Get Mystery Box with random crypto!

በታላቅ ድምቀት የተከበረው የ2017 ዓ/ም የሲዳማ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ ፊቼ ጨምበላላ በዓል በሰ | Natnael Mekonnen

በታላቅ ድምቀት የተከበረው የ2017 ዓ/ም የሲዳማ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ ፊቼ ጨምበላላ በዓል በሰላም መጠናቀቁን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሽመልስ ቶማስ የበዓሉን ፍፃሜ አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች ህብረተሰቡና ፖሊስ በጋራ ተቀናጅተው መስራት በመቻላቸው በዓሉ በሰላም ተከብሮ መጠናቀቁን ገልፀዋል።

በዓሉ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ኃላፊነት ለተወጡ ለሁሉም የክልሉ ህዝብ፣ ሌት ከቀን ደከመን ሰለቸን ሳይሉ የፀጥታውን ስራ ላከናወኑ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ ለፌደራል ፖሊስ፣ ለክልሉ ፖሊስ አመራርና አባላት እንዲሁም ለአጋዥ የፀጥታ ሀይሎች በኮሚሽኑ ስም ምስጋናቸውን ያቀረቡት ኮሚሽነሩ በቀጣይም በክልሉ ሁሉም ዞንና ወረዳዎች በዓሉ ቀጥሎ የሚከበር በመሆኑ የተለመደዉን ሰላም የማስጠበቅ ስራ በቅንጅት በመስራት ሁሉም ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።