ኢትዮ ቴሌኮም የቴሌኮም ማጭበርበር ድርጊቶችን #በ9090 አሳውቁኝ ብሏል።
ከቴሌኮም አገልግሎት ማጭበርበር ጋር በተያያዘ ጥቆማ ለመስጠት ኢትዮ ቴሌኮም የአጭር የጽሁፍ መልዕክት ቁጥር ይፋ አድርጓል።
ደንበኞች ከታች ያሉትን ቁጥሮች በማስቀደም የደረስዎትን መልእክት ወደ
9090 #በነፃ በመላክ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድ ትብብር ያደርጉ ዘንድም ጠይቋል።
በዚህም፦
- ከውጭ ሀገር የሚደወሉ ጥሪዎች በሀገር ውስጥ ቁጥር ሲቀበሉ 1ን በማስቀደም፤
- የማያውቁት የውጭ ሀገር ጥሪ ምልክት (Missed Calls) ሲያገኙ 2ን በማስቀደም፤
- የማያውቁት ሰው ገንዘብ፣ ካርድ ወይም የሞባይል ጥቅል እንዲልኩለት ካግባባዎት 3ን በማስቀደም፤
- የማጭበርበር መልእክት ከደረስዎ 4ን በማስቀደም፤
- የማያውቁት ሰው የቴሌብር ቁጥር እና የይለፍ ቃሎን ከጠየቅዎት 5ን በማስቀደም፤
- ለሌሎች የማጭበርበር ጥቆማዎች 6ን በማስቀደም በአጭር የጽሁፍ መልዕክት ጥቆማዎችን አድርሱኝ ሲል ጠይቋል።
@tikvahethmagazine @tikvahmagbot