌራ ታማሚዎች መሃከል ከአህጉሪቱ ከፍተኛ ታማሚዎች የተመዘገቡባት ኢትዮጵያ መሆኗን የአለም ጤና ድርጅት ሪፖርት አመልክቷል።

በተጠቀሰው ወር በኢትዮጵያ 4009 ሰዎች በኮሌራ መያዛቸው ተነግሯል። በኮሌራ ከተያዙት ሰዎች ውስጥም 24 ሰዎች መሞታቸው ተጠቁሟል። በኢትዮጵያ ባለፉት 3 ወራት 9,429 ሰዎች በኮሌራ ተይዘው 111 ሰዎች መሞታቸውንም ሪፖርቱ አመልክቷል።

በአፍሪካ ከጃንዋሪ 1 ቀን 2023 እስከ ማርች 31 ቀን 2024 በጠቅላላው በ18 ሀገራት 271,119 ሰዎች በኮሌራ በሽታ ሲያዙ በተጠቀሰው ጊዜ በኢትዮጵያ 39,892 ሰዎች በበሽታው ተይዘው 524 ሰዎች መሞታቸውም ነው የተገለፀው።

@TikvahethMagazine