Get Mystery Box with random crypto!

ከታላቁ ህዳሴ ግድብ በቀን እስከ 250 ኪሎ ግራም የሚደርስ ዓሳ እየተገኘ ነው ተባለ በቤኒሻንጉል | TIKVAH-MAGAZINE

ከታላቁ ህዳሴ ግድብ በቀን እስከ 250 ኪሎ ግራም የሚደርስ ዓሳ እየተገኘ ነው ተባለ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከዚህ ቀደም ታጥቀው ይንቀሳቀሱ የነበሩና ሌሎች ወጣቶች በ2 ማኅበር ተደራጅተው በጀመሩት የዓሳ ማስገር ስራ ከህዳሴ ግድብ በቀን እስከ 250 ኪሎ ግራም የሚደርስ ዓሳ እየተገኘ መሆኑ ተገለፀ።

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሐይቅ ግድቡ ውሀ መያዝ ከጀመረ ወዲህ በተለይም ለዓሳ ምርት ምቹ መሆኑ ሲገር በ8 ወራት ውስጥ 1729 ቶን ዓሳ ምርት ከህዳሴ ግድብ መገኘቱን ዶይቼ ቨለ በዘገባው አመልክቷል።

ወጣቶቹ የተደራጁበት ማህበርም 56 የሚደርሱ ወጣቶችን ያቀፈ ሲሆን በግደቡ ዳርቻ በሚሰሩት የዓሳ ማስገር ስራ በቀን ከ2 እስከ 3 ኩንታል ዓሳ እንደሚኝና በአካባቢው የዓሳ ማስገር ስራውን በማህበሰረብ አቀም ለማድረግና ለማሻሻል ዘመናዊ ጅልባዎች ያስፈልጋሉ ተብሏል።

@TikvahethMagazine