Get Mystery Box with random crypto!

​​​​​​ሰንበት ሰንበተ ክርስቲያን (እሑድ) እሑድ ማለት ‹‹አሐደ›› ከሚለው የግእዝ ቃል የወጣ | ✞ የማርያም ✞ ፳፩ እና ✞ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ልጆች ፲፫ ✞

​​​​​​ሰንበት
ሰንበተ ክርስቲያን (እሑድ)

እሑድ ማለት ‹‹አሐደ›› ከሚለው የግእዝ ቃል የወጣ ሲሆን ትርጉሙም የመጀመሪያ ማለት ነው፡፡ ይህቺ ዕለት በመጽሐፍ ቅዱስ ‹‹ከሳምንቱ በፊተኛው ቀን›› በመባል ትታወቃለች፡፡

ዮሐንስም በራዕዩ ‹‹የጌታ ቀን›› ያላት ናት (ራእይ 1፤10)፡፡ ቅዱስ ያሬድም በድጓው ላይ ‹‹ዕለተ እግዚአብሔር›› የሚላት ዕለተ እሑድ ናት፡፡

ዕለተ እሑድ እንደ ሰንበት የሚከበርበት ምክንያቶች፡-

እግዚአብሔር ሥራውን የጀመረባት ለሥነፍጥረት መጀመሪያ ዕለተ (ጥንተ ዕለት) ናትና
ዕለተ ሥጋዌ ናት፡፡ ጌታ የተፀነሰባትና እርቅ የተወጠነባት የፍሰሐ ቀን፡፡
ዕለተ ትንሣኤ ናት፡፡ ጌታ ከሙታን ተለይቶ የተነሳባት ዕለት
የቤተ/ክ የልደት ቅን ናት፡፡ መንፈስ ቅዱስ ለሐዋሪያት የወረደባት ኃይልና ፅናትን ያገኙባት ዕለት
ጌታ በክበበ ትስብእት በግርማ መለኮት ዳግም በቅዱሳን መላእክቱ ታጅቦ በጌትነቱ ለፍርድ የሚመጣባት ታላቅ የፍርድ ቀን ናትና የተለያዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶች የሚካሄዱባት ዕለት ናት(1ኛ ቆሮ 16፤1)
የሐዋሪያት ዘመንም በጤሮዓዳ ያሉ ክርስቲያኖች እሑድ ቀን ይሰበሰቡ ነበር (የሐዋ. 20፤7 በቤተክርስቲያን ታሪክ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ዕለተ እሑድ የክርስቲያኖች ሰንበት ናት በማለት
ሥራ እንዳይሰራባት አዋጅ አስነግሮ ነበር፡፡

ምንም እንኳን ይህቺ ዕለት በሐዲስ ኪዳን መከበር የጀመረ ቢሆንም በብሉይ ኪዳን ከፋሲካ በፊት የሰንበት (የቀዳሚት) ማግስት በመባል በኩራት እና ቀዳሚያት የሚያቀርቡበት ቀን ነበር። (ራዕ 1፡10)

በቀዳሚት ሰንበት ቅዱስ እግዚአብሔር ከሥራው ሁሉ አርፎ ሥጋዊ እረፍትን ለሰው እንዳስተማረ በእሑድ ቀን (በሰንበተ ክርስቲያን) በጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት የተገኘውን የዘላለማዊ የነፍስ ዕረፍት የምናስብበት ነው፡፡ (ዕብ 4፡1-10)

ከሰንበት ረድኤት በረከት ይካፍለን!
ሌሎች እህት ወንድሞች ይማሩበት ዘንድ አጋሩ

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
@muzemur
@muzemur
@muzemur

✞✞✞✞✞✞
✞✞✞✞✞✞

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✞✞✞ @muzemur ✞✞✞

✞✞✞✞✞✞
✞✞✞✞✞✞
@Muzemur
@muzemur
@muzemur