Get Mystery Box with random crypto!

#ታታር_ከየእጁጅና_መእጁጅ_በፊት_የመጡ_የእጁጅና_መእጁጆች      *Part*  *2* ታታሮች | Mushitaq tube ሙሽታቅ ቲዩብ

#ታታር_ከየእጁጅና_መእጁጅ_በፊት_የመጡ_የእጁጅና_መእጁጆች

     *Part*  *2*

ታታሮች የመስቀላውያንን ድለላ ሰምተው በአባሳውያን ኺላፋ ሀብት ምራቃቸውን ዋጡ።
ይህ እንግዲህ ታታሮች ከመስቀላውያን ጋር በጣም ብዙ ልዩነት እያላቸው ነው።
ነገር ግን እስልምናን ለማጥፋት እጅና ጓንት ሆኑ። ይህ አይደንቅም! ነቢዩን ለመዋጋት የሁዶች ከሙሽሪኮች ተቆራኝተዋል! ለማንኛውም ቺንግስ ካን የሙስሊሞችን ዋና ከተማ ባግዳድን ለመዝመት ዝግጅቱን አጠናቀቀ።

  በመካከሉ ግን ታላቋ "ኸዋሪዝም የምትባል ከተማ አለች ታታሮችም ከመሪዋ ሙሀመድ ሻህ ጋር ጉርብትና ነበራቸው  ይህን ተዋግቶ ካላለፈ እንዴት ይድረስ ወደ ዋናዋ ከተማ ባግዳድ ???
ቺንግስ ካን ኸዋርዚምን ምን ያደርጋቸው ይሆን???


ቺንግስ ካን ከሙሐመድ ሻህ ጋር የነበረውን ጉርብትና የሚያፈርስበት ምክኒያት ነገር ማፈላለግ ጀመረ።
ያገኘውን የምክንያት ታሪክ ልተወውና ወደጦሩ ልግባ።
ወረራው ተጀመረ።

ቺንግስ ካን ማለቂያ የሌለው ሰራዊቱን አስከትሎ ወደ ኸዋርዚም አመራ። ሙሐመድ ኢብኑ ኸዋርዚም ሻህ በበኩሉ የቺንግስ ካንን ሀይል ለመመከት ወታደሩን ይዞ ካዛኺስታን ላይ ተገናኙ።
4 ቀን የቆየ ከባድ ፍልሚያ ተካሄደ።

ከሙስሊሞች  20,000 ሰው ሞተ። ከታታሮች ደግሞ በእጥፍ ሞተ።ከብዛቱ አንፃር ግን ጭራሽ አልተነካም።
በዚህ ከቀጠሉ ማሸነፍ እንደማይችል የተረዳው ሙሐመድ ኢብን ኸዋርዚም ሻህ ቀሪ ወታደሩን ይዞ አፈገፈገ።

ከሌሎች ኢስላማዊ ሀገራት አጋዥ ሀይል ለመጠየቅም አይችልም። ምክኒያቱም ክፍል1  እንደጠቀስነው ከታታር ወረራ በፊት ሁሉም ሙስሊም ሀገራት እርስ በርስ ሚናከሱ ነበሩ።
ታዲያ  ማን ዞር ብሎ ያየዋል?

ሙስሊም ሀገራቶቹም አንድ ጠላታቸው ከሌላ ጠላት ጋር የተፋለመ እንጂ እነርሱን ለማጥቃት ነጩን በሬ እየመረጠ መሆኑ የገባቸው ዘግይቶ ነው።

ምንም እንኳ ኸዋርዚም በጦር ብርቱ ብትሆንም የታታርን ህዝብ ብዛት መክታ የመፅናት ችሎታው ግን የላትም።

በሌላ በኩል ዋና ከተማዋን ጥሩ ጥበቃ ሲመድብላት የግዛቱን ምስራቃዊ ማለትም የታታሮች ማለፊያ የሆኑ አካባቢዎችን ያለ ጥበቃ ነበር የተዋቸው።
የተወው የጦር ታክቲክ ስህተት እንዳይመስልህ! ይልቁንስ ራስ ወዳድነቱ በመቶ ሺህ
ከሚቆጠሩ ህዝቦቹ ቤተሰቦቹንና ዘመድ አዝማዶቹን እንዲመርጥ አድርጎት እንጂ።
ደግሞ እንዲህ አይነቱ ራስ ወዳድ መሪ መውደቁ አይቀሬ ነው።

ቺንግስ ካን ወረራውን ቀጠለ።ወደ " ቡኻራ " የኢማሙል ቡኻሪ ሐገር  ቺንግስ ካን መንገዱን ቀጥሎ ቡኻራ ደረሰ። የቡኻራ ሰዎች የሚያደርጉት ጠፋቸው። እጅ ይስጡ ወይስ ይፋለሙ? የተወሰኑት እንዋጋለን ከተማችንን እንጠብቃለን ሲሉ ከፊሎቹ ደግሞ ለነፍሳችን ደህንነት ጠይቀን እጅ እንስጥ ሲሉ ሀሳብ ሰነዘሩ። መስማማት ሲያቅታቸው እንፋለማለን ያሉት ሙጃሂዶች ወደ ከተማዋ ትልቁ ምሽግ ተመሸጉ። አብዛኞቹ ከታታሮች ደህንነት ጠየቁ የደህንነት ቃል ኪዳን ከተሰጣቸው ቡጏላ ከተማዋን ከፍተው ቁልፉን ለታታሮች አስረከቡ።

ቺንግስ ካን ቡኻራ ገባ። ቃሉን አላፈረሰም ማንንም አልነካም ነበር። የመጀመሪያ ስራ ያደረገው የተመሸጉትን ሙጃሂዶች መዋጋት ነበር። ለዚህም የከተማውን ህዝብ ሙስሊም ወንድሞቹን እንዲዋጋና ምሽጉን እንዲከፍቱ አዘዛቸው። ነዋሪዎቹም ታዘዙ። ታታሮችን አንዋጋም ብለው ሙስሊም ወንድሞቻቸውን ዑለማኦቻቸውን ግን ተፋለሙ። ከንዲህ አይነቱ ማህበረሰብ ታዲያ እንዴት ድል ይጠበቃል? ከልፋት ቡጏላ በኃይል ምሽጉ ተከፈተ። ሁሉንም ሙጃሂዶች ገደሏቸው። ከዚያ ቡጏላ እጅ የሰጡትን ፈሪ ነዋሪዎች ገንዘባቸውን እንዲያስረክቡ አዘዛቸው።

ይህ የክህደቱ መጀመሪያ ነው። ቃል የሰጣቸውና ወደ ከተማው ሲገባ ቃሉን ያላፈረሰው ይህን ሰዓት እየጠበቀ ስለነበር ነው። ገንዘባቸውን በእጁ ካደረገ ቡጏላ ለወታደሮቹ የፈለጉትን እንዲያረጉ ፈቀደላቸው። ከዚያማ አላህ እንጂ ቁጥራቸውን የማያውቀው ሰዎች ተገደሉ። ህፃን፣ ሴት፣ አዛውንት፣ ነፍሰጡር ሳይለዩ እንደ በግ አረዷቸው። የፈለጉትን እየቀሙ የፈለጉትን እየገደሉ ከተማዋን አዳረሱ። ሴት ልጅን ካባቷ፣ ሚስትን ከባሏ ፊት ደፈሯቸው። ሊከላከል የፈለገ ይገደላል። ሌላው በቅጣት አይነት ይሰቃያል። መስጂዶችን፣ መድረሳዎችን፣ መኖሪያ ቤቶችን አወደሙ አቃጠሉ። ከተማዋ የእሳት ከተማ እስክትመስል ተቀጣጠለች። ግና ደራሽ የለም!

እጅ የሰጡትም ሙጃሂዶቹም ተገደሉ! ግና የሁለቱ ሞት ፍፁም ለየቅል ነው! ለዲኑ ሲል ታግሎ ሸሂድ የሆነና ራሱ አዋርዶ እንደ በግ የታረደ በምን ቀመር እኩል ሊሆኑ ይችላሉ?!
ቡኻራ በዚህ መልኩ ወደመች! ግን ይህ የሰቆቃው መጨረሻ ይሆን? በፍፁም አይደለም ይህ መግቢያው ነው።
ታዲያ ከዚህ በጏላስ ምን ይከሰት ይሆን......

ክፍል ....3

     ...ይቀጥላል https://t.me/mushitaq_tube