Get Mystery Box with random crypto!

University of Ethiopia

የቴሌግራም ቻናል አርማ temihert — University of Ethiopia U
የቴሌግራም ቻናል አርማ temihert — University of Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @temihert
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.27K
የሰርጥ መግለጫ

MOE / STAR ACADEMY
✅ይህ በአይነቱ ልዩ የሆነ ቻናል የተዘጋጀው በ ማህበረሰቡ ጥያቄ መሰረት ሲሆን በውስጡም ለተለያዩ የክፍል ደረጃዎች የሚሆኑ ኖቶች፣pdf፣ሞዴል ፈተናዎች፣ማትሪክና የተለያዩ መረጃዎችን ያገኛሉ።
📚Freshma tutorial በዮኒቨርስቲ ተማሪዎች የተቋቋ
ad service: 📚 MOE በተለየ መልኩ
✅መረጃዎች በፍጥነት እንዲደርሶት ቻናላችንን #UNMUTE ✔ ያድርጉ ⏳

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-03-22 19:17:08 #EthiopianHumanRightsCouncil

የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት እንደገና እንዲፈተሽላቸው ጥያቄ ላቀረቡ ተማሪዎች መንግስት አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጥ ኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) ጠይቋል።

"የፈተናው ውጤት ከተገለጸበት ጊዜ ጀምሮ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች ውጤታቸው እንደገና እንዲፈተሽላቸው ለሚመለከተው አካል ጥያቄ እያቀረቡ እንደሚገኙ" ጉባኤው ገልጿል።

"በመሆኑም የሚመለከተው ክፍል የተማሪዎቹን ጥያቄ በመመርመር አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጣቸው" ጉባኤው አሳስቧል።

በፈተናው ውጤት ዙሪያ "ከተለያዩ አካላት የሚሰነዘሩ ሃሳቦች ማኅበረሰቡን ግራ እያጋቡ እና የተማሪዎቹንም ስነ ልቦና እየጎዱ በመሆናቸው የሚመለከተው አካል ተገቢውን ማብራሪያ እንዲሰጥ እና የእርምት እርምጃ እንዲወስድ" ኢሰመጉ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጥሪውን አቅርቧል።

@Temihert
1.5K viewsB£<><>, 16:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-21 20:28:09 | የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ
ማተብ ታፈረ (ዶ/ር)

"ተሰርቆ የወጣው ፈተና በአግባቡ ሳይታይ ቀርቶ በአማራ ክልል ተማሪዎች ላይ ተጽዕኖ ፈጥሮ ከሆነ፣ ተማሪዎች በጦርነት አውድ ውስጥ መቆየታቸው በልዩ ሁኔታ ጎድቷቸው ከሆነ፣ በእርማት ሂደት የተፈጠሩ ስህተቶች ካሉ እንዲታዩ ጥያቄ እያቀረብን ነው።"

"የተማሪዎች ውጤት መቀነስ እኛን ስለሚመለከት ችግሩ እስኪፈታ ቢሮው የማጣራት ሥራ እንዲከናወን እስከመጨረሻው ይቀጥላል።"

@Temihert
1.3K viewsB£<><>, 17:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-21 19:58:30 የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተማሪዎችን ፈተና ሂደት የሚያጣራ ቡድን ወደ ስፍራው መላኩን አስታወቀ
የ2013 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የክልሉ ተማሪዎች የውጤት ችግር መግጠሙን ተከትሉ ከፍተኛ ቅሬታ ፈጥሯል፡፡ የተማሪዎች ውጤት ያሳሰበው የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮም ችግሩን ለመፍታት በርካታ ተግባራትን ሲፈጽም ቆይቷል፡፡

በአሁን ሰዓትም ከክልሉ ትምህርት ቢሮ አመራሮቸና ባለሙያዎች፣ከአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤ፣ከዩኒቨርሲቲ ምሁራን፣ከትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራንና መምህራን የተውጣጣ ቡድን ወደ ፈተናወች ኤጀንሲ መላኩ ታውቋል፡፡

@Temihert
1.3K viewsB£<><>, 16:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-21 12:11:00 " ከ13, 862 ተፈታኞች 3,006 ተማሪዎች ብቻ ናቸው ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የመግቢያ ዉጤት ያስመዘገቡት " - የአዊ ብሔ/አሰ ትምህርት መምሪያ

በአማራ ክልል፤ የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ከ13 ሺ 862 ተፈታኞች 3 ሺህ 6 ተማሪዎች ብቻ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የመግቢያ ዉጤት ማስመዝገባቸዉን አሰታወቀ።

የመምሪያዉ ኃላፊ አቶ አለሙ ክህነት ፤ በ2013ዓ.ም በብሔረሰብ አስተዳደሩ በ29 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ 13 ሺህ 862 ተማሪዎች ሀገርአቀፋ ፈተና መፈተናቸውን ገልጸዋል።

ከነዚህም ዉስጥ በብሄረሰቡ ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ 3 ሺህ 6 ተማሪዎች ብቻ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የመግቢያ ዉጤት ማምጣታቸውን ነዉ ሀላፊዉ የተናገሩት።

አጠቃላይ የማለፋ ምጣኔም 21.7% ብቻ መሆኑ ተገልጿል።

ከተፈተኑት የተፈጥሮ ሳይንስ 5 ሺህ 745 ተማሪዋች መካከል 1 ሺህ 943 የመግቢያ ዉጤት አምጥተዋል። በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ ከተፈተኑት 8 ሺህ 117 ተማሪዎች ዉስጥ 1 ሺህ 63 ወደ የመግቢያ ዉጤት ያመጡ መሆናቸዉን ተገልጿል።

የእርማት ጥራት ችግር ማሳያ 140 ያመጣ ተማሪ እንደገና ሲፈተሸ 601 ፣ የሲቪክስ ት/ት ፈተና ችግር በሌለበት አካባቢ መሰረዝ እና የፈተና አስተዳደር ስርዓቱ በአግባቡ የተመሩ ባለመሆናቸዉ ለተመዘገበዉ ዝቅተኛ ዉጤት ተጠቃሽ ሞክንያቶች መሆኑን ትምህርት መምሪያው ገልጿል።

የፈተና ስርዓቱ ስለመታወኩ በተለያዩ ቴክኖሎጂዎች ቼክ ተደርጎ እንደገና መፈተሽ እንዳለበት ከሚመለከተው ጋር እየሰራ መሆኑን መምሪያው አሳውቋል።

እስከአሁንም መምሪያዉ ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ጋር የፈተና ሂደቱ እንደገና እንዲታይ ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልጾ ተማሪዎች እና የተማሪ ቤተሰቦች በትግስት እንዲጠብቁ አሳስቧል።

@Temihert
1.2K viewsB£<><>, 09:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-19 20:44:44 የተማሪዎችን ያልተጠበቀ የውጤት መቀነስ ምክንያት ለማወቅ ሁሉን አቀፍ ጥረት እያደረገ መኾኑን የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባዔ ገለጸ።

መማክርት ጉባዔው የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ይፋ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ ያሉ ጉዳዮችን በአንክሮ እየተከታተለ እንደኾነ ገልጿል።

የአማራ ክልል 12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ውጤት ከዚህ ቀደም ይመዘገብ ከነበረው ያነሰ መኾኑን መረጃ ማግኘቱንም አስታውቋል። ይህንን መሠረት በማድረግም የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባዔ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ዝቅተኛ ውጤት እንዲመዘገብ ያጋጠሙ ምክንያቶችን ለማጣራት ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ጋር በቅርበት እየሠራ እንደሆነ የጽሕፈት ቤቱ ኀላፊ ዶክተር ዳዊት መኮንን ገልጸዋል።

መረጃና ማስረጃን ምክንያት በማድረግ የውጤት መቀነስ ሥረ መሠረታዊ ምክንያቱን በትክክል ለማወቅ ኹሉንአቀፍ ጥረት እያደረገ እንደኾነም ጠቅሰዋል። ባልተለመደ መልኩ የአማራ ክልል ተማሪዎች ውጤት መቀነስ ጉባዔውን እንዳሳሰበው የገለጹት ዶክተር ዳዊት የችግሩን ምክንያት ከማወቅ ጀምሮ መፍትሔ እንዲሰጠው የሚጠበቅበትን ሚና ይጫወታል ነው ያሉት። ለዚህም ከፈተና እና ምዘና ባለሙያዎች፣ ከሶፍትዌር ባለሙያዎች እና ከመምህራን ጋር እየመከረ መኾኑን አመላክተዋል።

   ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@Temihert
@Temihert
1.1K viewsB£<><>, 17:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-19 20:09:54 #ምደባ

በ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስደው ወደዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ተማሪዎች ውጤት ተፈትሾ መተማመኛ ላይ እስኪደረስ የዩኒቨርስቲ መግቢያ ጊዜው እንዲራዘም ተጠየቀ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ለትምህርት ሚኒስቴር በፃፈው ደብዳቤ ጠይቋል።

የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት ከተገለፀበት ጊዜ ጀምሮ እጅግ በጣም ሰፊ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎቻችን ውጤታቸው እንደገና እንዲፈተሸላቸው እያመለከቱ መሆኑን የገለፀው የክልሉ ትምህርት ቢሮ በተጨማሪ በትምህርት አመራሩና በትምህርት ማህበረሰቡ ዘንድም በርካታ ጥያቄዎች እየተነሱ መሆኑን ቢሮው አትቷል። የተማሪዎች ውጤት በአግባቡ ተፈትሾላቸው ተገቢው መተማመን እስኪፈጠር ድረስ የተማሪዎች መግቢያ ቀን ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ቢሮው በደብዳቤ ትምህርት ሚኒስትርን ጠይቋል፡፡

https://t.me/Temihert
1.1K viewsB£<><>, 17:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-19 12:42:49 የቀጠለው ቅሬታ ...

የምስረቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ ከ12ኛ ክፍል ፈተና ጋር በተያያዘ የተነሳው ቅሬታ ነፃ እና ገለልተኛ በሆኑ አካላት ተጣርቶ ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጠው ጠየቀ።

መምሪያው የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ዉጤት በማስመልከት ለትምህርት ሚኒስቴር ቅሬታ ማቅረቡን እና ተገቢ ምላሽ ሊሰጠዉ እንደሚገባም ዛሬ ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

በዞኑ በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በ40 ት/ቤቶች በሶሻል ሳይንስ 15,222 ተማሪዎች ተፈትነው 1765 ተማሪዎች 11.6% ማለፋቸው በናቹራል/ተፈጥሮ/ሳይንስ ደግሞ 7,075 ተፈትነው 1,619 (22.8%) ተማሪዎች ብቻ ማለፋቸውን ተመላክቷል።

የዞኑ ትምህርት መምሪያ ለኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር የፈተና አስተራረም እና የውጤት አሞላል ችግር ያለበት መሆኑን በተደጋጋሚ ብንገልጽም የተሰጠው ምላሽ አጥጋቢ እንዳልሆነ ገልጿል።

የምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ ባወጣው መግለጫ ፥ ለቀረበው ቅሬታ ምክንያት ብሎ ከዘረዘራቸው መካከል አንደኛው የአብርሃ አፅብሃ 2ኛ ድረጃ ት/ቤት አንድ ተማሪ (አማኑኤል ፀሐይ) በመጀመሪያ የተለቀቀው ውጤት 162 ሆኖ በኦንላይ ቅሬታ ቢያቀብርም ሳይፈታለት ቀርቶ በአካል በሀገር አቀፍ ፈተና አገልግሎት ቀርቦ ሲያስፈትሽ 647 ሆኖ ተገኝቷል ብሏል።

ሌላው ተማሪዎች ፈተና ሲወስዱ በክልሉ ጦርነት የነበረበት ወቅት በመሆኑና ወላጆችም ግንባር የዘመቱ በመሆናቸው ተማሪዎች በስነልቦና ጫና ውስጥ ሆነው ፣ የከባድ መሳሪያ ተኩስ እየሰሙ መፈተናቸውን ይህ እየታወቀ እንደ ሰላማዊ ጊዜ ከሌሎች ክልሎች እኩል የመግቢያ ውጤት መወሰኑ ችግር ያለበት እና ኢፍትሃዊ እንደሆነ ገልጿል።

ያንብቡ : telegra.ph/East-Gojjam-03-19

@Temihert
@Temihert
▬▬▬▬▬▬▬▬
1.0K viewsB£<><>, 09:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-18 14:34:56
በዩንቨርስቲ መግቢያ ነጥብ ላይ ምንም አይነት ማሻሻያ እንደማይደረግ ተገለፀ

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ ሳሙኤል ክፍሌ ( ዶ/ር) በሰጡት ማብራሪያ የጸጥታ ችግር አጋጥሞ በነበረባቸው አካባቢዎች የተገኘው ውጤት ከሌላው ጊዜ የተለየ አለመሆኑን ተናግረዋል።

ዘንድሮ በ43ቱ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከ187 ሺ በላይ ተማሪዎች ይገባሉ ብለዋል።

የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ተፈራ ፈይሳ በበኩላቸው በእርማት ወቅት የነበሩ ስህተቶችን በወቅቱ አስተካክለናል፡ የሚሻሻል የነገር የለም ብለዋል።

@Temihert
@Temihert
▬▬▬▬▬▬▬
987 viewsB£<><>, edited  11:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-18 12:51:58 ''...በውጤት እና መቁረጫ ነጥቡ ዙሪያ አስፈላጊው ማብራሪያ እንዲሰጥ ለሚኒስቴር መስሪያቤቱ ጥያቄ አቅርቤ ምላሽ እየጠበኩ ነው'' የአበክመ ት/ቢሮ

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2013 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ የፈተና በውጤት እና መቁረጫ ነጥቡ ዙሪያ አስፈላጊው ማብራሪያ እንዲሰጥ ለሚኒስቴር መስሪያቤቱ ጥያቄ አቅርቤ ሚኒስቴር መሰሪያቤቱ በዛሬው ዕለት ተገቢው ማብራሪያ እንዲማሰጥ ገልጾልኛል ሲል አስታውቋል።

ቢሮው ''ብሔራዊ ፈተና በሁለቱም ዙር በሰላማዊ መንገድ እንዲሰጥ የሚፈለግብንን ሁሉ አድርገናል። ከ12ኛ ክፍል ፈተና አኳያ የክልሉ ድርሻም ይሄው ነው።'' ሲል በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ያሰፈረው።

''የአንደኛው ዙር ፈተና እንደተጠናቀቀ በሚቀጥለው ቀን ለሀገር አቀፍ ፈተናዎች ድርጅት በወቅቱ ፈተና ተሰርቋል እየተባለ በማህበራዊ ሚዲያ ሲስራጭ በነበረው የተለያየ መረጃ ምክንያት የፈተና ውጤት ትንተናው በጥንቃቄ እንዲታይ በፅሁፍ ጥያቄ አቅርበናል። ሌሎች ጠቃሚ ሀሳቦችንም በወቅቱ አቅርበናል።'' ሲል ዛሬ ባወጣው መረጃ ገልጿል።

አክሎም በሚኒስቴር መስሪያቤቱ በኩል አስፈላጊው ማብራሪያ ከተሰጠ በኋላ በትምህርት ቢሮው በኩል የሚፈለጉ መረጃዎች ካሉ መረጃዎችን ሳልደብቅ ገልጻለሁ ብሏል።

''የተማሪዎች ውጤት ለዞኖች፣ ወረዳዎች እና ትምህርት ቤቶች በግልፅ የተላለፈ ስለሆነ ለመሸፋፈን የሚፈልግ አካልም የለም መሸፋፈንም አይቻልም።'' ማለቱን ከቢሮው ገጽ ተመልክተናል።

@Temihert
913 viewsB£<><>, 09:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ