Get Mystery Box with random crypto!

ትኩረት ለወላጅ አልባ ህፃናት ሃሳቡ የተፀነሰው ከ6 ዓመታት በፊት ነው። መቅደስ የልጆች አድማስ | Natnael Mekonnen

ትኩረት ለወላጅ አልባ ህፃናት

ሃሳቡ የተፀነሰው ከ6 ዓመታት በፊት ነው። መቅደስ የልጆች አድማስ ሙሉ በሙሉ አገር በቀል የሆነና በአርቲስት መቅደስ ፀጋዬ @mekdes_tsegaye_official የተመሰረተ የበጎ አድራጎት ድርጅት ነው::

ድርጅቱን ሙሉ ለሙሉ በመገንባትና በሙሉ አቅሙ ስራውን እንዲጀምር ለማድረግ እስከ አንድ ቢሊዮን ብር የሚያስፈልግ መሆኑን የገለፀችው አርቲስት መቅደስ በመጀመሪያው ዙር 200 ህፃናትን ከመላው ኢትዮጵያ እንደሚቀበል ተነግራለች።

ልዩ ትኩረት እና ጥበቃ ለሚያስፈልጋቸው ወላጅ አልባ ህፃናት ሁሉን አቀፍ እንክብካቤ በመስጠት በቀጣይ የሕይወት ጉዟቸው ስኬታማ እንዲሆኑ ለማድረግ ትኩረቱን አድርጎ የሚሰራ የበጎ አድራጎት ማዕከል እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ላይ በተሰማሩ ተፅእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች በቦርድ አባልነት ተሰይመዋል፡፡ .

ያልተከፈለ ብዙ እዳ አለብኝ በማለት ህልሟን ይዛ ወደ ህዝብ የመጣችው አርቲስት መቅደስ፣ ማእከሉን እውን ለማድረግ ይፋ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀግብር በሳምንቱ መገባደጃ በስካይ ላይት ሆቴል አስጀምራለች።