የቤቶች መረጃ አስተዳደር ስርዓት በኦሮሚያ ዘጠኝ ከተሞች ሊተገበር ነው ተባለ። ከቤቶች መረጃ አያያዝና አስተዳደር ጋር በተያያዘ የሚስተዋለውን ሰፊ ክፍተት ለመሙላት ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው የታመነበት የቤቶች መረጃ አስተዳደር ሶፍትዌር ትግበራ በኦሮሚያ ዘጠኝ ከተሞች ዛሬ በይፋ ተጀምሯል ተብሏል። በክልሉ ከ122ሺህ በላይ የሚገኙ የቀበሌ ቤቶችን ለመመዝገብ፣ ጥገናና እድሳት ለማድረግ፣የኪራይ ውልን ለማከናወን፣ በተከራዮች የሚነሱ የተለያዩ ጉዳዮችንና ቅሬታዎችን ለመከታተልና መፍትሔ በወቅቱ ለመስጠት የመረጃ ስርዓቱ እጅግ ጠቃሚ ነው ተብሏል። @tikvahethmagazine @tikvahmagbot 18.4K viewsedited 13:22