Get Mystery Box with random crypto!

'የአፍሪካ ተምች' በጅማ ዞን መከሰቱ ተገልጿል። 'የአፍሪካ ተምች' በጅማ ዞን በሸቤ ሰምቦ ወ | TIKVAH-MAGAZINE

'የአፍሪካ ተምች' በጅማ ዞን መከሰቱ ተገልጿል።

'የአፍሪካ ተምች' በጅማ ዞን በሸቤ ሰምቦ ወረዳ መከሰቱን የጅማ እፅዋት ክሊኒክ ማዕከል አስታውቋል፡፡ የማዕከሉ ሀላፊ አቶ ቦና ሂርጳ ፥ ተምቹ በወረዳው በሚገኙ አራት ቀበሌዎች መከሰቱን መግለጻቸውን ፋብኮ ዘግቧል።

በዚህም በ400 ሄክታር መሬት ላይ በሚገኝ የበቆሎ፣ጤፍ፣ማሽላ፣ ዳጉሳ እና የግጦሽ ሳር ላይ ጉዳት አድርሷል ነው ያሉት፡፡

አሁን ላይ ተባዮችና የዕፅዋት በሽታዎች እየተስፋፉ በመሆኑ አርሶ አደሩ ማሳውን በመፈተሽ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባው አሳስበዋል ሲል ዘገባው አመላክቷል፡፡

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot