Get Mystery Box with random crypto!

''...በውጤት እና መቁረጫ ነጥቡ ዙሪያ አስፈላጊው ማብራሪያ እንዲሰጥ ለሚኒስቴር መስሪያቤቱ ጥያቄ | University of Ethiopia

''...በውጤት እና መቁረጫ ነጥቡ ዙሪያ አስፈላጊው ማብራሪያ እንዲሰጥ ለሚኒስቴር መስሪያቤቱ ጥያቄ አቅርቤ ምላሽ እየጠበኩ ነው'' የአበክመ ት/ቢሮ

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2013 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ የፈተና በውጤት እና መቁረጫ ነጥቡ ዙሪያ አስፈላጊው ማብራሪያ እንዲሰጥ ለሚኒስቴር መስሪያቤቱ ጥያቄ አቅርቤ ሚኒስቴር መሰሪያቤቱ በዛሬው ዕለት ተገቢው ማብራሪያ እንዲማሰጥ ገልጾልኛል ሲል አስታውቋል።

ቢሮው ''ብሔራዊ ፈተና በሁለቱም ዙር በሰላማዊ መንገድ እንዲሰጥ የሚፈለግብንን ሁሉ አድርገናል። ከ12ኛ ክፍል ፈተና አኳያ የክልሉ ድርሻም ይሄው ነው።'' ሲል በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ያሰፈረው።

''የአንደኛው ዙር ፈተና እንደተጠናቀቀ በሚቀጥለው ቀን ለሀገር አቀፍ ፈተናዎች ድርጅት በወቅቱ ፈተና ተሰርቋል እየተባለ በማህበራዊ ሚዲያ ሲስራጭ በነበረው የተለያየ መረጃ ምክንያት የፈተና ውጤት ትንተናው በጥንቃቄ እንዲታይ በፅሁፍ ጥያቄ አቅርበናል። ሌሎች ጠቃሚ ሀሳቦችንም በወቅቱ አቅርበናል።'' ሲል ዛሬ ባወጣው መረጃ ገልጿል።

አክሎም በሚኒስቴር መስሪያቤቱ በኩል አስፈላጊው ማብራሪያ ከተሰጠ በኋላ በትምህርት ቢሮው በኩል የሚፈለጉ መረጃዎች ካሉ መረጃዎችን ሳልደብቅ ገልጻለሁ ብሏል።

''የተማሪዎች ውጤት ለዞኖች፣ ወረዳዎች እና ትምህርት ቤቶች በግልፅ የተላለፈ ስለሆነ ለመሸፋፈን የሚፈልግ አካልም የለም መሸፋፈንም አይቻልም።'' ማለቱን ከቢሮው ገጽ ተመልክተናል።

@Temihert