Get Mystery Box with random crypto!

University of Ethiopia

የቴሌግራም ቻናል አርማ temihert — University of Ethiopia U
የቴሌግራም ቻናል አርማ temihert — University of Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @temihert
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.27K
የሰርጥ መግለጫ

MOE / STAR ACADEMY
✅ይህ በአይነቱ ልዩ የሆነ ቻናል የተዘጋጀው በ ማህበረሰቡ ጥያቄ መሰረት ሲሆን በውስጡም ለተለያዩ የክፍል ደረጃዎች የሚሆኑ ኖቶች፣pdf፣ሞዴል ፈተናዎች፣ማትሪክና የተለያዩ መረጃዎችን ያገኛሉ።
📚Freshma tutorial በዮኒቨርስቲ ተማሪዎች የተቋቋ
ad service: 📚 MOE በተለየ መልኩ
✅መረጃዎች በፍጥነት እንዲደርሶት ቻናላችንን #UNMUTE ✔ ያድርጉ ⏳

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-07 14:00:33 የ2015 ዓ.ም ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተናን ዲጂታላይዝ ለማድረግ/በኦንላይን ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

የፈተና አሰጣጡን ሙሉ ለሙሉ አውቶሜት ለማድረግ ከቻይና መንግስት ጋር እየተሠራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ ጠቁመዋል።

ለፈተናው የሚቀመጡ ተማሪዎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በርካታ ታብሌት ኮምፒዩተሮች እንደሚያስፈልጉ ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ በኮቪድ-19 ምክንያት አምራች ድርጅቱ ኮምፒዩተሮቹን በተያዘለት ጊዜ ማምረት አለመቻሉን ገልጸዋል።

ኮምፒዩተሮቹ በተያዘላቸው ጊዜ ከደረሱ በቂ ዝግጅት ስለተደረገ የቀጣይ ዓመት ፈተና ኦንላይን እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል።

ታብሌቶቹ በሚጠበቀው ጊዜ ካልደረሱ፥ መንግስት የፈተና ስርቆት የሚቀነስበት የተሻለ አሰራር በመከተል ፈተናው ይሰጣል ብለዋል።

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

https://t.me/Temihert
296 viewsB£<><>, 11:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 13:00:59 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመስጠት ታብሌቶች ካልደረሱ ሌሎች አማራጮች እንደሚጠቀም መንግስት አስታወቀ!!

በሚቀጥለዉ አመት በኦንላይን ይሰጣል ለተባለዉ ሀገር አቀፍ ፈተና ይገባሉ የተባሉ 1 ሚሊዮን ታብሌት ኮምፒውተሮች በወቅቱ ካልደረሱ ሌሎች ምርጫዎችን መንግስት ይከተላል-ጠ/ሚ አብይ

በ2015 ዓ.ም የሚሰጠዉ ሀገር አቀፍ ፈተናን ዲጂታል በሆነ መንገድ በኦንላይን ምዘናዉን ለመስጠት ታቅዶ እንደነበር ይታወሳል። ለዚህም 1ሚሊዮን የሚሆኑ ታብሌት ኮምፒውተሮች ወደ ሀገር ይገባሉ ተብሎም ነበር።

ጠ/ሚ አብይ ይህን በተመለከተ በሰጡት ማብራርያ ያለዉን ስርቆት ለማስቀረት ሲባል ፈተናዉን ዲጂታላያዝ ማድረጉ አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል። ለዚህም 1ሚሊዮን ታብሌት ኮምፕዩተሮቹን ከቻይና መንግስት ጋር በመሆን ለማስገባት እየተሰራ እንደነበር አስታዉሰዋል። ሆኖም በኮቪድ 19 ቫይረስ ምክንያትም አምራች ድርጅቱ ስራዉን በተያዘለት ግዜ ማጠናቀቅ አለመቻሉን አስታዉቀዋል።

በ2015 ለመስጠት የታቀደዉ ፈተናዉ ፤ በቂ ዝግጅት ስለተደረገ ታብሌት ኮምፒውተሮቹ በተያዘላቸዉ ግዜ ከደረሱ ፈተናዉ ይሰጣል ብለዋል። ሆኖም ታብሌቶቹ በግዜዉ ካልደረሱ መንግሰት ሌሎች ምርጫዎችን እንደሚጠቀም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንስተዋል።
https://t.me/Temihert
352 viewsB£<><>, 10:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 10:17:14 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርስቲዎች ዉስጥ እንደሚሰጥ ተገለፀ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በሆሳዕና ፣ በወራቤና በወልቂጤ ከተሞች የሚገኙ ሁለተኛ ደረጃና ሞዴል ትምህርት ቤቶችን ጎብኝተዋል።

በጉብኚታቸዉ ወቅት ከተማሪዎችና ከትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ጋር ባደረጉት ቆይታ የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና በትምህርት ቤቶች ሳይሆን በዩኒቨርስቲ ውስጥ እንደሚሰጥ ገልጸዋል።

እንደሚኒስትሩ ገለጻ የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና በኤሌክትሮኒክስ /online/ መስጠት እስከሚጀመር ድረስ በዩኒቨርስቲዎች መሰጠቱ ይቀጥላል።

የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርስቲ እንዲሰጥ የተወሰነው የፈተና ሰርቆትና ማጭበርበርን ለማስቀረት ታስቦ በመሆኑ ተማሪዎች ትምህርት በስራና በታታሪነት የሚገኝ መሆኑን አውቀው በርትተው መማር ፣ማጥናትና ማወቅ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

የትምህርት ሚኒስቴር የትምህርትን ጥራትን ለማሻሻል በአጠቃላይና ከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፎች ሌሎችንም የተለያዩ እርምጃዎች በመውሰድ ላይ መሆኑንም ፕሮፌሰር ብርሀኑ ጠቁመዋል።

ሚኒስትሩ ሶስቱንም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የጎበኙ ሲሆን የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ ችግኝም ተክለዋል፡፡

○ ትምህርት

ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ

https://t.me/Temihert
502 viewsB£<><>, 07:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 15:22:37 የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና መቼ ይሰጣል ?

የትምህርት ሚኒስቴር የብሄራዊ ፈተና መሰረቅንና ኩረጃን ለመከላከል ፈተናው በኦንላንይ መስጠት እስኪጀመር ድረስ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንዲሰጥ መወሰኑ ይታወቃል።

የፈተናውን አሰጣጥ ሂደትን በተመለከተ ለጊዜው በዝርዝር የሚታወቅ ነገር የለም።

ከዚህ ቀደም የ2014 ብሄራዊ ፈተና ከመስከረም 20 / 2015 ዓ/ም በኃላ እንደሚሰጥ መገለፁ የሚዘነጋ አይደለም ፤ እስካሁን ድረስ የተቀየረም ሆነ በትምህርት ሚኒስቴር የተገለፀ አዲስ ነገር የለም።

ከትላንት ጀምሮ በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች ፈተናው ሃምሌ እና ነሃሴ ላይ ነው የሚሰጠው እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ ምንጩ ያልታወቀና ሀሰተኛ በመሆኑ ተማሪዎች በተረጋጋ መንፈስ በጥናታችሁ ላይ እንድታተኩሩ ወላጆችም ልጆቻችሁ የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ እገዛችሁን እንድታጠናክሩ ይሁን።

እጅግ በርካታ ተማሪዎች እንዲሁም ወላጆች የሚከታተሉት የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ጉዳይን በተመለከተ ከትምህርት ሚኒስቴር ውጭ የሚወጡ መረጃዎችን አምናችሁ አትቀበሉ። አንድን መረጃ ስትሰሙ ከትምህርት ሚኒስቴር መሆኑን አረጋግጡ።


@Temihert
@Temihert
450 viewsB£<><>, 12:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 16:27:13 hi guys endet nachu bet tekimtachu online sra mesrat metfilgu inbox https://t.me/Iwellej
588 viewsB£<><>, edited  13:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 21:21:53 #NEAEA

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2014 ዓ.ም የአጠቃላይ ትምህርት ማጠናቀቅያ ብሄራዊ ፈተና ምዝገባ እያካሄደ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በ2014 ዓ.ም በመደበኛ፣ በማታ እና በግል ብሄራዊ ፈተናውን የምትፈተኑ ተማሪዎች እስከ ሰኔ 27/2014 ዓ.ም ድረስ እንድትመዘገቡ እያሳሰብን እስካሁን ሳትመዘገቡ ለቀራችሁ ተፈታኝ ተማሪዎች በቀረው ጊዜ እንድትመዘገቡ እናሳውቃለን፡፡

በየደረጃው የምትገኙ የትምህርት አመራሮች በተለይም የት/ቤት ር/መምህራን ተፈታኝ ተማሪዎች በተቀመጠው የጊዜ ሠሌዳ እንዲመዘገቡ አስፈላጊውን ጥረት እንድታደርጉ እየጠየቅን፤ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለሚፈጠረው ችግር አገልግሎቱ ኃላፊነቱን የማይወስድ መሆኑን ይገልጻል፡፡

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

ለተጨማሪ የትምህርት መረጃዎች

@Temihert
714 viewsB£<><>, 18:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-27 22:17:59 comment kalchu grup ley adersunhttps://t.me/minsterofedu
942 viewsB£<><>, 19:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-27 22:07:29 Selam.weid ye temihert betsboche alchulgn tetifaftnale awekalew ye chanle abalte ke leb yekirta iaylku.semoun be adis negir



metichalew le chanale adis yehonchu betsib endtihonu.egibazchalew melkam.koyeta
856 viewsB£<><>, 19:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-22 21:09:49 የትምህርት ሚኒስቴር ወደ መንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የሚገቡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምርጫቸውን
እንዲያስተካክሉ የሰጠው የጊዜ ገደብ ዛሬ ተጠናቋል።

የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ አቅም፣ የተማሪዎች አማካይ ውጤት አፈፃጻጸም፣ ወዘተ ከግንዛቤ በማስገባት ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምርጫቸውን እስከ መጋቢት 13/2014 ዓ.ም ድረስ በ Portal.neaea.gov.et ገብተው እንዲያስተካክሉ መጋቢት 08/2014 ዓ.ም ማሳወቁ አይዘነጋም።

ከምደባ በኋላ የሚቀርብ ምንም አይነት የምደባ ለውጥ የማያስተናግድ መሆኑን ሚኒስቴሩ መግለጹ ይታወሳል።

በዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ላይ በርካታ ቅሬታዎች በተለይ ከአማራ ክልል መነሳታቸው ይታወቃል።

ሚኒስቴሩ በቅሬታዎቹ ላይም ሆነ በዩኒቨርሲቲ ምርጫ ማስተካከያው ላይ ያለው አዲስ ነገር የለም።

   ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/Temihert
2.4K viewsB£<><>, edited  18:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-22 20:26:25 የካፋ ዞን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት በድጋሚ ይታይልኝ የሚል ጥያቄ ማስነሳቱን አስታወቀ።

በደቡብ ምዕራብ ክልል ካፋ ዞን ትምህርት መምሪያ ፤ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን ከተቀበሉ 57 ትምህርት ቤቶች ዉስጥ የመቁረጫ ነጥብ ያመጡ ከ21 ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ተማሪዎች ብቻ ናቸው ያለ ሲሆን፤ ይህም ቅሬታ አስነስቷል ብሏል።

የዞኑ ትምህርት መምሪያ ፤ በማህበራዊ ሳይንስ እና በተፈጥሮ ሳይንስ በአጠቃላይ 4 ሺህ 579 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና መውሰዳቸውን ገልጿል።

ዞኑ ካስፈተናቸው ተማሪዎች ከማህበራዊ ሳይንስ እና ከተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ በአጠቃላይ የዩኒቨርስቲ መግቢያ ነጥብ ያመጡ ተማሪዎች 7 መቶ 38 ተማሪዎች ብቻ መሆናቸውን አመልክቷል።

የካፋ ዞን አምና በነበረው አፈጻጸም 621 የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት የተመዘገበበት ዞን መሆኑን እና ከአንድ ትምህርት ቤት በአማካኝ እስከ 88 በመቶ የሚያልፍበት እንደሆነ ገልጿል።

የዘንድሮው አጠቃላይ ዉጤት ታይቶ የማይታወቅ በመሆኑ ዞኑ ያነሳውን የተማሪዎች የፈተና ውጤት በድጋሚ ይታይልኝ ጥያቄ የትምህርት ሚኒስቴር በአጽኖት እንዲመለከተው መጠየቁን አሃዱ ኤፍ ኤም 94.1 ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።

@Temihert
1.8K viewsB£<><>, 17:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ