Get Mystery Box with random crypto!

#ጾመ_ሐዋርያት (ሰኔ 6 - ሐምሌ 5) (የ2014 ዓ.ም) ‹‹ይህ ጾም በአላዋቂዎችን እና በቤተ | ✞ የማርያም ✞ ፳፩ እና ✞ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ልጆች ፲፫ ✞

#ጾመ_ሐዋርያት (ሰኔ 6 - ሐምሌ 5)
(የ2014 ዓ.ም)

‹‹ይህ ጾም በአላዋቂዎችን እና በቤተክርስቲያን ጠላቶች የሽማሌዎች ጾም እየተባለ ምዕመናን እንዳይጾሙት ብዙ ተለፍቷል..››

በየዓመቱ በዕለተ ሰኑይ የሚጀምሩ ሶስት አጽዋማት ብቻ አሉ ፡፡ ከእነርሱ መካከል አንዱ ጾመ ሐዋርያት ነው ፡፡ ቅበላው በዕለተ እሑድ ይሆንና ጾሙ ሰኞ ይውላል ፡፡ የ2014 ዓ.ም ጾመ ሐዋርያት ሰኔ 6 ይገባል ፡፡

ይህ ጾም እራሱ ጌታቸን ኢየሱስ ክርቶስ ትንቢት የተናገረለት ጾም ነው፡፡
ይህ ታላቅ ጾም የዛሬ 1901 ዓመት በፊት በራሳቸው በቅዱሳን ሐዋርያት የተጀመረ ጾም ነው ፡፡ ከሰባቱ አጽዋማት መካከልም አንዱ ነው ፡፡
ፈሪሳውያ ጌታችንን ደቀ መዛሙርትህ አይጾሙም ብለው በጠየቁት ጊዜ እርሱም ‹‹ ሚዜዎች ሙሽራ ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉን ? ነገር ግን መሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል ፤ በዚያ ጊዜም ይጾማሉ ፡፡ በአረጀ ልብስ አዲስ እራፊ የሚያኖር የለም ፤ መጣፊያው ልብሱን ይቦጭቀዋልና ፤ መቀደዱም የባሰ ይሆናል ፡፡ በአረጀ አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም ፤ ቢደረግ ግን አቁማዳው ይፈነዳል የወይን ጠጁም ይፈሳል ፡፡አቁማዳው ይጠፋል ፡፡ ነገር ግን አዲሱን የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ያኖረዋል ሁለቱም ይጠባበቃሉ ፡፡›› ማቴ 9 ፥ 14-17 አላቸው ፡፡ይህ ቃለ እራሱ ጌታችን መድኀኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ ስለ ጾመ ሐዋርየት የተናገረው ትንቢት ነው ፡፡

‹‹#መሽራው_ከተወሰደ በኃላ›› ማለት ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሰማይ ካረገ በኃላ ማለት ሲሆን ይህን ጾም ከዕረገት በኃላ የምንጀምረው ፤ ይህን ምሳሌ በማድረግ ነው ፡፡ አስር ቀን ዘግይቶ መጀመሩም የሐዋርያት ሰውነት ለጾሙ መዘጋጀት ነበረበትና ነው ፡፡

የዚህን ማብራርያ በቀጣይ ጽሁፋችን እንመለስበታልን፡፡
ይህ ጾም በአላዋቂዎችን እና በቤተክርስቲያን ጠላቶች የሽማሌዎች ጾም እየተባለ ምዕመናን እንዳይጾሙት ብዙ ተለፍቷል ልናውቅ የሚገባው ነገር ግን ሐዋርያት ዓለምን ዞረው ከማስተማራቸው በፊት ይህን ጾም ጾመዋል ፡፡ በዚህም ጌታችን የተናረው ተንቢት ተፈጽሟል፡፡ ከሰባቱ አጽዋማትን አንዱ ነው ፡፡ በዚህ ምክንያት ይህን ጾም ታላቅ እና ልዩ ያስብለዋል ፡፡ ይህንን አውቀን ሁላችንም ልንጾመው ይገባል ፡፡