የኢትዮጵያ ቡና በአልጄሪያ ገበያ ስለሚቀርብበት ሁኔታ ምክክር ተካሄደ በአልጄሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው የኢትዮጵያ ቡና በአልጄሪያ ገበያ ስለሚቀርብበት ሁኔታ በሀገሪቱ እውቅ ከሆነው የቡና አቅራቢ ፌኔክ ኮፊ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል። አምባሳደር ነቢያት በውይያታቸው የኢትዮጵያ ባለ ልዩ ጣዕም ቡና ቀጥታ ወደ አልጄሪያ ገበያ ስለሚቀርብበት ሁኔታ መምከራቸውን አስታውቀዋል። ኢትዮጵያ ባለፉት 10 ወራት በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ውጭ ከተላከ ቡና አንድ ቢሊዮን ዶላር ገቢ እንዳገኘች መገለጹ ይታወሳል። (ENA) @tikvahethmagazine @tikvahmagbot 20.5K viewsedited 13:23