Get Mystery Box with random crypto!

#ምደባ በ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስደው ወደዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ተማሪዎች ውጤት ተፈትሾ | University of Ethiopia

#ምደባ

በ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስደው ወደዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ተማሪዎች ውጤት ተፈትሾ መተማመኛ ላይ እስኪደረስ የዩኒቨርስቲ መግቢያ ጊዜው እንዲራዘም ተጠየቀ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ለትምህርት ሚኒስቴር በፃፈው ደብዳቤ ጠይቋል።

የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት ከተገለፀበት ጊዜ ጀምሮ እጅግ በጣም ሰፊ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎቻችን ውጤታቸው እንደገና እንዲፈተሸላቸው እያመለከቱ መሆኑን የገለፀው የክልሉ ትምህርት ቢሮ በተጨማሪ በትምህርት አመራሩና በትምህርት ማህበረሰቡ ዘንድም በርካታ ጥያቄዎች እየተነሱ መሆኑን ቢሮው አትቷል። የተማሪዎች ውጤት በአግባቡ ተፈትሾላቸው ተገቢው መተማመን እስኪፈጠር ድረስ የተማሪዎች መግቢያ ቀን ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ቢሮው በደብዳቤ ትምህርት ሚኒስትርን ጠይቋል፡፡

https://t.me/Temihert