Get Mystery Box with random crypto!

Mushitaq tube ሙሽታቅ ቲዩብ

የቴሌግራም ቻናል አርማ mushitaq_tube — Mushitaq tube ሙሽታቅ ቲዩብ M
የቴሌግራም ቻናል አርማ mushitaq_tube — Mushitaq tube ሙሽታቅ ቲዩብ
የሰርጥ አድራሻ: @mushitaq_tube
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 290
የሰርጥ መግለጫ

#هدفنا الأكبرهو الاتباع الحق / ونشر الخير@
እውነታን መከትል እና# /ኸይርን ማስፋፋት
Chanalun
https://t.me/ oenAgZ8QStdlZDk0
☟︎︎︎ወደ #YouTube ቻናላችን☟︎︎︎
https://youtube.com/channel/UCU9vnAaFwHNYCN0WQE_2ZJA

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-12-11 22:16:00 ከአቡ ሁረይራ እንደተወራልን ነብያችን ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም ሰውባን ለተባለ ሶሀባ እንዲህ አሉ

"ሰውባን ሆይ ለወደፊት ህዝብ ሁላ ተሰብስቦ  ይህን እስልምና ለማድ እንደቀረበ እንጀራ ሲቆራርሱት ብታይ ምን ይሰማሀል??"

ሰውባን:  "ትንሽ ስለሆነ ነው የሚቆራርሱን???"

ነብያችንም
  "ላ እንዲያውም ያኔ በጣም ብዙ ናችሁ ነገር ግን ልክ እንደ አቧራ ናችሁ ሰብሳቢ የላችሁም ቀልባችሁም ላይ ወህን ይገባል" አሉ
ሰውባን:  ወህን ምንድን ነው?

ነብያችን:  "የዱንያ ውዴታና የሞት ፍራቻ"
አዎን ባሁን ግዜ ያለንበትን ማንነት ነው የተናገሩት
ዱንያም አብሮን ላይዘልቅ ሞትም ላናመልጠው.... ያሳዝናል
አየህ ግን ወዳጄ ቁጥራችን በዝቶ ለምን እንደምንሸነፍ???
6 views19:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-08 22:00:58 #ታታር_ከየእጁጅና_መእጁጅ_በፊት_የመጡ_የእጁጅና_መእጁጆች
ክፍል 6
ወዳጄ
አየህ በድል ደስታ አየቦረቁ የመጣውን ፈተና???

የዱንያ ፍቅር ከባድ ነው።
የቱርኩ አሚርና የሀራቱ አሚር የምርኮ ድርሻቸውን ጠየቁ። የመሪነትን ቦታም ፈለጉ አልተስማሙም ተጨቃጨቁ፤ ከዚያም ሰይፍ ተማዘዙ። አዎ የታታር ወታደሮች ገና ሳያልቁ በምርኮ ገንዘብ ሰይፍ ተማዘዙ።
በትንሹ ተጋደሉ ከተገደሉት ውስጥ የሰይፈዲን ወንድም ነበር። ሰይፈዲን በغግራቅ በዚህ ተናዶ ወታደሩን ይዞ ለመሄድ ወሰነ። ጀላሉዲን ማድረግ የሚችለውን ሁሉ አድርጎ እንዲቀር ተማፀነው። እሺ ሊል ግን አልቻለም። ሙስሊሞች ተለያዩ። ያ አሏህ

የሰይፈዲን ወታደር መቀነስ በሙስሊሞች ውስጥ ክፍተት ፈጠረ። ቺንጊስ ካን ያለ የሌለ ሀይሉን ይዞ ሊፋለም ወደ ገዝና ተንቀሳቀሰ። ሙስሊሞች ፍርሀት ዋጣቸው። ጀላሉዲን ባለው ሰራዊት ታታሮችን መግጠም እንደማያዋጣ ስላወቀ ወታደሩን ይዞ ወደ ደቡብ ሸሸ። ቺንጊስ ካን ግን የገባበት ገብቶ ለመፋለም ቆርጧል። ጀላሉዲን ወታደሩን ይዞ እንዳባቱ ከከተማ ወደ ከተማ እየሸሸ ፓኪስታንን አቆራርጦ ህንድና ፓኪስታንን የሚለየው የኢንደስ ወንዝ ሲደርስ የቺንጊስ ካን ሰራዊት  ደረሰባቸው። ከፊት ለፊታቸው የኢንደስ ወንዝ ከኋላቸው የቺንጊስ ካን ለአይን የሚያታክት ሰራዊት!
... ከጦርነት ውጭ ምርጫ የለም።

እጅግ ከባድ ፍልሚያ አደረጉ። ከዚህ ጦርነት አንፃር የእስካሁኑ ጦርነቶች ጨዋታ ነበሩ ማለት ይቻላል። #ታታሮች ለበቀል #ሙስሊሞች ለመዳን! ጦርነቱ ሶስት ቀን ቀጠለ። በአራተኛው ቀን ከሁለቱም በኩል የተገደሉ ሰዎች በጣም ስለበዙ ሁለቱም ጦርነቱን አቁመው ቀሪ ሰራዊታቸውን ማስተካከል ያዙ።

በዚህ መሀል ጀላሉዲን ጀልባ አስመጥቶ  ፈጣን ውሳኔ ወሰነ ሽሽት!!!.

ከቅርብ ሰዎቹ ጋር በመሆን ጀልባቸውን ተሳፍረው ወደ ህንድ አመሩ። ትተው የመጡት ግን ታታርን ብቻ አልነበረም።

ይልቁንስ የሙስሊሞችን መሬት፣ ከተሞችን፣ ሙስሊም ነዋሪዎችንም ነበር ለታታር አስረክበው የሸሹት።

የታታሮችን ጭካኔ ዳግም ማስረዳት አይጠበቅብኝም።
አፍጋኒስታን/ገዝና ገብቶ ወንዶችን ምንም ሳያስቀር አረደ፣ ሴቶችን አንድም ሳያስተርፍ ማረከ፣ ቤቶችን ምንም ሳይተው አቃጠለ። የገዝና ከተማን ከካርታ ሰረዛት። ቺንጊስ ካን ከማረካቸው ውስጥ የጀላሉዲን/የንጉሱ ልጆችም ነበሩ። ሁሉንም አረደ ። ቺንጊስ ካን ሲመኘው የነበረውን አፍጋኒስታንን እንዲህ በቀላሉ በእጁ አደረገ።

በዚህ መልኩ ታታሮች ከቻይና ተነስተው ካዛኺስታን፣ ኡዝቤኪስታን፣ ቱርክማኒስታን፣ አፍጋኒስታን፣ ኢራን፣ አዘርቢጃን እና አርሜኒያ በእጃቸው ገቡ። ኢራቅንም ተቃርበዋል። የሚገርመው ይህን ሁሉ የተቆጣጠሩት በአንድ አመት ውስጥ ነው በ617 ዓ.ሒ!!!
በታሪክ እንዲህ አይነት ፈጣን ወረራ ሰምቼ አላውቅም።

በወረራቸው ለመያዝ የሚመቸውን ገንዘብ እየያዙ የማይመቸውን ያቃጥላሉ።

ከዛስ ጉዞአቸውን...
ወዴት ያደርጉ ይሆን??
ውይ ታታር  ክፍል
ይቀጥላል....
https://t.me/+oenAgZ8QStdlZDk0
42 views19:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-07 16:59:52 #قصة_ታሪክ__ወሬ

ጥበብ_በንግግርህ_አትራፊ_ሁን

አንዴ አንድ ንጉስ በህልሙ 32 ጥርሱ በሙሉ ሲረግፍ አየ ከዛም ይህን ህልም ለማስፈታት አንድ ህልም ፈች ዘንድ ሄደና ጠየቀው
ህልም ፈቹም ተደናግጦ እውነት አንተ ነህ ያየኸው??  ሲል ጠየቀው

ንጉሱ:  አዎ
ህልም ፈች:  ሁሉ ቤተሰብህ ዘርህ እንዳለ ሊያልቅልህ ነው
ንጉሱም በንዴት : ወታደሮችን ግደሉት ብሎ ወደ ሌላ ህልምፈች ሄደ ሁለተኛውም ይህንን መልስ መለሰ እንደመጀመሪያው ህልም ፈች እጣ ፋንታ ደረሰው

አሁንም ሶስተኛ ህልም ፈች ዘንድ ሄደ ሶስተኛው ፈችም
"አንተ ነህ ያየኸው??
ንጉስ:  አዎን
ህልም ፈች:   ማሻአሏህ አረ ዘይረኝ ደስ የሚል ነው
ንጉሱ:  ምንድን ነው??

ህልም ፈች:   "ከቤተሰቦችህ ከዘርህ ሁላ እድሜው ረዥም አንተ ነህ"  አለው

ንጉሱም በፍቹ ተደስቶ ገንዘብ ሸልሞት ሄደ

አየህ ንግግር መናገርህን ሳይሆን አነጋገርህን ተመልከት
ሶስቱም የተናገሩት አንድ አይነት ቢሆንም ሁለቱ ሞትን አንዱ ገንዘብን አተረፉ
በንግግርህ አትራፊ ሁን
https://t.me/+oenAgZ8QStdlZDk0
44 views13:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-07 09:01:57 #ታታር_ከየእጁጅና_መእጁጅ_በፊት_የመጡ_የእጁጅና_መእጁጆች
                ክፍል 5
ታታሮች መረውን ካወደሙ በኋላ ወደ ነይሳቡር አመሩ።
       *ነይሳቡር*
በከተማው ውስጥ በቂ የጦር ሀይል ቢኖርም የመረው አስደንጋጭ ዜና ልባቸውን በፍርሃት ስለሞላው ለታታር እጅ ሰጡ። የቺንግስ ካን ልጅ የከተማዋን ነዋሪዎች በሙሉ ወደ በረሃ ወጥተው ጭንቅላታቸው እንዲበጠስ አዘዘ። ሴቶችን ማረከ። ከተማዋን ለአስራ አምስት ቀናት ለገንዘብ ፍለጋ ሲሉ ቆዩባት። በዚህ መልኩ ነይሳቡርን በቀላሉ ቅሪት አድርገው ለቀቋት።

           *በሀራት*
ተረኛዋ የኹራሳን ከተማ ናት።  ሰሜን ምእራብ አፍጋኒስታን የምትገኝ ከተማ ስትሆን በጣም ሰፊና ብርቱ ከተማ ብትሆንም የመረውና የነይሳቡር እጣ ፋንታ እልቀረላትም። ወንዶቿ ተገደሉ፤ ሴቶቿ ተማረኩ።
*"መሊክ ኻን"* የተባለው ንጉሷ ግን ከተወሰኑ ወታደሮች ጋር ወደ *ገዝና* ከተማ ሸሽቶ ማምለጥ ቻለ። ኹራሳንና በሀራት አከተሙ።

ቀጣይ እቅዳቸው የኸዋርዚም ዋና ከተማን(ኸዋሪዝም ትባላለች) delete ማድረግ ነው። በጀይሁን ወንዝ ፊት ለፊት ነች። ባላት ትልቅ ወሳኝነት ቺንግስ ካን ብዙውንና ታላቁን ሰራዊት ነበር የላከው። ይህ ሰራዊት ኸዋርዚምን ለ5_ ወር ከቦ ቢቆይም መክፈት ስላልቻለ በተጨማሪ ሀይል ጥቃታቸውን አጠናክረው ምሽጉን ደርመሰው መግባት ቻሉ። አስፈሪ ፍልሚያ ተካሄደ። በመጨረሻም ድል ለታታሮች አመዘነ። ሙስሊሞች እየሸሹ በየጉድጓዱ መደበቅ ጀመሩ።

ታታሮች መቆጣጠር ሲሳናቸው  እጅግ ዘግናኝ እርምጃ ወሰዱ።

ይኸውም የጀይሁንን ወንዝ ግድብ በማፈረስ ከተማዋን በጎርፍ አጥለቀለቋት።ቤቶች ተደረመሱ። ከኸዋርዚም ሰዎች አንድም አልተረፈም። ከሰይፍ የዳነ ሁሉ በጎርፉ አለቀ። ኸዋርዚም ከከተማነት ወደ ባህርነት በአንድ ፀሀይ ተሸጋገረች። ከዚያ በፊት ከተማዋን የሚያውቃት አሁን የት አካባቢ እንደነበረች ማወቅ አይችልም። ያሳዝናል ኸዋርዚም ስላችሁ ያሁን ሰዎች አታውቋት ይሆናል ምክንያቱም ከካርታ ላይ ሰረዟታ!!።
             *ገዝና*
ታታሮች ቀጣይ እርምጃቸው የኸዋርዚምን ደቡባዊ ግዛት መዝመት ነው። ደቡብ ኸዋርዚም የሙሐመድ ኢብኑ ኸዋርዚም ሻህ ልጅ ጀላሉዲን ነው የሚያስተዳድረው። ጀላሉዲን የታታሮች ሙሉ ዜና ደርሶታል። የኹራሳንና የኸዋርዚም መውደቅ የአባቱ ሞት ደርሶታል። ቀሪው እሱ መሆኑ ኃላፊነቱን አክብዶበታል። ቢሆንም ግን ሰራዊት እያሰባሰበ ነው። የጀላሉዲን መናገሻ ከተማው ገዝና የምትባል ከተማ ናት (ከካቡል እቅራቢያ በተራሮች የተከበበች አፍጋኒስታናዊ ከተማ ነች)።

ጀላሉዲን ትልቅ ሰራዊት ማዘጋጀት ቻለ። በቅርቡ የሸሸው የሀራቱ አሚር *መሊክ ኻን* ከቀሪው ሰራዊቱ ጋር በመሆን ከጀላሉዲን ጎን ታታርን ለመፋለም ተዘጋጅቷል። ከቱርክ ሙስሊም መሪዎች አንዱ የሆነው *ሰይፈዲን በغግራቅ* ሰላሳ ሺህ ወታደር አስከትሎ ጀላሉዲንን ተቀላቀለ።

ሰይፈዲን ጀግና፣ በሳልና ብልህ መሪ ነው። ወታደሮቹም እንዲሁ። ጀላሉዲን ሰራዊቱን አስከትሎ ከገዝና ከተማ ወጣ ብሎ በለቅ የተባለ በተራራ የታጠረ ቦታ ላይ ሰፍሮ ታታርን መጠበቅ ጀመረ። ታታሮች ደረሱ። ፍልሚያው ተጀመረ፤ ሙስሊሞች ተሟሙተው ተጋደሉ። ከኸዋሪዝም ያላቸው ቀሪ ሀገር ይሄ ነው።

የጀላሉዲን አመራርና የሰይፈዲን በግራቅ ወታደሮች ጀግንነት የሙስሊሞችን መንፈስ አደሰ። ፍልሚያው 3 ቀን ዘለቀ። ታታሮችን ውሀ በላቸው። የአሏህ እርዳታ መጣ። *ሙስሊሞች ድል አደረጉ* ። ታታሮች እግሬ አውጪኝ ብለው ወደ ቺንግስ ካን ፈረጠጡ። አላሁ አክበር! አሏሁ አክበር! አሏሁ አክበር!!!

  ሽሽት የማያውቁት ታታሮች ለመጀመሪያ ጊዜ ተሸነፉ። አዎ! ሙስሊሞች በአንድነት ሲፋለሙ የአላህ እገዛም ተጨመረ።
ጀላሉዲን ቺንግስ ካንን ለዳግም ፍልሚያ ጋበዘው። ቺንግስ ካን በፍርሀት በጣም ግዙፍ ሰራዊት በልጁ አሚርነት ላከ። ከመጀመሪያው የከበደ ፍልሚያ  ተካሄደ። ሱብሀነሏህ አሁንም ድሉ የሙስሊሞች ሆነ።


  ከ10,000+ በላይ ሙስሊም ምርኮኞችን ከታታሮች ነፃ አወጡ። በጣም ብዙ ገንዘብ ማረኩ። ይህን ታላቅ ድል አጣጥመው ሳይጨርሱ ትልቅ አደጋ አንዣበበ።
ምንድን ነው???
ክፍል
ይቀጥላል.....
55 views06:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-03 21:27:33 አጂብ
አቡ ዘር አል ጊፋሪይ
ለምን አቡ ዘር ተባሉ
ትክክለኛ ስማቸው ጁንዱብ ኢብኑ ጁናዳህ ነው
#ጊፋሪይ
    የጎሳቸው ስም ነው ከመካ ወጣ ብለው የሚኖሩ ማንም የሚፈራቸው የሽፍታ ዘሮች ነበሩ

ዋናው ነጥብ  #አቡ_ዘር ለምን ተባሉ???
ዘር ማለት ትንሽየ ብናኝ ነው

ንግድ እየነገዱ ሳለ ከሚዛናቸው በስህተት ብናኝ ገብቶባቸው ተፀፅተው እሪ ብለው ጮሁ
በዚህም ስቀውባቸው አቡ ዘር(የብናኝ አባት) አሏቸው

ከኛ ግን ስንቶች ነን በየምክንያቱ ምናጭበረብር??
አሏህ ይጠብቀን 
https://t.me/Mushitaq_Tube
68 views18:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-02 08:24:58 #ታታር_ከየእጁጅና_መእጁጅ_በፊት_የመጡ_የእጁጅና_መእጁጆች
ክፍል 4

ኹዋሪዝምና ኹራሳን ታላላቅ ሀገሮች ናቸው
ከኹዋሪዝም
ቡኻራ ሰምረቀንድ ጠፉ
ቀጣዩዋ ሰለባ ኹራሳን
ከኹራሳንም ከተማ
ረይ
በለኽ
ጧሊቃ
መረው...
በሁሉም የግፍ በትራቸው ተዳረሰ። እንዴት ነበር

በለኽ ዜናው ስለደረሳቸው መምጣታቸውን ሲሰሙ በፍርሀት ራዱ።
ገና በገና የደህንነት ቃል ኪዳን ጠየቁ። ታታሮች ቃላቸውን ሰጥተው ከተማዋን ተረከቡ። ቃላቸውንም አላጠፉም። ጉድ በል! ታታሮች ቃላቸውን ጠበቁ??

ጉዟቸውን ወደ ጧሊቃን አድርገው ምሽጓን ከበቡ። ስለ ከበዳቸው ከቺንግስ ካን አጋዥ ሀይል አስልከው ከተማዋን በኃይል ከፈቱ። እንደለመዱት ሴት ወንድ፣ ህፃን አዋቂ ሳይሉ ጨፈጨፉ።

ቺንግስ ካን የበለኽን ሰዎች ሳይጨፈጭፍ የተዋቸው ምክኒያት አሁን ግልፅ ሆነ።

የመረውን ሙስሊሞች እንዲዋጉ አስገደዳቸው። ታታሮችን የፈራው ልባቸው በሙስሊም ወንድሞቻቸው ላይ ወኔ አመጣ። ቺንግስ ካን በልጁ የሚመራ በመቶ ሺ..ዎች የሚቆጠር ሰራዊት ወደ መረው ላከ። የበለኽ ሙስሊሞችም ነበሩ። የመረው ሙስሊሞች ግን በሁለት መቶ ሺህ የሚገመት ሰራዊት አዘጋጅተው ጠበቋቸው። ተፋጠጠጡ።
ፍልሚያው ተጀመረ፤ ሙስሊሞች በፅናት ተሟሙተው ተጋደሉ። ከሁለቱም ወገን ሰወች ወደቁ። ብዙም ሳይቆይ ግን የጦሩ ሚዛን ወደ ታታሮች አደላ። በአራተኛው ቀን የታታሮች የጦር መሪ (የቺንግስ ካን ልጅ) ለመረው ከተማ አሚር "ራስህንና ህዝብህን አታስጨርስ፤ እኛ ጋር ና አሚርነትህን እናፀናልሀለን፤ አካባቢውንም ለቀን እንሄዳለን" የሚል መልዕክት ላከ።

የመረው አሚር የታታሮችን ቃል አመነ፤ ቃለቸውን እንደሚጠብቁ ራሱን አሳመነ። በተባለው መሰረት ወጥቶ የቺንግስ ካን ልጅ ማረፊያ ዘንድ ሄደ። የታታሩ መሪ አከበረው፣ በደማቁ ተቀበለው። ከዚያም "አጋዦችህንና የከተማውን ታላላቅ ሰዎች አምጣቸውና ለስልጣን የሚገባ ካለ መርጠን እንሾመዋለን፤ ከኛም ጋር ይሆናል" አለው።

የመረው አሚር አሁንም ተታለለ።

የቺንግስ ካን ልጅ በእጁ ሲገቡ እንዲታሰሩ አዘዘ። ከዚያም ሁለት መዝገብ ሰጥቶ አንደኛው ላይ፦ የመረው ከተማ ባለ ሀብቶችና ከበርቴ ቱጃሮችን እንዲመዘግቡ፣ ሁለተኛው ላይ ደግሞ የባለ ሙያዎችን ስም እንዲመዘግቡ አስገደዳቸው። ከዚያም የከተማዋ ሙሉ ነዋሪወች እንዲመጡ አዘዘ። ከሰባት መቶ ሺህ የሚልቁት የከተማው ነዋሪዎች አንድም ሳይቀሩ መጡ።
የሚከተሉትን ትዕዛዛት አስተላለፈ፦

_ትዕዛዝ 1፦ የከተማው አሚርና ባለ ስልጣናት እንዲገደሉ

_ ትዕዛዝ 2፦ ባለ ሙያወችን ጠርተው ወደ ታታሮች ሀገር ወደ ሞንጎሊያ ተልከው በሙያቸው እንዲያገለግሉ።
_ ትዕዛዝ 3፦ ባለሀብቶችና ነጋዴዎችን ገንዘባቸው የት የት እንዳለ እስኪናገሩ እንዲቀጡ፤ እንዲገረፉ።
_ ትዕዛዝ 4፦ ከተማው ውስጥ ገንዘብና የገንዘብ ዘር ያለበት ነገር ሁሉ እንዲወረስ። ገንዘብ ፍለጋ ከተማዋን ሶስት ቀን ፈተሿት። የአሚሮችን ቀብር ቆፈረው ፈተሹ
_ዘግናኙ ትዕዛዝ 5፦
የከተማዋ ነዋሪዎች በሙሉ እንዲታረዱ አዘዘ። ሴቱን ወንዱንም ህፃናቱንም ሁሉንም እንደበግ አረዷቸው። ሰባት መቶ ሺህ ሰው በአንድ ቀን!? 700 ሽህ??
ታማኝ ኡለማዎች ኢብኑል አሲር ኢብኑል ወርድይ አህመድ ዘይኒ ዳህላን ባይጠቅሱት ወላሂ ለማመን ይከብዳል።
በምን ሰበብ እንደገደሏቸው ታውቃላችሁ? ከተማዋን ልንከፍት ስንመጣ ተከላክላችኋል በማለት ሳታማሀኝ ብላኝ ነው ነገሩ! በዚህ መልኩ መረውን ባዶ ከተማ አደረጓት።
ከዛስ ተረኛዋ ማን ናት???
  ነይሳቡር ምን ተፈረደባት ይችስ?
ክፍል
ግፉ አላለቀም ይቀጥላል....
https://t.me/+oenAgZ8QStdlZDk0
71 views05:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-01 10:18:38 ከአቡ ሁረይራ እንደተወራልን ነብያችን ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም ሰውባን ለተባለ ሶሀባ እንዲህ አሉ

"ሰውባን ሆይ ለወደፊት ህዝብ ሁላ ተሰብስቦ  ይህን እስልምና ለማድ እንደቀረበ እንጀራ ሲቆራርሱት ብታይ ምን ይሰማሀል??"

ሰውባን:  "ትንሽ ስለሆነ ነው የሚቆራርሱን???"

ነብያችንም
  "ላ እንዲያውም ያኔ በጣም ብዙ ናችሁ ነገር ግን ልክ እንደ አቧራ ናችሁ ሰብሳቢ የላችሁም ቀልባችሁም ላይ ወህን ይገባል" አሉ
ሰውባን:  ወህን ምንድን ነው?

ነብያችን:  "የዱንያ ውዴታና የሞት ፍራቻ"
አዎን ባሁን ግዜ ያለንበትን ማንነት ነው የተናገሩት
ዱንያም አብሮን ላይዘልቅ ሞትም ላናመልጠው.... ያሳዝናል
አየህ ግን ወዳጄ ቁጥራችን በዝቶ ለምን እንደምንሸነፍ???
https://t.me/mushitaq_tube
59 views07:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-30 17:23:10 #ታታር_ከየእጁጅና_መእጁጅ_በፊት_የመጡ_የእጁጅና_መእጁጆች

               ክፍል 3

የሰቆቃው አመት! 617ተኛው አመተሂጅራ
...ይህ አመት በእስልምና ታሪክ አምሳያውን ያጣ አመት ነው። ታዋቂው አሊም ኢብኑል አሲር በጊዜው ከነበሩትና ግፉን ካዩት አንዱ ነበሩ።
እንዲህ ይላሉ " አንድ ሰው አላህ ኣደምን ከፈጠረ ጀምሮ እንዲህ አይነት ዘግናኝ መከራ አልታየም ቢል በፍፁም አልዋሸም። እስከ የውመል ቂያማም ከየእጁጅና መእጁጅ ውጭ እንዲህ አይነት ጅምላ ጭፍጨፋ ይከሰታል ብየ አላምንም። ሴት፣ ህፃናት፣ አዛውንት ሳይለዩ አረዱ። የእርጉዝ ሆድ ቀደው ሽሉን ፈጠፈጡ!"

ይህ ግፉን በአይኑ የተመለከተ ሰው ንግግር ነው! ።
ቡኻራን ከጨረሱ ቡጏላ ወደ ሰመርቀንድ/ኡዝቤኪስታን አመሩ። በጉዟቸው ወቅት ምርኮኞችን በሚያሳቅቅ ሁኔታ የደከሙትን እየገደሉ ይዘዋቸው ሄዱ።
ምርኮኞችን፦

-ባንዲራ አሸክመው ቁጥራቸውን ያበዙባቸዋል።
--በፍልሚያ ወቅት ከፊት በማሰለፍ እንደ ጋሻ ይጠቀሙባቸዋል።
--እንዲዋጉ በማድረግ የሰው ሀይላቸውን ይቆጥብቧቸዋል።
--ሊከፍቱት በሚፈልጉት ከተማ ፊት ለፊት በማረድ እጅ ካልሰጡ ይህ እንደሚጠብቃቸው ያስፈራሩባቸዋል።
--ወታደር ከተማረከባቸው እንደ መቀየሪያ ይጠቀሙባቸዋል።

ቺንግስ ካን ሰመረቀንድን ከበበ። የከተማዋ ወታደሮች ወጥተው ሊፋለሟቸው ይገባ ነበር። ግና ይህ አልሆነም።
ፍርሃት ልባቸውን ሞላው። ከከተማው የኢስላም ፍቅርና ወኔ ያላቸው ጀግና ኡለማዖችን ጨምሮ ሰባ ሺህ ሙጃሂዶች ለመፋለም ቆረጡ። የፈሩት ወታደሮች ይህን ያህል ብዛት ያለው ህዝብ እንደሚዋጋ እያወቁ አብረው ለመፋለም አሁንም አልተስማሙም።

ምንም ልምድ የሌላቸው ሰባ ሺዎቹ ሙጃሂዶች ለመፋለም ወጡ።
የታታር ሰራዊት ሙጃሂዶቹን ሲያይ ሸሹ። ሳያስቡት ከከተማው ራቁ። ሰባ ሺውም ሙጃሂድ እግረኞች ነበሩ። አንድ እንኳ ፈረስ አልነበራቸውም። ድንገት ሳያስቡት አንድ አደጋ መጣባቸው። ድንገት የታታር ጦር ከቧቸዋል። ሲሸሽ የነበረው የታታር ጦር ፈርተው ሳይሆን ስትራቴጂ ነበር። ከባድ ፍልሚያ ተደረገ። በታታሮች ድል አድራጊነት ተጠናቀቀ። ከሙስሊሞች ስንት እንደተገደለ ታውቃላችሁ?? አንዳቸውም አልተረፉም!...ሰባ ሺዎቹም ሸሂድ ሆኑ!
አዎ ሰመር ቀንድ ሰባ ሺህ ሙጃሂዶቿን በሰዓታት ውስጥ ተነጠቀች
ታታሮች እንደገና ሰመርቀንድን ወረሩ።

የከተማዋ ወታደሮች በሰላም ከተማዋን ሊያስረክቡ ተስማሙ:: ታታሮችም የደህንነት ቃል ሰጧቸው። ታታሮች እንደገቡ ወታደሮቹን መሳሪያቸውንና መጓጓዣቸውን ተረክበው  በቃላቸው መሰረት አደረሷቸው። ወደ አኼራ አዎ ሁሉንም አረዷቸው። ከዚያማ ሴት፣ ወንድ፣ ህፃን፣ አዛውንት ሳይመርጡ ያሻቸውን ጨፈጨፉ። ቁጥራቸውን አላህ ብቻ የሚያውቀው ሰዎች የታታሮች ሰይፍ ሰለባ ሆኑ። ገንዘባቸው....

የሙሐመድ ኢብኑ ኸዋርዚም ሻህ አላማ ተሳካ! ሽሽቱ ተሳካለት!!! ሱብሀነላህ!
ሙሐመድ ወዲያው ጦበሪስታን/ስፔን እንደገባ ሞተ።
ተዋርዶ ሞተ። የቱ ነበር ክብር?
በአላህ መንገድ ሲዋጋ መሞት ወይስ በሽሽት? ሰው የመሞቻ ጊዜውን መምረጥ አይችልም ግን የአሟሟቱን ሁኔታ መምረጥ ይችላል!
ፍርሃት እድሜን እንደማይጨምር ሁሉ ጀግንነት እድሜን አይቀንስም።

ቡኻራን [የኢማሙል ቡኻሪይን ሀገር]  አጠፉ
ሰምረ ቀንድን አስወገዱ

አሁንስ ተረኛዋ ማን ትሆን???
ክፍል   ይቀጥላል
https://t.me/mushitaq_tube
62 views14:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-29 20:28:12 #من_ديوان_الرجال_የወንዶች_መዝገብ

እስኪ ዛሬ አንዲት ታሪክ ሀሁ ልበላችሁ
ጀግና ሳለን
አንዴ ኻሊድ ካፊር ጋር ጦርነት እየገጠሙ ሳለ የካፊሩ ንጉስ ህዝቦቹን ሊያበራታ
  የሙስሊሞችን መሪ ጭንቅላት የሚያመጣልኝ ልጄን እድረዋለሁ አለ ከዛ  ኻሊድም ቀበል አርገው
የንጉሱን አንገት የሚቆርጥልኝ
ያችን ቢክራ ልጁን እጀባዋለሁ አሉ
ጦርነቱም በሙስሊሞች አሸናፊነት ተጠናቀቀ

ኻሊድም የገቡትን ቃል ለመሙላት ሶሀባዎችን ጠየቁ
"ማን ነው ንጉሱን የገደለ??? "
ይቻት ልጂቱ

ምንም ምላሽ የለም
      ኻሊድም ሴቲቷን  ያባትሽን ገዳይ ታውቂዋለሽ??  አሏት አወ አለች
ኻሊድም አሳይኝ አሏት
አማትራ አማትራ ......
  ያውልህ  ያ ነው ያባቴ ገዳይ ብላ አሳየቻቸው ገዳዩም ........

አብዱሏህ ኢብኑ ዙበይር ነበሩ
ኻሊድም ይህን ሲያውቁ ለምን እየለፈለፍኩ ዝም አልከኝ አሉት

አብዱሏህም
"""የተዋጋሁትኮ ለአሏህ እንጅ ለሴት ብየ አደለም """
  ጀግንነት  ነበረ ታሪካችን

https://t.me/mushitaq_tube
69 views17:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-28 15:54:44 #ታታር_ከየእጁጅና_መእጁጅ_በፊት_የመጡ_የእጁጅና_መእጁጆች

     *Part*  *2*

ታታሮች የመስቀላውያንን ድለላ ሰምተው በአባሳውያን ኺላፋ ሀብት ምራቃቸውን ዋጡ።
ይህ እንግዲህ ታታሮች ከመስቀላውያን ጋር በጣም ብዙ ልዩነት እያላቸው ነው።
ነገር ግን እስልምናን ለማጥፋት እጅና ጓንት ሆኑ። ይህ አይደንቅም! ነቢዩን ለመዋጋት የሁዶች ከሙሽሪኮች ተቆራኝተዋል! ለማንኛውም ቺንግስ ካን የሙስሊሞችን ዋና ከተማ ባግዳድን ለመዝመት ዝግጅቱን አጠናቀቀ።

  በመካከሉ ግን ታላቋ "ኸዋሪዝም የምትባል ከተማ አለች ታታሮችም ከመሪዋ ሙሀመድ ሻህ ጋር ጉርብትና ነበራቸው  ይህን ተዋግቶ ካላለፈ እንዴት ይድረስ ወደ ዋናዋ ከተማ ባግዳድ ???
ቺንግስ ካን ኸዋርዚምን ምን ያደርጋቸው ይሆን???


ቺንግስ ካን ከሙሐመድ ሻህ ጋር የነበረውን ጉርብትና የሚያፈርስበት ምክኒያት ነገር ማፈላለግ ጀመረ።
ያገኘውን የምክንያት ታሪክ ልተወውና ወደጦሩ ልግባ።
ወረራው ተጀመረ።

ቺንግስ ካን ማለቂያ የሌለው ሰራዊቱን አስከትሎ ወደ ኸዋርዚም አመራ። ሙሐመድ ኢብኑ ኸዋርዚም ሻህ በበኩሉ የቺንግስ ካንን ሀይል ለመመከት ወታደሩን ይዞ ካዛኺስታን ላይ ተገናኙ።
4 ቀን የቆየ ከባድ ፍልሚያ ተካሄደ።

ከሙስሊሞች  20,000 ሰው ሞተ። ከታታሮች ደግሞ በእጥፍ ሞተ።ከብዛቱ አንፃር ግን ጭራሽ አልተነካም።
በዚህ ከቀጠሉ ማሸነፍ እንደማይችል የተረዳው ሙሐመድ ኢብን ኸዋርዚም ሻህ ቀሪ ወታደሩን ይዞ አፈገፈገ።

ከሌሎች ኢስላማዊ ሀገራት አጋዥ ሀይል ለመጠየቅም አይችልም። ምክኒያቱም ክፍል1  እንደጠቀስነው ከታታር ወረራ በፊት ሁሉም ሙስሊም ሀገራት እርስ በርስ ሚናከሱ ነበሩ።
ታዲያ  ማን ዞር ብሎ ያየዋል?

ሙስሊም ሀገራቶቹም አንድ ጠላታቸው ከሌላ ጠላት ጋር የተፋለመ እንጂ እነርሱን ለማጥቃት ነጩን በሬ እየመረጠ መሆኑ የገባቸው ዘግይቶ ነው።

ምንም እንኳ ኸዋርዚም በጦር ብርቱ ብትሆንም የታታርን ህዝብ ብዛት መክታ የመፅናት ችሎታው ግን የላትም።

በሌላ በኩል ዋና ከተማዋን ጥሩ ጥበቃ ሲመድብላት የግዛቱን ምስራቃዊ ማለትም የታታሮች ማለፊያ የሆኑ አካባቢዎችን ያለ ጥበቃ ነበር የተዋቸው።
የተወው የጦር ታክቲክ ስህተት እንዳይመስልህ! ይልቁንስ ራስ ወዳድነቱ በመቶ ሺህ
ከሚቆጠሩ ህዝቦቹ ቤተሰቦቹንና ዘመድ አዝማዶቹን እንዲመርጥ አድርጎት እንጂ።
ደግሞ እንዲህ አይነቱ ራስ ወዳድ መሪ መውደቁ አይቀሬ ነው።

ቺንግስ ካን ወረራውን ቀጠለ።ወደ " ቡኻራ " የኢማሙል ቡኻሪ ሐገር  ቺንግስ ካን መንገዱን ቀጥሎ ቡኻራ ደረሰ። የቡኻራ ሰዎች የሚያደርጉት ጠፋቸው። እጅ ይስጡ ወይስ ይፋለሙ? የተወሰኑት እንዋጋለን ከተማችንን እንጠብቃለን ሲሉ ከፊሎቹ ደግሞ ለነፍሳችን ደህንነት ጠይቀን እጅ እንስጥ ሲሉ ሀሳብ ሰነዘሩ። መስማማት ሲያቅታቸው እንፋለማለን ያሉት ሙጃሂዶች ወደ ከተማዋ ትልቁ ምሽግ ተመሸጉ። አብዛኞቹ ከታታሮች ደህንነት ጠየቁ የደህንነት ቃል ኪዳን ከተሰጣቸው ቡጏላ ከተማዋን ከፍተው ቁልፉን ለታታሮች አስረከቡ።

ቺንግስ ካን ቡኻራ ገባ። ቃሉን አላፈረሰም ማንንም አልነካም ነበር። የመጀመሪያ ስራ ያደረገው የተመሸጉትን ሙጃሂዶች መዋጋት ነበር። ለዚህም የከተማውን ህዝብ ሙስሊም ወንድሞቹን እንዲዋጋና ምሽጉን እንዲከፍቱ አዘዛቸው። ነዋሪዎቹም ታዘዙ። ታታሮችን አንዋጋም ብለው ሙስሊም ወንድሞቻቸውን ዑለማኦቻቸውን ግን ተፋለሙ። ከንዲህ አይነቱ ማህበረሰብ ታዲያ እንዴት ድል ይጠበቃል? ከልፋት ቡጏላ በኃይል ምሽጉ ተከፈተ። ሁሉንም ሙጃሂዶች ገደሏቸው። ከዚያ ቡጏላ እጅ የሰጡትን ፈሪ ነዋሪዎች ገንዘባቸውን እንዲያስረክቡ አዘዛቸው።

ይህ የክህደቱ መጀመሪያ ነው። ቃል የሰጣቸውና ወደ ከተማው ሲገባ ቃሉን ያላፈረሰው ይህን ሰዓት እየጠበቀ ስለነበር ነው። ገንዘባቸውን በእጁ ካደረገ ቡጏላ ለወታደሮቹ የፈለጉትን እንዲያረጉ ፈቀደላቸው። ከዚያማ አላህ እንጂ ቁጥራቸውን የማያውቀው ሰዎች ተገደሉ። ህፃን፣ ሴት፣ አዛውንት፣ ነፍሰጡር ሳይለዩ እንደ በግ አረዷቸው። የፈለጉትን እየቀሙ የፈለጉትን እየገደሉ ከተማዋን አዳረሱ። ሴት ልጅን ካባቷ፣ ሚስትን ከባሏ ፊት ደፈሯቸው። ሊከላከል የፈለገ ይገደላል። ሌላው በቅጣት አይነት ይሰቃያል። መስጂዶችን፣ መድረሳዎችን፣ መኖሪያ ቤቶችን አወደሙ አቃጠሉ። ከተማዋ የእሳት ከተማ እስክትመስል ተቀጣጠለች። ግና ደራሽ የለም!

እጅ የሰጡትም ሙጃሂዶቹም ተገደሉ! ግና የሁለቱ ሞት ፍፁም ለየቅል ነው! ለዲኑ ሲል ታግሎ ሸሂድ የሆነና ራሱ አዋርዶ እንደ በግ የታረደ በምን ቀመር እኩል ሊሆኑ ይችላሉ?!
ቡኻራ በዚህ መልኩ ወደመች! ግን ይህ የሰቆቃው መጨረሻ ይሆን? በፍፁም አይደለም ይህ መግቢያው ነው።
ታዲያ ከዚህ በጏላስ ምን ይከሰት ይሆን......

ክፍል ....3

     ...ይቀጥላል https://t.me/mushitaq_tube
80 views12:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ