Get Mystery Box with random crypto!

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodoxmezmur — ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit
የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodoxmezmur — ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit
የሰርጥ አድራሻ: @ortodoxmezmur
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 135.77K
የሰርጥ መግለጫ

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን።
. ዝማሬ ዳዊት
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ።
ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት
@zmaredawit_messengerbot ላይ
ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 33

2023-02-15 13:53:07 ​​በዝማሬ ዳዊት Tube የተላለፉ ትምህርቶች

ኦርቶዶክስ እና የዓለም እምነቶች



እግዚአብሔርን እንዴት መውደድ እንዳለብን



666 እና የውጭ ዘፋኞች



ዘፈን እንዴት ተፈጠረ? ማንስ አስተማረን?



ስለ ቶ መስቀል ክፍል 1



ስለ ቶ መስቀል ክፍል 2



ስለ ቶ መስቀል የመጨረሻው ክፍል



ሴጋ የፈጸመ የተክሊል ጋብቻ ይገባዋልን?



በጸሎት መሀል ወሬ ማውራት



ቅዠት ምንድን ነው?



የምግብ ሰዓት ጸሎት



የምእመናን አለባበስ ምን ይመስላል



ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እና ፕሮቴስታንት ክፍል አንድ



ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እና ፕሮቴስታንት ክፍል ሁለት



ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እና ፕሮቴስታንት የመጨረሻው ክፍል



ስለ ቅዱስ ቁርባን ክፍል አንድ



ንስሐ መግባት ለምን እንፈራለን?



ሕማማት



ስለ ዓቢይ ጾም



ዘጠኙ አጾማት



ለፓስተር ዳዊት የተሰጠ ምላሽ



ለዮናታን አክሊሉ የተሰጠ ምላሽ



ጸሎት ምንድን ነው?



ክርስቲያናዊ የሆነ ጾም እንዴት እንጹም



ከፍቅረኛዬ ጋር ወደፊት ስለምንጋባ አሁን ግንኙነት ብንፈጽምስ?



ግብረ አውናን ምንድነው?



ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል ማድረግ ያለብን ዝግጅት?



ስለ መጽሐፍ ቅዱስ? 81 ወይስ 66





በዝማሬ ዳዊት የተላለፉ አጭር ታሪኮች

የሰይጣን ጥያቄ



ባላገሩ




የልደት (ገና) መዝሙሮች



የጥምቀት መዝሙሮች



አጫብር ወረብ



መጾሙን ይጾማል - የበገና መዝሙር



ማን ይመራመር - የበገና መዝሙር



የሰርግ መዝሙሮች



ዓለምን ዞሬ አየሁት? - የበገና



ስለ ቸርነትህ - የበገና




ለሁሉም ሼር ያድርጉ ላላወቁት እናሳውቅ!
Subscribe ማድረግዎን እንዳይዘነጉ
7.9K views10:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-15 12:55:19



የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ በተመለከተ
የእሑድ ሰላማዊ ሰልፍ ከመቅረጡ አንጻር
ቤተክርስቲያን ላይ አሁን ምን አይነት ችግሮች ሊጋረጡ ይችላሉ? ምንስ ጥሩ ጎን አለው?
አሁንም ቤተክርስቲያንን ለማጥፋት የሚጥሩ የመንግስት አካላት እነማን ናቸው?

እንደ አንድ ኦርቶዶክስ ከእኛ ምን ይጠበቃል የሚለውን በተከታታይ ክፍሎች የተካተተ ነው የሚሆነው።


ሁላችንም የዩቲዩብ ቻናሉን ሰብስክራይብ በማድረግ እንቀላለቀል።
7.8K viewsedited  09:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-15 09:58:56
ማኅበረ ቅዱሳን በሁለት አኅጉረ ስብከቶች የሚገኙ አዳዲስ አማንያንን አስጠመቀ።

የማኅበረ ቅዱሳን ትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ በጎ አድራጊ ኦርቶዶክሳውያንን በማስተባበር ያሠራቸውን በሁለት አኅጉረ ስብከቶች ውስጥ የሚገኙ ሦስት አብያተ ክርስቲያናት ማለትም

1. በከምባታ ጠምባሮ ሀላባ ሀገረ ስብከት የቡጌ ኢየሱስና የጀባ ዶዶባ ቅዱስ ሩፋኤል አብያተ ክርስቲያናት

2. በቤንች ሸኮ፣ሸካ እና ምዕራብ ኦሞ ዞን ሀገረ ስብከት ጋሮ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያንን
በየካቲት 5 እና 6 ቀን 2015 ዓ.ም አስመረቀ፡፡

በምረቃው ዕለታትም 163 አዳዲስ አማንያን ሥርዓተ ጥምቀት ተፈጽሞባቸዋል።

በዕለቱም የአኅጉረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ እና የመምሪያ ኃላፊዎች፣ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
11.0K views06:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-14 20:47:25 ​​VALENTINE'S DAY
ሼር በማድረግ ትውልዱን ከጥፋት እንታደግ

አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለኛ ቤዛ ሆኖ በፍቅሩ የገዛን እጃችንን ለጣኦት እንድንሰጥ አይደለም ብዙ ዋጋ የተከፈለብን እስከ ሞት እንከን በሌለው ፍቅሩ የወደደን መንግስቱን እንድንወርስ እንጂ እንድንጠፋ አይደለም።

የቫላንታይ ቀን ድብቅ እውነታ ስንቶቻችን እናውቃለን? ይህን የቫላታይን ቀን (የፍቅረኛሞች ቀን) ብለን ስንቶቻችን ነን የምናከብረው ? ወይስ ሰው ስላከበረውና የስልጣኔ መገለጫ መስሎን ነው የምናከብረው ???

ከክርስቶስ ልደት በፊት በባቢሎን ፤ቤልዘቡል ፤በግሪክ ፓን ፤ ሮማ ሞሎቅ ፤ በላቲን ሳተርን ለሚባሉት ሰይጣኖች ያላገቡ ሴቶች ደም የሚፈስላቸው ቀይ ልብስ የሚለበስላቸው ጣኦቶች ናቸው ይህ ዛሬ ቫለንታይን ተብሎ የመጣው ማለት ነው።

የሚገርመው ደሞ ሴቶቹ በዚህ ቀን ለመደፈር ብለው እራቁታቸውን ጫካ መግባታቸው ነው በዚህ ቀን የተደፈረች እና ደሟን ያፈሰሰች ሴትም ሆነ ወንድ በጣኦቱ የተመረጠ እና የተባረከ ነው መባሉ ነው ይበልጥ ነገሩን ሰይጣናዊ የሚያደርገው።

ግሪክ አርኬዲያ ብለው በሚጠሩት አስቀያሚ ትርጉም ባለው ተራራቸው ላይ በዚህ ቀን ላይ ነው ያላገቡ ወንድ እና ሴቶቻቸውን ጣኦቱ ስር ወሲብ በመፈጸም ገላቸውን አርክሰው ለሰይጣን የሚገብሩት።

ይህ የሰይጣን ቀን ነው ክርስትና ይሄን ትከለክላለች ታወግዛለች። (ሁሉም ቀን የእግዚአብሔር ነው ግብሩ ነው የሰይጣን የሚያደርገው)

ኢየሱስ ክርስቶስ ከመውለዱ ከዘመናት በፊት አረማውያን ሮማውያኖች Feb 14 ማታ እና ለ Feb 15 ንጋት አጥቢያ የተኩላ አዱኚ ለሚሉት ሉፐርካልያ (luperkalya ) ጣኦት የሚዘጋች ክብረ በአል ነው፡፡

ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ክርስትና ተቀብሎ እውነተኛ የጽድቅ ሃይማኖት መሆኑን በማውጁ ማንኛውም የጣኦት አምልኮ እንዲቀር ቢያስጠነቅቅም የተውሰኑ የሮማውያን ሰዎች ግን በአሉን ማክበር አልተውም።

እንዴት ይህ አረማዊ ባህል ቫለንታይን የሚል ሰያሜ ተሰጠው? ቫለንታይን የሚል ስም በሮማውያን ዘንድ የተለመደ ስያሜ ነው፡፡ ቫለንታይን የጥንታዊ ታዋቂው ሉፐርኩስ ጣኦት ነው።

ሉፐርኩስ በግሪካዎያን ፓን (pan) ተብሎ ሚጠራው ከወገቡ በታች በግ አናቱ ላይ ቀንድ ያለው ጣኦት ነው። በጥንታውያን አይሁድ ደግሞ ይህ ፓን ባል (baal) በሚል ስያሜ ይታወቃል።

ጥንታውያን ሮማውያን ከባቢሎናውያን የቀዱት አረማዊ የልብ (heart) ምልክት ይጠቁማሉ፡፡ በባቢሎናውያን ባል (bal) ልብ የሚል ፍች ነው ያለው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ይህ አረማዊ የልብ ምልክት ለቫለንታይን ቀን (የፍቅረኛሞች ቀን) የምንለው መግለጫነት እንጠቀምበታለን። ባል የባቢሎናውያን ጣኦት ነበር።

በዚህ የሃጥያት ቀን በትንቹ ይህ ይሆናል

1. በዚህ ቀን February 14 በብዙ የሚቆጠሩ እህቶቻችንን ክብረ ንጽህናቸውን (ድንግልናቸውን) ያጣሉ

2. በርካታ ወጣቶች በስካር ምክንያት በሚያሽከረክሩት መኪና ህይወታቸውን እና አካላቸውን ያጣሉ

3. በአለማችን ላይ በከፍተኛ ሁኔታ የአልኮል መጠጥ ሽያጭ የሚከናወንበት ቀን ነው በአጠቃላይ የዝሙት እና ስካር መንፈስ የሚነግስበት በከፍተኛ ሁኔታ ሰይጣን በደም የሚረካበት ቀን ነው።

Valentine day ማለት ሰይጣን በጥልቅ እና ረቂቅ ሃሳብ ብዙዎችን የሚያጠምድበት ቀን ነው አስተውሉ ሰይጣን ከ7ሺህ አመት በላይ የክፋት ልምድ አለው።

እንግዲህ ምርጫው ያንተ/ቺ ነው :- የእግዚአብሔር ወይም የሰይጣን ልጅ መሆን???

" ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል፤ አንተም እውቀትን ጠልተሃልና እኔ ካህን እንዳትሆነኝ እጠላሃለሁ፤ የአምላክህንም ሕግ ረስተሃልና እኔ ደግሞ ልጆችህን እረሳለሁ። "
(ትንቢተ ሆሴዕ 4 : 6)

እግዚአብሔር አምላክ ማስተዋሉን ያድለን።
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
8.2K views17:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-14 13:56:59
ሕገወጡ ስብስብ አሁን በቲክቶክ ላይ Live መግለጫ እየሰጡ ይገኛል
12.7K views10:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-14 13:38:37
አስፈራርተው ወስደውኝ ነው

እንግዲህ ተመልከቱ ክርሰቲያኖች እሁድ እለት ወደ ቅድስት ቤ/ክ በይቅርታ የተመለሱት አባት ያን እለት ቪዲዮውን ያያችሁ አይታቹኋል።ዛሬ ደግሞ ወደ ሕገ ወጡ ሲኖዶስ በድጋሚ ተመልሰዋል።

ጌታ ሆይ ምን ጉድ ነው ???

ምንድነው ቆይ አየሆነ ያለው?
12.8K views10:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-14 13:36:16
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልዑካን እና የሩሲያ ቤተ ክርሰቲያን አገልጋዮች እንዲሁም የመንግስት ባለ ስልጣናት በእንዲህ አይነት መልኩ እየመከሩ ይገኛሉ።
12.1K views10:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-13 22:19:09 የዚህ መንግስት ሌላ ራስ ምታት የካቲት 23
15.7K viewsedited  19:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-13 21:03:35 የኦርቶዶክሳውያን እስር እንደቀጠለ ነው

የማኅበረ ቅዱሳን ጭሮ ማእከል አባል የሆነው ዶ/ር እንዳሻው ዘርፉ በጸጥታ አካላት ተወስዳል

ዛሬ 5:00 አከባቢ ደ/ር እንዳሻዉ ዘርፉን ለጥያቄ እንፈልግሃለን በማለት በማለት አፍነው ወስደውታል።
16.2K views18:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-13 20:53:40
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት (EOTC TV) የኦሮምኛ ቋንቋ ጋዜጠኛ ዲ/ን ዮሴፍ ከተማ በጸጥታ ኃይሎች ታፍኖ ተወሰደ።

ዛሬ ሰኞ የካቲት 6 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 አካባቢ በሥራ ጉዳይ በመንቀሳቀስ ላይ እያለ መካኒሳ አካባቢ ለጥያቄ እንፈልግሃለን የሚሉ የመንግሥት የጸጥታ አካላት አፍነው ወስደውታል።

የኦሮምኛ ቋንቋ ጋዜጠኛ ዲ/ን ዮሴፍ ከተማ በወቅታዊ ጉዳይ ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተደጋጋሚ ቃለ ምልልሶች በማድረግ ወደ ምእመናን ሲያደርስ ቆይቷል።

ምንጭ: EOTC TV
16.3K views17:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ